
September 2, 2020 – Konjit Sitotaw
የአለም ባንክ ቃል አቀባይ ዴቪድ ኤም ቴኺስ ለኢትዮጵያ ቼክ ባደረሱት መረጃ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሪፎርም እና ለሚያስፈልገው የፋይናንስ አቅም “ሙሉ ድጋፍ” እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።
ከባንኩ ቃል አቀባይ ዴቪድ ኤም ቴኺስ ከደቂቃዎች በፊት ለኢትዮጵያ ቼክ የደረሰው ይህ መረጃ እንደሚያመለክተው ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ሪፎርም እና ለሚያስፈልገው የፋይናንስ አቅም “ሙሉ ድጋፍ” እንደሚሰጥ ባንኩ አስታውቋል።
ባንኩ በIDA-19 እቅዱ ኢትዮጵያ ውስጥ ፋይናንስ የሚያረጋቸው የልማት ፕሮግራሞች 2.9 ቢሊዮን ዶላር መሆኑን ጠቅሶ ለባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ቦርድ የሚቀርቡ ፕሮጀክቶች የተለመደ ሂደታቸውን ጠብቀው እያለፉ እንደሆነ ገልጿል።
የዓለም ባንክ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በቅርበት መስራቱን እንደሚቀጥል አረጋግጧል!
ባንኩ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት እያከናወነ ያለውን ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ በፋይናንስ መደገፉን እንደሚቀጥል አስታውቋል።
8:53 AM · Sep 2, 2020·Twitter Web App
59
Retweets
21
Quote Tweets
158
Likes
ባንኩ በመግለጫው ከፈረንጆቹ ሀምሌ ወር 2020 እስከ ሰኔ ወር 2023 ድረስ ኢትዮጵያ ለምታከናውናቸው የልማት ስራዎች የሚሰጠው አጠቃላይ የፋይናነስ ድጋፍ 2 ነጥብ 9 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደሚደርስ አመልክቷል።
የበጀት ድጋፍን ጨምሮ ባንኩ የፋይናስ ድጋፍ የሚያደረግባቸው የተለያዩ ፕሮጀክቶች ለዓለም ባንክ ስራ አስፈፃሚ ቦርድ ለውይይት እየቀረቡ የመፅደቃቸው ጉዳይም መደበኛ አካሄድን ተከትሎ እየተከናወነ መሆኑን አብሮ ገልጿል።የአለም ባንክ ለኢትዮጵያ ሊያቀርብ የነበረውን የ2 ቢልዮን ዶላር የድጋፍ እና ብድር ስምምነት አቋርጧል የሚል ዜና ዛሬ በዋዜማ ሬድዮ ተሰርቶ በስፋት ሶሻል ሚድያ ላይ ተጋርቷል።–በዘገባው መሰረት የተቋረጠው ስምምነት የኮሮና ቫይረስ ጫናን ለመከላከል እና ለሰብዓዊ ስራዎች ከሚውለው ውጪ ለኢትዮጵያ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሀ ግብር ባንኩ ሊያቀርበው የነበረውን ነው።መረጃውን ለማጣራት ለኢትዮጵያ መንግስት እንዲሁም ለአለም ባንክ ኢትዮጵያ ቼክ ጥያቄ አቅርቦ ነበር።–የኢትዮጵያ መንግስት መረጃው የሀሰት እንደሆነ ገልፆ “ይህ በለጋሽ ሀገራት እና በኢትዮጵያ መሀል ያለውን ግንኙነት ለማጠልሸት ታስቦ የተሰራጨ ነው። እንኳን ድጋፉ ሊቋረጥ በዚህ ዙርያ ምንም አይነት ውይይትም ሆነ ንግግር አልነበረም” ብሏል።–ኢትዮጵያ ቼክ ቀድሞ ከባንኩ በደረሰው መረጃ መሰረት ይህ ዛሬ የሚጠበቀው መግለጫ “የአለም ባንክ ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዘርፍ ለውጥ ያለውን ሙሉ ድጋፍ የሚገልፅበት እንዲሁም IDA-19 በተባለው የድጋፍ ማእቀፍ ከፍ ያለ ፋይናንስ ባንኩ እንደሚሰጥ የሚያረጋግጥበት” ነው ተብሏል።
