የዩኒቨርሲቲዎች መከፈተን በተመለከተ ዶክተር ሙሉ ነጋ (የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ) ጠይቀናቸው ተከታዩን መረጃ ሰጥተውናል ፦ ቲክቫህ ኢትዮጵያ

– በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ከዚህ ቀደም በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉ።
– የዩኒቨርሲቲዎች ዳግም መከፈት ውሳኔ የሚያገኘው በጤና ሚኒስቴር እና በኮቪድ-19 መከላከል ግብረ ኃይል በመሆኑ የነሱ ምላሽ እየተጠበቀ ነው።
– ዩኒቨርሲቲዎች እያደረጉ ያሉትን ዝግጅት በተመለከተ (ምን ያህል ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጁ ሆነዋል? የሚለውን ለመገምገም) ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር ፣ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የሚቀጥለው ሳምንት ሰፊ የውይይት መድረክ ሊድረግ ዝግጅት እየተደረገ ነው።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሙሉ ነጋ ለተማሪዎች ሊሰጥ ስለታሰበው የተከታታይ ምዘና ተከታዩን መረጃ አግኝቷል ፦
– ተማሪዎች ከሚማሩበት ተቋም የሚላክላቸውን የኮርስ ማቴሪያሎች በማንበብ ለቀጣይ ስራ ዝግጁ እንዲሆኑ ስራዎች ሲከናወኑ ቆይቷል ፤ ይህ ስራ በምዘና መደገፍ ስላለበት ነው ውሳኔው የተላለፈው።
– ተማሪዎች በቤታቸው ሆነው የሚላክላቸውን የኮርስ ማቴሪየሎችን ይበልጥ እንዲየነቡ ለማድረግ ፣ ያነበቡትንም ለመመዘን እስከ 30 % ተከታታይ ምዘና ይሰጣቸዋል።
– ከ30 % የሚያዘው ምዘና ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲዎች ተከፍተው እስኪመለሱ ድረስ ከትምህርታቸው እንዳይርቁ ለማነሳሳትም ጭምር ነው።
– ተማሪዎች የሚያነቡትን ማቴሪያል ከ30% ቤት ውስጥ ሆነው በሚሰሩት አሳይመንት ይመዘናሉ፤ ይህ ማለት ተማሪዎች የሚወስዱትን ኮርስ 30% በቤታቸው ሆነው ይጨርሳሉ (ምዘናው እንደየዩኒቨርሲቲው ሊለያይ ይችላል ከ5 % ፣ 10 % …እያደረጉ መጨረስ ይችላሉ)
– የተቀረው 70 % ደግሞ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲመለሱ የሚወስዱት ምዘና ይሆናል።
– ተማሪዎች ትምህርት የሚያስፈልጋቸው ለራሳቸው መሆኑን አውቀው የሚላክላቸውን ማቴሪያሎች ተግተው እንዲያነቡት መልዕክት ተላልፏል።
(ሁሉንም የመንግስት እና የግል ዩኒቨርሲቲዎች ይመለከታል)