Source: https://amharic.voanews.com/a/covid-vaccine-9-2-2020/5568071.html

https://gdb.voanews.com/082474A9-7F6B-4F04-A78D-DA97477270E6_cx0_cy4_cw0_w800_h450.jpg

መስከረም 02, 2020

ፎቶ ፋይል

ፎቶ ፋይል

Print ዋሺንግተን ዲሲ — ሙከራ ላይ ያሉ በርካታ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባቶች የመጨረሻ የሙከራ ደረጃ ላይ መድረሳቸውን በክትባቶቹ ሥራ አመራር ውስጥ ያሉ ባለሥልጣናት ገለፁ።

የእንግሊዝ እና የስዊድን የመድሃኒት ኩባኒያው አስትራዜኔካ ሰኞ ባወጣው መግለጫ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሚከናወነው የክትባቱ የመጨረሻ ሙከራ ከተለያዩ ዘሮች ብሄሮችና መልክዓ ምድራዊ አካባቢዎች በተውጣጡ ሰላሳ ሺህ አዋቂዎች በማሳተፍ እንደሚጠናቀቅ አመልክቷል።

የዩናይትድ ስቴትስ ብሄራዊ የጤና ተቋማት ኤንአይኤች ተሰርቶ ሞደርና በተባለው ኩባኒያ ተመርቶ የሚወጣው ክትባትም ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ብዙ ሺህዎች የተቆጠሩ ሰዎች በማሳተፍ ሙከራ ላይ ውሏል።