ኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ /ኢሕአፓ / በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልላዊ መንግስት በተደጋጋሚ የሚፈፀመው ብሔር ተኮር የዘር ማጥፋት ወንጀል ባስቸኳይ እንዲቆም ና የህግ የበላይነት እንዲከበር በአፅንኦት ይጠይቃል።
ከዚህ በፊት ባወጣቸው አቋሙቹ እንደ ገለፀዉ የክልሉ ልዩ ሀይል አባላት በገለልተኝነት ሰላም ለማስከበር ከመጣር ይልቅ ለታጣቂ ቡድኖች መረጃ አሳልፎ በመስጠት የክህደት ና የስነምግባር ጉድለት እየታየባቸው መሆኑን ከተለያዩ ምንጮች አረጋግጠናል ፤ስለዚህ ታጣቂ አሸባሪዎች የንፁሃን ዜጎችን ደም አፍስሰው በቀላሉ እንዲሰወሩ የሚያግዙ የልዩ ሀይል አባላት ተገልለው ፀጥታ የማስከበር ተግባሩን የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት በተናጠል እንዲፈፀም እንጠየቃለን።
ኢሕአፓ በእንዲህ አይነት እጅግ ዘግናኝ የዘር ጭፍጨፋ /በተለይም በአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች / ድርጊት ህይወታቸውን ላጡ ፣ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ፣ሀብትና ንብረታቸው ለወደመባቸው ዜጎች የተሰማዉን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ፣የፌዴራል ና የክልሉ መንግስት በጥምረት ለተጎጂዎች ተገቢ ካሳ በመክፈል ወደ ነበሩት ቀዬ የመመለስ ና መልሶ የማቋቋም ተግባራት በፍጥነት እንዲፈፀሙ ና በዚህ የወንጀል ድርጊት የተሳተፉ ተጠርጣሪዎችን አድኖ በመያዝ በሕግ ፊት ተጠያቂ እንዲያደርጉ ኢሕአፓ በአፅንኦት ያሳስባል።
በመጨረሻም በሀገራችን ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ለሚከሰቱ ብሔርና ሐይማኖት ተኮር ግጭቶች ና የዘር ማጥፋት ወንጀሎች መቀፍቀፊያ የሆነው ቋንቋን ማዕከል ያደረገው የፌደራሊዝም ስርአት ና ለዚህ እዉቅና የሚሰጠው ሕገመንግሥት ተብዬው ሕገ ህወሃት ስለሆነ በጥናት ላይ የተመሰረተ ማሻሻያ እንዲካሄድ ሁልጊዜም ጥያቂያችንን በሰላማዊ መንገድ ለኢትዮጵያ ህልውና ስንል ዘወትር እናቀርባለን!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ
