September 9, 2020 – Konjit Sitotaw
ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዮት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው ተሾሙ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስን የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዮት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ አድርገው ሾሙ።ሹመቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት መስጠታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል።
Office of the Prime Minister – Ethiopia@PMEthiopia
ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስን የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዮት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ አድርገው ሾመዋል።
PM Abiy Ahmed appointed Professor Beyene Petros as Deputy Director General of Policy Research Institute.
28 Retweets 13 Quote Tweets 320 Likes
ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ለረጅም በተቃዋሚ ፓርቲ መሪነት እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በመምህርነት ሲያገለግሉ የቆዩ ምህሁር ናቸው።
–
ከዚህ ባሻገርም ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በሽግግር መንግሥቱ የመጀመሪያ ዓመታት ላይ ለአጭር ጊዜ የትምህርት ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትር አገልግለው የነበሩ ሲሆን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልም ነበሩ።
–
ፕሮፌሰሩ ኅብረትና መድረክን በመሳሰሉ የፓርቲዎች ስብስቦች እንዲፈጠሩ ጉልህ ሚና የነበራቸው ሲሆን ፓርቲዎቹን በአመራርነትም አገልግለዋል።

