September 11, 2020 – Konjit Sitotaw
ሕወሓት በትግራይ ክልላዊ ምርጫ 98.2 በመቶ በማግኘት አሸናፊ ሆኗል።
ቢቢሲ – በትግራይ ጳጉሜ 4/2012 በተደረገው ክልላዊ ምርጫ ሕወሓት በአብላጫ ድምጽ አሸነፈ!
የክልሉ የምርጫ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሙሉ ወርቅ ኪዳነማርያም ለቢቢሲ እንደተናገሩት ሕወሓት ከአጠቃላይ የመራጮች ድምጽ 98.2 በመቶ በማግኘት አሸናፊ ሆኗል።

በዚህም የተነሳ የክልሉ ምክር ቤት ካለው መቀመጫ 152 ወንበር በሕወሓት የተያዘ ሲሆን 38 ደግሞ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች ይከፋፈላል ተብሏል።
ሕወሓት የምክር ቤቱን መቀመጫ 80 በመቶ ሲይዝ በቅርቡ በነበረው ውሳኔ መሰረት ቀሪው 20 በመቶ ደግሞ የምክር ቤቱ ምርጫ በምርጫ ተፎካካሪ ለነበሩ ፓርቲዎች ይከፋፈላል ተብሏል።
80 በመቶውን የያዘው ፓርቲ ቀሪው 20 በመቶ ላይ ይፎካከራል ወይ የሚለው ላይ ድርድር እንደሚኖር ይጠበቃል።
በምርጫው ባይቶና ፣ ትግራይ ነጻነት፣ ሳልሳይ ወያነ እንዲሁም አሲምባ እንደ ቅደም ተከተላቸው ድምጽ ማግኘታቸው ተገልጿል።
በክልሉ ምርጫ ክልሉን የሚያስተዳድረውን ህወሓትን ጨምሮ 5 ፓርቲዎች መሳተፋቸው ይታወሳል።
በትግራይ ክልል የተደረገው ምርጫ ውጤት ፦
- – ህወሓት : (98.2 %)
- – ውድብ ብሄራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ (ባይቶና) : (0.8%)
- – ውድብ ናፅነት ትግራይ: (0.71%)
- – ውድብ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ: (0.27%)
- – ዴሞክራውያዊ ውድብ ዓሲምባ: (0.01%)
- በዓድዋ ከተማ ህወሓትን ወክለው የቀረቡት ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤ : 59,369
- በመቐለ ወይዘሮ ኬርያ ኢብራሂም : 154,226
- በኣላማጣ አቶ ጌታቸው ረዳ : 94,836
- በመቐለ የባይቶና ሊቀመንበር አቶ ኪዳነ አመነ : 12,048
- በቦራ ሰለዋ የሳልሳይ ወያነ ሊቀመንበር አቶ ሃይሉ ጎደፋይ : 109
- በዓዲግራት የውድብ ናፅነት ትግራይ ሊቀመንበር ግርማይ በርሀ : 1,703
- በዓኒቴና የዓሲምባ ሊቀ መንበር አቶ ዶሪ አስገዶም : 156 ድምፅ በማግኘት ተመርጠዋል።
