የክልሉ ምርጫ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም ለቢቢሲ እንደገለፁት ለምርጫ ከተመዘገበው መራጭ 97 በመቶ ያህሉ መርጧል። ለምርጫ የተመዘገቡ ነዋሪዎች ከለሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ጀምረው በመውጣት መምረጣቸውን የገለፁት ኮሚሽነሩ ከእኩለ ቀን በኋላ አብዛኛው የመራጭ ጣብያዎች ባዶ እንደነበሩ ገልፀዋል።
በምርጫ ወቅት ይህ ነው የሚባል ያጋጠመ ችግር አለመኖሩን የገለፁት ኮሚሽነር ሙሉ ቀን፣ ከተቃዋሚም ፓርቲዎችም ቢሆን የደረሳቸው ቅሬታ አለመኖሩን ገልፀዋል።
በአንዳንድ የምርጫ ጣብያዎች ለምርጫ የተመዘገበ ነዋሪ ሙሉ በሙሉ መምረጡን በማንሳትም አጠቃላይ መራጩ 97 በመቶ መሆኑን ገልፀዋል። የድምጽ ቆጠራው በጣብያ ደረጃ እስከ ጠዋት ድረስ ያልቃል ያሉት ኮሚሽነሩ የምርጫው ውጤት መስከረም 2 ይገለፃሉ ተብሎ መታቀዱን ገልፀዋል።
BBC