September 17, 2020

የመከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ መግለጫ

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የተፈጠሩ ችግሮችን ለማረጋጋት የመከላከያ ሰራዊት በወሰደው ሁሉን አቀፍ ዘመቻ በግጭት ምክንያት ከቀያቸው የተፈናቀሉ ከ25 ሺህ በላይ ዜጎች ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ ማድረጉን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጀኔራል መሀመድ ተሰማ ሰሞነኛ ጉዳዮችን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ ተከታዩን ብለዋል ፦

– በክልሉ የተፈጠረው የፀጥታ ችግር ከክልሉ የፀጥታ ኃይሎች አቅም በላይ አልነበረም ሊከሰትም አይገባው ነበር።

– ችግሩ በተፈጠረበት ሰዓት መከላከያ የራሱ ተልዕኮ ላይ ነበር ሠራዊቱ ወደ ስፍራው በማቅናት የአከባቢውን ሰላምና ደህንነት የማስከበር ስራ በጀግንነት ተሰርቷል።

– መከላከያ ከገባ በኋላ በአጥፊዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ በመውሰዱ አሁን በክልሉ ያለው ሁኔታ ወደ ቀድሞ ሰላማዊና መረጋጋት እንቅስቃሴ ተመልሷል።

– በማህበራዊ ሚዲያዎች “መካላከያ ቀድሞ ወደ ስፍራው አልደረሰም” በሚል እየተናፈሰ ያለው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው።

– በክልሎች የፀጥታ ችግሮች ሲከሰቱ የማረጋጋት ግዴታ በዋናነት የክልልና የወረዳ የጸጥታ ኃይል ነው መከላከያ የራሱ ግዳጆች ቢኖሩትም ከክልሎቹ አቅም በላይ የሆነ የፀጥታ ችግር ሲያጋጥም አስፈላጊውን እርምጃ እየወሰደ ይገኛል።

– በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መከላከያ ግዳጅ እንደተሰጠው ከ150 ኪሎ ሜትር ውስጥ 50 ኪሎ ሜትሩን በእግሩ በመጓዝ በታጣቂዎች ላይ አስፈላጊውን እርምጃ ወስዷል።

(ኢቲቪ)