September 7, 2020

ፍርድ ቤቱ የአሥራት ጋዜጠኞች በዋስትና እንዲፈቱ ወሰነ

አራዳ የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሥራት ጋዜጠኞች እያንዳንዳቸው በ10 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ውሳኔ አስተላልፏል።

ፖሊስ በተደጋጋሚ መረጃ አቀርባለሁ በሚል ቀጠሮ እንዲሰጠው ቢጠይቅም በተሰጠው ቆጠሮ አለኝ ያለውን መረጃ ማቅረብ አልቻለም። በመሆኑም ፍርድ ቤቱ በላይ ማናዬ፣ ሙሉጌታ አንበርብር፣ ምስጋናው ከፈለኝ እና ዮናታን ሙሉጌታ በእያንዳንዳቸው በ10 ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲለቀቁ ወስኗል።