September 24, 2020 – Konjit Sitotaw
የኢሰመኮ ጋዜጣዊ መግለጫ
************************
የፍርድ ቤት ውሳኔ አለመከበር ለሰብዓዊ መብቶች መከበር አደጋ ነው!********************************************************
አላስፈላጊ እስር ማስቀረትና የዋስትና መብት ማክበር ያስፈልጋል!***************************************************

(አዲስ አበባ፤ መስከረም 14 ቀን 2013 ዓ.ም.) የምሥራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቶ ልደቱ አያሌው በአንድ መቶ ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲወጡ መስከረም 12 ቀን 2013 ዓ.ም. ትዕዛዝ የሰጠ ቢሆንም፤ እስካሁን ድረስ አለመፈታታቸውን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የሚከተለውን ብለዋል ፡፡
–
‹‹የሰብዓዊ መብቶች መከበር ዋና ዋስትናው የፍርድ ቤት ውሳኔ መከበር በመሆኑ፤ አቶ ልደቱ አያሌውን ጨምሮ በፍርድ ቤት የዋስትና መብት ተፈቅዶላቸውና የዋሰትና ሁኔታውን አሟልተው ከእስር እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የሰጠላቸው ታሳሪዎች በሙሉ በአስቸኳይ እና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከእስር ሊፈቱ ይገባል››
