On Sep 13, 202082

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 7 ሺህ 162 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 413 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 64 ሺህ 301 ደርሷል።

በሌላ በኩል ባለፉት 24 ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ የ17 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በዚህም በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎቸ ቁጥር 1 ሺህ 13 መድረሱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ያሰፈሩት መረጃ ያመለክታል።

በ24 ሰዓታት ውስጥ 490 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ስሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 24 ሺህ 983 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

እንዲሁም 38 ሺህ 303 ሰዎች ደግሞ በአሁን ወቅት ቫይረሱ የሚገኝባቸው ሲሆን 342 ፅኑ ህሙማን ደግሞ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል ተብሏል።

#FBC