ግራፊክስ

ባለፉት 24 ሰዓታት ለ 20 ሺህ 778 ሰዎች በተደረገው ምርመራ 804 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በዚህም መሰረት በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 55 ሺህ 213 አድርሶታል።

የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጋራ በሚያወጡት ዕለታዊ መግለጫ መሰረት 10 ሰዎች በዛሬው ዕለት መሞታቸው ተገልጿል። አገሪቱ በኮሮናቫይረስ ያጣቻቸው ዜጎች ቁጥርም 856 ሆኗል።

ከዚህም በተጨማሪ 380 ሰዎች ማገገማቸው የተገለፀ ሲሆን ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 20 ሺህ 283 ደርሷል።

ኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ ያከናወነቻቸው የላብራቶሪ ምርመራዎችም 970 ሺህ 591 ሆኗል።