አቶ መስፍን ወ/ማርያምን (ለፕሮፌሰርነታቸው ምንም ዓይነት መረጃ ስለሌለ እንደሆነ አቶ ያልኳቸው ግንዛቤ ይያዝልኝ) እና ሌሎች የተማርን የተመራመርን ነን!” የሚሉ መሰል ግልብ ተደማሪ ግለሰቦች ፊደል እንደቆጠረ ሰው ኧረ እስኪ ቆይ ገና ምንም ሳናይ ቀድመን ካመሰገንን ኋላ ለማማት ለመተቸት ይቸግረናልና ብንቆጠብ ይሻለናል!” ሳይሉ ወያኔ/ኢሕአዴግ ተሐድሶ፣ ጥልቅ ተሐድሶ ምንንትስ እያለ ሕዝብን ለማሞኘት የመዘዛቸው ካርዶቹ ስላለቁበትና ሲጨንቀው ለውጥ!” የሚል ድራማ አምጥቶ ለድራማውም ዕኩይ ገጸ ባሕርይና መልካም ገጸባሕርይ ተዋንያንን በመምረጥ ለመልካም ገጸ ባሕርይ የለውጥ ኃይል፣ ለዕኩይ ገጸባሕርይ ደግሞ ለውጥ አደናቃፊ የሚል ሥያሜ ሰጥቶ በደንብ አግርጎ ሲተውንብን እነ አቶ መስፍን ወልደማርያምና መሰሎቻቸው የወያኔን ኩሊዎች ዐቢይ አሕመድንና የለውጥ ኃይል!” እያሉ ሲያደንቁት የነበረውን የወያኔ ምስለኔ ቡድን ከእግዚአብሔር የተላኩልን፣ ሙሴያችን፣ አሻጋሪያችን!” ምንንትስ እያሉ በባዶ ወሬ ብቻ ተደልለው እስከማምተክ ሲደርሱና የኢትዮጵያን ሕዝብ ሲያሳስቱ በዚህ የድንቁርና ተግባራቸው እየተበሳጨሁ ስድብና ዘለፋ ሳይቀር እያዘነብኩባቸው ተው በኋላ ማጣፊያው ያጥራቹሃል! የኢትዮጵያን ሕዝብ እያሳሳታቹህ ነው እንዲህ ብሎ ለውጥ የለም ድራማ ነው እየተወኑብን ያሉት ተው አትጃጃሉ….!” እያልኩ ስለፈልፍ አልሰማ ብለው በሚጣፍጠው የቀን ቅዠት ሲቃዡ ከርመው ዛሬ ሕውሓትን የቀን ጅብ ብሎ ሲሳደብ የነበረ የተራበ ጅብ ሁኖ ማየት ያሳፍራል!” ብለውን አረፉት!!!

እነ ኩሊ ዐቢይስ የቀን ጅቡ የወያኔ ታዛዥ ኩሊ ሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከእነዚህስ ወያኔ ይሻለናል!” እንዲል የማድረግ የቤት ሥራ ከወያኔ ተሰጥቷቸው የኩሊነታቸውን ሥራ የሚሠሩ ታዛዥ የወያኔ ባሮች ናቸው እንጅ ዘገምተኞቹ እንደሚሉት ሥልጣን በእጃቸው ያለና አራጊ ፈጣሪዎች ሆነውስ አይደለም!!!

ኦሕዴድ ለኦሮሞ ሕዝብ አሳቢ ቢሆን ወይም የኦሮሞ ሕዝብ ታጋይ ቢሆንና ሥልጣንም በእጁ ያለ ቢሆን መሰንበቻውን እንዳደረገው ለማሳበቢያ እንዲሆነው ሀጫሉን ከገደለ በኋላ ቄሮን ከቦታ ወደቦታ በጭነት መኪኖች ጭኖ እያዘዋወረ ከጸጥታ አካላቱ ጋር አቀናጅቶ በማሠማራት የስም ዝርዝር ሰጥቶ ከሻሸመኔ እስከ ሐረርና ድሬዳዋ ድረስ በብዙ ከተሞች በፈጸማቸው ትላልቅ ኢንቨስትመንቶችን ጨምሮ የባለሀብቶችን ንብረቶች የማውደምና የዜጎችንም ነፍስ በአሰቃቂ ሁኔታ የማጥፋት እጅግ አስደንጋጭ ጥፋት በመፈጸም ኢንቨስትመንት የሚባል ነገር ክልላችን ከሚሉት የሀገሪቱ ክፍል እንዲሸሽ፣ ሌላም አዳዲስ ኢንቨስትመንት ትውር እንዳይል፣ ኦሮሞ በጭራቅነትና በደንቆሮ ሕዝብነት እንዲታይ እንዲቆጠር አያደርግም አይሠራም ነበር፡፡ በምንም መልኩ ቢታሰብ በዚህ አረመኔያዊና የድንቁርና ተግባር የኦሮሞ ሕዝብ ተጠቃሚ ሊሆን አይችልም፡፡ ተጠቃሚ ሊሆን በማይችልበት ጉዳይ ደግሞ ለኦሮሞ የሚታገልና ለኦሮሞ የሚያስብ ድርጅት ሊሠራ አይችልም!!!

