
ፕሮፌስር በየነ ጴጥሮስ
የፓርላማ አባል በመሆናቸው የሚገባቸባውን ደሞዝ እንዲወስዱ ሲጠየቁ “የዩንቨርሲቲ መምህር በመሆኔ የሚከፈለኝ ደሞዝ አለኝ፥ሁለቱም ከመንግስት ኪስ የሚወጡ ናቸው” በማለት እምቢኝ ያሉ ምሁር ናቸው።
በሚንስተር ማዕረግ የሚገባቸውን ጥቅማጥቅም “ቤት ስላለኝ ተጨማሪ ቤት አያስፈልገኝም” በማለት እምቢኝ ያሉ ምሁር ናቸው።
ለመቃወም ብቻ የማይቃወሙ ምሁር ናቸው።
አበል ለመብላት ሲሉ ብቻ ስብሰባ የሚያዘጋጁ ባለስልጣናት በሞሉባት አገር፣የራሳቸውን ቤት አከራይተው በመንግስት ቤት የሚኖሩ ባለስልጣናት በሞሉባት አገር፣በሞተ ሰው ስም ደሞዝ ደርበው የሚበሉ ባለስልጣናት በበዙበት አገር፣የገዛ አገራቸውን እየሰረቁ የሰው አገር የሚያለሙ ባለስልጣናት በበዙባት አገር….ፕ/ር #በየነ_ጴጥሮስን አለማድነቅ ንፉግነት ነው።
ከፌስ ቡክ የተገኝ
