አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጳጉሜ 4 ቀን 2012 ዓ.ም አዲስ…

September 9, 2020

የሀሰት ትርክትና ጥላቻን በተለያዬ መንገድ ለመቀልበስ ያለመ ዓለም አቀፍ የአማራ ህብረት መመስረቱ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ      ጳጉሜ 4 ቀን 2012 ዓ.ም          አዲስ…

የሀሰት ትርክትና ጥላቻን በተለያዬ መንገድ ለመቀልበስ ያለመ ዓለም አቀፍ የአማራ ህብረት መመስረቱ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጳጉሜ 4 ቀን 2012 ዓ.ም አዲስ…

የሀሰት ትርክትና ጥላቻን በተለያዬ መንገድ ለመቀልበስ ያለመ ዓለም አቀፍ የአማራ ህብረት መመስረቱ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጳጉሜ 4 ቀን 2012 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በአማራው ላይ ካለፉት በርካታ ዓመታት ጀምሮ በጽንፈኞች እየተነገረ ያለ የሀሰት ትርክትንና ጥላቻን ለመቀልበስ ያለመ ዓለም አቀፍ የአማራ ህብረት መመስረቱንና ህጋዊ እውቅናም ማግኘቱን የገለፀው የህብረቱ ጸሀፊ ወጣት መሳፍንት መንግስቱ ነው። ወጣት መሳፍንት ከባህር ዳር ለአማራ ሚዲያ ማዕከል እንደገለፀው ህብረቱ የመንግሥት አካል ያልሆነ፣ለትርፍ ያልተቋቋመ፣ከማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት ያልወገነ እና ሕጋዊ ዓላማን ለማሳካት ተመዝግቦ የሚንቀሳቀስ የሲቪክ ተቋም ነው፡፡ የዓለም አቀፍ የአማራ ህብረት ዋና ዓላማም በቅኝ ገዥዎች ጭቅላት ተፀንሶ፣በዘመነ-ጣሊያን ተወልዶ፣ በዘመነ – ወያኔ የጎለመሰውን አማራን ከፖለቲካ፣ከኢኮኖሚ እና ከሕገ-መንግሥት ሥልታዊ በሆነ መንገድ የማግለል ሥርዓትን ለመቀልበስ እንደሆነ ገልጧል፡፡ አማራውን ያጠለሸ የውሸት (የፈጠራ) ታሪክ መቀልበስ እንዳለበት አብዛኛው የኢትዮጵያውያ ህዝብ ይስማማል ብሎ ማህበሩ እንደሚያምን የተገለፀ ሲሆን ኢትዮጵያውያንን ማናከስንና ኢትዮጵያን መፈረካከስን መሠረት ያደረገው ህወሀት የአማራን ታሪክ ያረከሰና ለኢትዮጵያ ሀገሩ የፈፀማቸውን ተግባራት ያንኳሰሰ የፈጠራ ትርክት ላይ መጠመዱንም ጠቅሷል። አማራ ከሌሎች የኢትዮጵያ ልጆች ጋር የነበረውን ሁለንተናዊ ግንኙነት በጨቋኝና- ተጨቋኝ ታሪክ ላይ የተመሰረተ እንደነበር በማስመሰል በውሸትና በስሜት ተገፋፍተው አማራን እንዲገድሉ፣እንዲያፈናቅሉ፣እንዲያቃጥሉና እንዲበድሉ በመላዋ ኢትዮጵያ መዋቅር ዘርግቶ፣በጨቅላ ህፃናት አእምሮ ጭምር እንዲቀረፅ ሥርዓተ-ትምህርት አዘጋጅቶ መስራቱን አውስቷል። አማራ ለኢትዮጵያ የፈፀማቸውን ገድላት ከተቀበሩበት አውጥቶ፣በህያው ምሁራን ምሥክርነት አስረግጦ ወደ እውነተኛው የኢትዮጵያ ታሪክ ለመመለስ ያለመው ህብረቱ ቀደምት እና ሀቀኛ የታሪክ ድርሳናትንና በህይወት ያሉ ሀገር- አቀፍና ዓለም-አቀፍ ምሁራንን በምስክርነት እያቀረበ፣ ልዩ ልዩ የመገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም እንደሚሰራ አስታውቋል። የአማራ አርሶ አደሮች፣ነጋዴዎች፣ምሁራን፣ ወጣቶችና በሌሎች የሙያ መስኮች የተሠማሩ ወገኖች ህብረት መሥርተው፣ተደማምጠውና ተናበው እንዲሠሩ፣የአማራ ህልውና እንዲከበርና በሀሰት የጠለሸው ታሪኩ እንዲስተካከል ከመስራት አንጻር የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ የማስተባበር ተልዕኮ እንዳለውም ተገልጧል፡፡ አማራው፣ ኢትዮጵያ ባላት የተፈጥሮ ጸጋ፣ሰው ሰራሽ ሀብት እና ለሀገር ባበረከተው ልክ እውነተኛ ታሪኩ ተነግሮ፣ህልውናው ተከብሮ እንዲኖር፣ እንዲለማና ተጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ በማስተማር፣በማሰልጠን፣በማንቃትና በማብቃት ረገድም አልሞ እንደሚሰራ ነው የህብረቱ ጸሀፊ የተናገረው። ህብረቱ በኢፊዲሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ነሀሴ 11 ቀን 2012 ዓ.ም ተመዝግቦ ህጋዊ ሰውነት የተሰጠው መሆኑ ታውቋል። ከዓለም አቀፍ የአማራ ህብረት ጸሀፊ ከወጣት መሳፍንት መንግስቱ ጋር የተደረገው ቆይታ በአሚማ የዩቱብ አድራሻ ይጠብቁ።

Source: Link to the Post