Image may contain: one or more people, people standing, flower and outdoor

ያቀዳችሁትና ያሰባችሁት፣የምትመኙት መልካም ሁሉ በገሃድ የምታዩበትም ዓመት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።አገራችን የተደቀነባትን አደጋ በጋራ አክሽፈንም  ሰላምና አንድነትዋን  የምናስጠብቅበትም ዓመት ይሁንልን።

በአንገብጋቢው ጉዳይ ላይ ድርጅታችን ያወጣውን መግለጫ ሳካፍላችሁ እናንተም ባላችሁበት አጋርነታችሁን እንድትገልጹ በትህትና እጠይቃለሁ።

ድር ቢያብር አንበሳ ያስር!r

ከአርባ ስድስት ዓመት በፊት በእስርቤት እያለሁ ካወጣኳቸውና ከእስር ባልደረቦቼ ጋር በዘመርናቸው  ሶስት መዝሙሮች በአንዱ ውስጥ የሚከተለው ስንኝ ይገኝበት ነበር ፣ታዲያ አለመታደል ሆኖ ያ መልእክትና ጥሪ ተግባራዊ ሳይሆን  ዓመታት አልፋው ግማሽ ዘመን ሊሆነው ነው። ሌሎቹ መዝሙሮች በስፋት የሚታወቀው ተነሳ ተራመድ የሚለው ሲሆን ሌላው ደግሞ ይኖራል ይኖራል  የሚለው ነበር።

በስማን ያገሬ ሰው ውስጥ የሚከተለው ስንኝ ይገኝበታል፤ለአሁኑም ላለንበት ሁኔታ ተገቢ ጥሪ ስለመሰለኝ አቅርቤዋለሁ።

ስማኝ ያገሬ ሰው ባንድ ላይ ተነሳ፣

ድር ከተባበረ ይጥላል አንበሳ።

እስላም ወይ ክርስቲያን ሳይባል በሙሉ፣

የጎሳ ልዩነት ሳይኖር በመሃሉ፣

ያገርን ነቀርሳ መንቅላችሁ ጣl

ባላባት ጭሰኛ ማለቱ ለምን ነው፣

ልዩነት የለውም የሰው ልጅ እኩል ነው። ይከኛውን አማራ ኦሮሞ፣ትግሬ ወላይታ፣አፋር  ቤኒሻንጉል…..ወዘተ በሚለው ሊለወጥ ይችላል።ምክንያቱም ባላባታዊ ስርዓት ጠፍቷል ተብሎ ከታመነበት።ግን በባላባቱ ቦታ ሕዝቡ የመንግሥት ጭሰኛ መሆኑ አልቀረለትም።

መልካም ንባብ ይሁንላችሁ

አገሬ አዲስ