ሰሞንኛ የአገዛዙ አሳሳች ወይም አጃጃይ እርምጃ!!!

አገዛዙ ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በሚለው የሀገራችን ክፍል ለተፈጸመው የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ከክልል እስከ ወረዳ እጃቸው አለበት፣ ኃላፊነታቸውን አልተወጡም!” የተባሉ 45 የጸጥታውና የአሥተዳደር ኃላፊዎችን ከኃላፊነታቸው መነሣታቸውን የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የሚሉት የአገዛዙ አሥተዳደርን ጠቅሰው የአገዛዙ የብዙኃን መገናኛዎች ገልጸዋል!!!

ይሄንን አሳሳች ወይም አጃጃይ የማስመሰያ እርምጃም ከቅጥረኛው የአብን አመራሮች ጀምሮ እስከ የብአዴን ቅጥረኛ አንቂዎች በአድናቆት እያራገቡ አማራን ለማጃጃል ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ!!!

ይሄ ዓይነት የአገዛዙ የማጃጃያ እርምጃ ግን አዲስ አይደለም፡፡ ባይገርማቹህ ያውም ከስድስት ዓመታት በፊትም በዚሁ የቤንሻንጉል ጉምዝ በሚለው አገዛዙ የልቡን ይሠራና ሲያበቃ በአማራ ላይ ለተፈጸመ ጭፍጨፋ ተጠያቂ ናቸው!” ብሎ የካቢኔ አባላት ሳይቀሩ በርካታ አመራሮች ከኃላፊነት መነሣት ብቻ ሳይሆን ታስረው ሕግ ፊትም እንዲቀርቡ አድርጎ ነበረ፡፡ በዚያው ሰሞን ብቻ ለማስመሰል ይሄንን ካደረገና ካረሳሳ በኋላ ግን እነኙሁን ሰዎች መልሶ ከነበሩበት ወረዳና ዞን ወደሌላ ሾማቸው እንጅ ከኃላፊነትም ተነሥተው አልቀሩም፣ የሚገባቸውን የእስራት ፍርድም እንዲፈረድባቸውም አልተደረገም ነበር!!!

ዘገምተኛው መንጋ ግን ያ የወያኔ ኩሊ ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሚሞሪው አጭር ነው!” እንዳለው ሁሉ የማስታወስ ችሎታው አጭር ስለሆነ ያለፈውን ይረሳል፡፡ አንዴ በተታለለበት ዘዴ ሁለቴና ሦስቴ ብቻ አይደለም ሽህ ጊዜ ደጋግሞ ይታለላል፡፡ አገዛዙ ይሄንን ስለሚያውቅ ትናንት ያታለለበትን ዘዴ እየደጋገመ ሲያመጣው ይነቃብኛል!” ብሎ ትንሽ እንኳ አይሳቀቅም!!!

ይሄ የማታለያ ዘዴ በዚህ አገዛዝ የተለመደና ይሁነኝ!” ተብሎ የተያዘ ዘዴ መሆኑ በደንብ የሚታወቅ ነው፡፡ የሀጫሉን ግድያ ተከትሎ አገዛዙ ኦሮሚያ በሚለው የሀገራችን ክፍል ለተፈጸመው የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ እጃቸው እንዳለበት ታውቆ ታስረው የነበሩ የአገዛዙ የሥራ ኃላፊዎችን፣ ፖሊሶችንና ጥቃቱን የፈጸሙ ቄሮዎችን አገዛዙ በቁጥጥር ስር አድርጎ ከሰነባበተ በኋላ እነ እከሌ ናቸው የጠቆሙባቹህ!” እያለ ፈትቶ ጭራሽ እንዲያውም በዚህ ሰሞን ከግድያ የተረፉ ሰለባ ወገኖቻችንን አንተ ነህ የጠቆምክብኝ፣ አንች ነሽ የጠቆምሽብኝ!” እያሉ ሀገር ለቀው እንዲወጡ ካልሆነ ግን እንደሚገሏቸው እያስፈራሯቸው መሆኑን የኢሳት አዲስ አበባ ዜና በቀደምለት ዘግቧል፡፡ ስለሆነም ዘገምተኛው መንጋ ከኃላፊነት ተነሡ!” በሚለው ዜና ባትጃጃልና ብትነቃ ይሻልሀል!!!

ሌላኛው የሰሞኑ ማጃጃያ ወይም ማስመሰያ ደግሞ አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና አቶ አገኘሁ ተሻገር ከሁለት ዓመት በፊት አቶ ደመቀ መኮንን በባሕርዳር ስታዲየም የወሸከተውን የማጃጃያ ቃል በመድገም ከአሁን በኋላ ግን!” እያሉ ዘራፍ ለአማራ!” ፉከራ ማሰማታቸው ነው፡፡ ይሄም ዘገምተኛውን መንጋ በሰፊው እያጃጃለው እንደሆነ እያየሁ ነው!!!

ሲጀመር እነኝህ ባለሥልጣናትም ሆኑ ፓርቲያቸው ዛሬም ሆነ በሠላሳ ዓመት የአገዛዝ ዘመናቸው መቸ አማራ በአማራነቱ ተለይቶ ተጠቅቷል!” ወይም በአማራ ላይ እየተፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ መቸ ያምናሉና ነው ፀረ አማራው ብአዴን በሰሞኑ ጭፍጨፋ የተፈጠረበትን ጥላቻ ለመግፈፍና አማራን ለማጃጃል ሲል ዘራፍ!” ያለውን የውሸት ፉከራ ዘገምተኛው መንጋ እውነት መስሎህ እሰይ እንደሱ ነው እንጅ!” እያልክ የምትጃጃለው??? እንኳንና በአማራ ላይ የዘር ማጥፋት ጥቃት ወይም ጭፍጨፋ ተፈጽሟል!” ብለው የማያምኑትንና ተፈጽሟል!” ቢሉ እንኳ አማራን ከማጃጃያነት ባለፈ ተጠያቂዎችን በሙሉ በዚህ ወንጀል ተጠያቂ አድርገው አማራ ፍትሕ እንዲያገኝ ለማድረግ እንዳልሆነ መታወቅ አለበት፡፡ ምክንያቱም ለጌቶቻቸው ለትግሬ/ወያኔ ብለው ይሄንን የዘር ማጥፋት ጥቃት ከእነሱ በላይ በአማራ ላይ የፈጸመ የለምና ነው!!!

አንዳንድ ምሁራን ነን፣ ተንታኝ ነን፣ ፖለቲከኛ ነን!” የሚሉ ግልብ ግለሰቦች በተለያዩ የውይይት መድረኮች ላይ ብአዴንም ሆነ አጠቃላይ አገዛዙ እየተፈጸመ ያለውን ግልጽ የዘር ማጥፋት ጥቃት ወይም ጭፍጨፋ የዘር ማጥፋት ጥቃት ነው!’ ብሎ ማመን የማይፈልገው የዘር ማጥፋት ጥቃት ከባድ ዓለም አቀፋዊ ወንጀል በመሆኑ ተጠያቂነት እንዳይከተለው ወይም እንዳይመጣበት ስለሚፈራ ነው የዘር ማጥፋት ጥቃቱን ማመን የማይፈልገው!” ሲሉ አደምጣለሁ!!!

ልብ በሉ ጥቃቱን ፈጻሚ ስለሆነ ነው!” አይደለም የሚሉት፡፡ ይሁንና ግን የሚጠቅሷቸው መረጃዎች በሙሉ የጥቃቱ ፈጻሚና አቀናባሪ አገዛዙ መሆኑን የሚያረጋግጡ ናቸው፡፡ መረጃዎቹ የሚያሳዩዋቸው ሀቅ ሌላ እነሱ የሚቀባጥሩት ደግሞ ሌላ ነው፡፡ አገዛዙ ለራሱ ያልተጨነቀበትንና ኧረ በዘር ማጥፋት ወንጀል እንዳልጠየቅ!” ብሎ ችግሩን ለመቅረፍ ጨርሶ ያልሞከረበትንና ያልፈራበትን ጉዳይ እነሱ ተጨንቀውለት እንዲህ ስለሆነ፣ እንዲያ ስለሆነ!” እያሉ ማምለጫ ምክንያት ያበጁለታል!!!

እነኝህ የዘር ማጥፋት ጥቃቶች በተፈጸሙ ቁጥር ግን አቶ ዐቢይ አሕመድ ለማስመሰልም እንኳ ቢሆን ሐዘኔን እገልጻለሁ!” ለማለት ባለመፍቀድ ይልቁንም የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋው በተፈጸሙባቸው ቀናት በሶሻል ሚዲያ አካውንቱ ላይ አንዴ ለካናዳ ጠ/እንኳን ደስ አለዎት!” በማለት፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ በቤሩቱ ፍንዳታ ሐዘኔን እገልጻለሁ!” በማለት፣ በሌላ ጊዜም የሚለው ቢያጣ እንኳ ትኩረት የማይሰጠውን የማይረባ ነገር በማለት፣ ሲለውም ደግሞ ሀጫሉን ነጥሎ ለይቶ ሐዘኔን እገልጻለሁ!” በማለት ያለ አበሳቸው አማራ ወይም ክርስቲያን በመሆናቸው ብቻ ከሕፃን እስከ ሽማግሌ ለተጨፈጨፉ ንጹሐን ወገኖቻችን ግን ለሚረባውም ለማይረባውም ሲከፍተው የሚውለውን አፉን ሐዘኔን እገልጻለሁ!” ባለማለት ሕዝቡ አቶ ዐቢይ አሕመድ እኮ እኛን ለማጽናናት የማይፈልገውና ጥቃቱ በሚፈጸሙብን ቀናት እየወጣ ሌላ ነገር የሚናገረው ከምንም እንደማልቆጥራቹህና ትኩረት እንደማልሰጣቹህ እወቁት!’ ማለቱ እኮነው!” ብሎ እንዲያስብና ሕዝባችንን በተፈጸመበት የዘር ማጥፋት ጥቃት ላይ ተጨማሪ የሥነልቡና ጥቃት በማድረስ ለማብሸቅ፣ ለማብገንና ለማሳረር መጣሩ በተጨማሪም በአማራና ክርስቲያን በሆኑ የሌሎች ብሔረሰብ አባላትም የሚፈጸመውን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ለማስተባበል የደነቆረ የማስተባበያ ምክንያት በመስጠት በተደጋጋሚ ጥረት ማድረጉ ሁሉ እጁ እንዳለበት እየጠቆመ፤ በተለይም ደግሞ በጭፍጨፋው ላይ የአገዛዙ መዋቅር ከጸጥታው እስከ አሥተዳደሩ ተሳታፊ ሆኖ እየታየና በመረጃ በሚገባ የተረጋገጠ ጉዳይ ሆኖ እያለ አገዛዙን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ማመን የማይፈልገው ተጠያቂነት እንዳይመጣበት ስለሚፈራ ነው!” የሚሉ ምሁራን ነን ባይ ዘገምተኞችን ምን ትሏቸዋላቹህ??? አገዛዙ ተጠያቂነት እንዲመጣበት ቢፈራ ነው ወይ ከፍተኛ ንቀት፣ እብሪትና ማን አለብኝነት በተሞላበት በዚህ መልኩ ይሄንን ሁሉ እያደረገ ያለው???

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው