September 28, 2020 – Konjit Sitotaw
ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቦርድ አመራር አባሉ የሆኑት ጌታሁን ካሳ ዛሬ በገዛ ፍቃዳቸው ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መልቀቂያ እንዳስገቡ በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል። ጌታሁን ከዐመት በፊት ከተሾሙት 5ቱ አዳዲስ የቦርዱ አባላት አንዱ ናቸው። እኝሁ የቦርዱ አባል በገዛ ፍቃዳቸው መልቀቂያ ያስገቡበትን ምክንያት ግን ቦርዱ ከመግለጽ ተቆጥቧል።
National Election Board of Ethiopia- NEBE
@NEBEthiopia
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቦርድ አመራር አባል የሆኑት ዶክተር ጌታሁን ካሳ በዛሬው እለት በገዛ ፈቃዳቸው ሃላፊነታቸውን መልቀቃቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ ለኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማስገባታቸውን እናሳውቃለን::
11:45 AM · Sep 28, 2020 ·Twitter Web App
23 Retweets 17 Quote Tweets 77 Likes
ዶ/ር ጌታሁንን የኢትዮጵያ ቼክ በስልክ አግኝተን በጉዳዩ ዙርያ ጠይቀናቸዋል። ሲመልሱም “ትክክል ነው፣ መልቀቂያዬን ዛሬ አስገብቻለሁ። ብዙ ምክንያቶች አሉኝ፣ አሁን ግን ልገልፃቸው አልፈልግም” ብለው መረጃው ትክክል መሆኑን አረጋግጠውልናል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የቦርድ አባል የሆኑት ዶ/ር ጌታሁን ካሳ ከአባልነታቸው ራሳቸውን አግለዋል?
ይህ መረጃ ዛሬ በስፋት እየተሰራጨ ስለነበር በርካታ የኢትዮጵያ ቼክ አንባቢዎች እንድናጣራላችሁ ጥያቄ እየላካችሁልን ነበር።

