29/09/2020 

እስክንድር ነጋ በፍርድ ቤት የተናገረው !

ይድነቃቸው ከበደ

* የእነ እስክንድር ነጋ የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደርጓል!

” ጊዜው የምርጫ አመት ነው ።በምርጫ መሳተፍ እንፈልጋለን ፤ ጉዳያችን እረጅም ጊዜ

ሳይፈጅ በአጭሩ እንዲያልቅ ፍ/ቤቱን እጠይቃለሁ ።

” ከዚህ ልቦለድ ክስ ነፃ እንደምንወጣ ጥርጥር የለኝም። የሚጠብቀን ህዝብ አለ፤ በሕዝብ መመዘን እንፈልጋለን ።”

ያለ ሲሆን ፤ ከዚህ ቀደም ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቶ አልተፈጸመም ያለውን አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን ፦

” ባለቤት እና ልጄ ውጪ ሃገር ስለሚገኙ በስልክ እዳናግራቸው ይህ ፍርድ ቤት ለማረሚያ ቤት ትዕዛዝ የሰጠ ቢሆንም ፤ ማረሚያ ቤቱ ይህን ትዕዛዝ አልፈጸመም ። አሁንም ቤተሰቤን እንዳገኘ ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ይስጥልኝ ” በማለት አቤቱታ አቅርቧል ።

የእነ እስክንድር ነጋ የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደርጓል!ዛሬ መስከረም 19 /2013 እነ እስክንድር ስንታየሁ፣ አስቴር እና አስካል  ከፍተኛው  ፍርድ ቤት የጠዋት ችሎት ይቀርባሉ። ቀጠሮው ፣  ዐቃቤ ህግ በተከሳሾች ላይ ያቀረበውን ክስ አሻሽሎ እንዲያቀርብ ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ በመስጠቱ ነው እና በዋስትና ጥያቄያቸው ላይ ውሳኔ ለመስጠት ሲሆን ለእነ እስክንድር ዋስትናውን ውድቅ አድርጎታል።