እንዲህ እያደረገ በኦሮሞ ላይ እየተጫወተ ያለው ፍጹም ታማኙ የወያኔ ባሪያ ኦሕዴድ ኦሮሞን ተረኝነት እንዲሰማውና ባለጊዜ የሆነ እንዲመስለው ማድረግ ሲፈልግ ደግሞ መሰንበቻውን ስናየው እንደነበረው የአዲስ አበባ ሕዝብ ለዓመታት አልበላም አልጠጣም!” ብሎ ቆጥቦ የገነባቸውን የኮንደሚኒየም ቤቶችንና የአዲስ አበባን መሬት ለካድሬዎቹ በማደልና በማስወረር፣ ሕገወጥ በሆነ መንገድ የአዲስ አበባን የነዋሪነት መታወቂያ በማደል፣ በከተማ አሥተዳደሩም ኦሮሞ ካድሬዎችን ብቻ በመቅጠር ወዘተረፈ. እያደረገ ውስጡን የማያውቀውን የኦሮሞን ሕዝብ ያጃጅላል!!!

እናም ኦሕዴድ ፈጽሞ ለኦሮሞ ሕዝብ የሚሠራና የሚታገል ድርጅት አይደለም፡፡ እንደ ብአዴን ሁሉ ወያኔን ተግቶ እያገለገለ ያለ፣ ለወያኔ ጥቅም እየፈጋ ያለ የወያኔ ባሪያ ወይም አሻንጉሊት ድርጅት ነው፡፡ ባጭሩ ኦሕዴድ በአሁኑ ሰዓት እያደረገ ያለው ኦሮሞን የወያኔ ዱላ አድርጎ ክልላችን ነው!” በሚሉት ያለውን አማራን፣ ጉራጌን…. በመቀጥቀጥና አረመኔያዊ ግፍ በማስፈጸም በኦሮሞ ኪሳራ ሰይጣናዊ የወያኔን ጥቅም የማስጠበቅ ተልእኮ ተሰጥቶት ያንን ለማስፈጸም እየፈጋ ያለ ፍጹም ታማኝ የወያኔ አህያ ወይም ባሪያ ድርጅት ነው ኦሕዴድ ማለት!!!

በቃ ልክ ፀረ አማራውን ብአዴንን ዓይታቹህ ኦሕዴድን እዩት፡፡ ቅንጣት ታክል ልዩነት የላቸውም ሁለቱም አንድ ናቸው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ሁለቱም ከኋላ የሚዘወሩትና የሚታዘዙት በወያኔ ነው፡፡ ሁሉም የምታዩት ነገር ሁሉ ድራማ ነው፡፡ ድራማው ብዙ ስለማይቆይ መጨረሻ ላይ ሁሉንም ትረዱታላቹህ፡፡ የተታለላቹህ ሰዎች ጭንቅላታቹህ ማገናዘብና መመርመር ስለማይችል፣ ከተጨባጩ እውነታ ጋር ፈጽሞ ባልተገናዘበ ሁኔታ ለመልካም ምኞታቹህ በጣም ጉጉና ተላላ ስለሆናቹህ ነው እንጅ ይሄንን መረዳት ከባድ ሆኖ አልነበረም!!!

ኦሕዴድ ማለት ይሄ እንጅ እነ አቶ መስፍን ወ/ማርያም እንደሚመስላቸው ሥልጣን በእጁ ያለና አራጊ ፈጣሪ ሆኖ የቀን ጅቡን ወያኔን አባሮ ወደ የተራበ ጅብነት የተለወጠ ተረኛ ጅብ አይደለም፡፡ ከተራው ሰው በተለየና በላቀ መልኩ ማሰብ፣ ማገናዘብ፣ መመርመር፣ መረዳት፣ መገንዘብ፣ ማስተዋል የሚጠበቅባቸው የተማርኩ፣ የተመራመርኩ፣ የጠነቀኩ ነኝ!” የሚሉ ወገኖች በዚህ ደረጃ በተራ ምናምንቴዎች ተታለው ሲያፍሩና እንዲህ ሲዋረዱ ማየት እንዴት ያሳፍራል ወገኖቸ???

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው