ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 25,158 የላብራቶሪ ምርመራ 1206 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን የጤና ሚኒስትር ተናግሯል፡፡
–
ባለፋት 24 ሰዓታት የ21 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 918 አድርሶታል።
–
በሌላ በኩል በትናንትናው ዕለት 531 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን ይህም ከበሽታው የገገሙ ሰዎችን ቁጥር 21,307 አድርሶታል፡፡
–
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 58,672 ደርሷል፡፡
