2020-09-17
ስለ ዐማራ ለመጮኽ ዐማራ መሆን አይጠበቅብኝም። ሰው መሆን በቂ ነው!!!
[ ዘመድኩን በቀለ ]
እንዴት ነህ አማራ?
«ዘውድአለም ታደሰ»
እንዴት ነህ ግዮኑ – እንዴት ነህ አማራ አንት የታሪክ ዶሴ – አንት የሰሜን ጮራ ተነሳብህ አሉ – የተሳለ ሳንጃ – የጨከነ ካራ
እንዴት ነህ አማራ?
ገደሉህ ይሉኛል – አረዱህ ይሉኛል ህመምክን ስሰማ – መንፈሴን ያመኛል ደከመ ይሉኛል ፥ መረረው ይሉኛል ላድንህ ባልችልም ፥ የቀመስኩት ሁሉ ይጎመዝዘኛል!!
እንዴት ነህ አማራ?
አንተ ያገር ካስማ – አንተ ያገር አጥር
ግማሽ ጎኔ ሞተ – ሞትህን ስቆጥር
ተሸለተ ሲሉኝ – መኖሬን ጠላሁት
ሳቅና ደስታዬን – በቅፅበት አጣሁት!!
እንዴት ነህ አማራ?
ደምህን እረጭተህ – ፈትተህ የለቀቅከው ፊደል ቀርፀህ
ሰጥተህ – ቀድመህ ያሳወቅከው ሰላምክን ሲያውከው … አጥንት ከስክሰህ – ባቀናሀት ሐገር ትገባበት ጨንቆህ – ሰርክ ስትቸገር በነፃ ገበያ ፥ በዘመነ ቁማር ፥ በርካሽ ሲሸጡህ ዘርህን መንዝረው ፥ጎሳህን አስልተው ፥ ከመሃል ሲያወጡህ እርጥብ አፈር ምሰው የቀበሩህ ለታ ሰላሜ እንደዝናር ከነፍሴ ተፈታ!! እንዴት ነህ አማራ? ጀግናማ ጀግና ነህ ፥ ምንሽር ትራስህ ለሐገር የምትተርፍ ፥ እንኳን ላንድ እራስህ ገላህ ቢራቆትም ፥ ክብርህ ሁሌ ሙሉ
ካንተ የተጣላ – ፍፃሜው አያምርም – መውደቅ ነው እድሉ!!
የተነሳህ ለታ አጥር ላያቆምህ እሳቱ ላይፈጅህ
ከሰማየ ሰማይ ተቀብቷል እጅህ!!
እንዴት ነህ አማራ?

