ጣልያን ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት ከፍተኛ ተጋድሎ ያደረጉ ሴት የነፃነት ታጋዮችን በሚዘክረው ዘ ሻዶው ኪንግመፅሃፏ ኢትዮጵያዊአሜሪካዊቷ ደራሲ መዓዛ መንግስቴ ለቡከር ሽልማት እጩዎች መካከል አንዷ ሆናለች።

20 መስከረም 2020, 10:21 EAT

ለነፃነት በተደረገው ትግል ላይ የጥቂት ወንዶች ሚና በጎላበት ሁኔታ ሴት ነፃነት ታጋዮች ከታሪክ መዝገብ መፋቃቸውንና ግዙፍ አስተዋፅኦቸው ምን ይመስል ነበር በማለት አስርት አመታትን ወደ ኋላ ተጉዛም መዓዛ በዘ ሻዶው ኪንግታስቃኛለች።

የፅሁፍ ስራው ግን ቀላል አልነበረም፤ መዓዛ እንደምትለው ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታዎች የተደራረቡበት ሁኔታም ነበር።

ጣልያንኛ መማር ነበረባት እንዲሁም የመጀመሪያ ረቂቅ ፅሁፉን ለማጠናቀቀም አሰልቺና አድካሚ የሚባሉ አምስት አመታት ፈጅተውባታል።

በመሰላቸት ፅሁፉን ጥላው እንደነበርም ለቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ ሬድዮ ፕሮግራም ተናግራለች።

በጣም ፈታኝና ከፃፍኩዋቸው ሁሉ መጥፎ የምለው ነው። እስርስር አድርጎኝ ነበር፤ የሞራል ውድቅትም ደርሶብኝ ነበር። የመጀመሪያ ረቂቄንም ጥዬ እንደገና ከዜሮ ጀምሬያለሁብላለች።

መፅሃፏንም ፅፋ ለማጠናቀቅ አስር አመት ወስዶባታል።

ስለ ፅሁፍ ስታወራም የፅሁፍ ስራ በደንብ ውስጥን መመልከትና መነሳሳትን ይጠይቃል። አንዳንዴ ወንበሬ ላይ ተቀምጬ መፃፍም ከፍተኛ ትግል ነበረው። ከመፅሃፌም ጋር አብሬ አድጌያለሁ። ለዚህ ሽልማትም ዕጩ በመሆኔ የተሰማኝ ፍፁም ደስታ ነውትላለች።

መጽሐፉ መቼቱን ያደረገው የሁለተኛው አለም ጦርነት ጅማሮ የሚባለውና ፋሽስት ጣልያን ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት ነው።

ስለ ጣልያኖች በተለምዶ የሚባሉ ነገሮችን ማካተት አልፈለፈግኩም፤ ስለዚህ ጣልያንኛ ተማርኩ። ጣልያኖችን አዋርቻለሁ። የወታደሮቹን ልጅና ልጅ ልጆችም እንዲሁ። በጦርነቱ ወቅት የመዘገቧቸውን ሁኔታዎች፣ ደብዳቤዎችና የግል መረጃዎችም በራሴ ፈትሻለሁትላለች መዓዛ

የቋንቋ ችሎታዬም ሲዳብር፣ ገፀ ባህርያቶቼም እየተወሳሰቡ መጡበማለትም ታስረዳለች።

በዩናይትድ ኪንግደም የፅሁፍ ዘርፍ ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጠው የቡከር ሽልማት በእንግሊዝኛ ለተፃፉ ድርሰቶች ሽልማትን ይሰጣል።

በዩናይትድ ኪንግደም፣ አየርላንድ ለታተሙ ወይም ዬየትኛውም አገር ዜጎች ፅሁፋቸው በእንግሊዝኛ ቋንቋ ለሆኑ ነው።

ከመዓዛ መንግሥቴ በተጨማሪ የዚምባብዌዋ ፂፂ ዳንጋሬምባም ሞርነብል ቦዲበሚለው ድርሰቷ እጩ ሆናለች።

አሸናፊዎቹም ህዳር መጀመሪያው ሳምንት ላይ ለህዝብ ይፋ ይሆናሉ።

ቢቢሲ