October 2, 2020 – Konjit Sitotaw
በኢትዮጵያ በዜጎች ላይ የተደቀነውን የደኅንነት ስጋት እና የፖለቲካ ምኅዳሩን መጥበብ በቅርበት እየተከታተሉ መሆናቸውን ለአሜሪካው ፕሬዝዳንታዊ ዕጩ ጆ ባይደን የውጭ ፖሊሲ አማካሪ የሆኑት አንቶኒ ብሊንከን በትዊተር ገጻቸው አስፍረው ተመልክተናል።

We are closely watching developments in Ethiopia with concern for the security of all its citizens and the closing of civic space. Leaders across the political spectrum should prioritize dialogue over violence and repression to preserve the promise of a transition to democracy.
662 318 people are Tweeting about this
የሀገሪቱ ዲሞክራሲያዊ ሽግግር እንዲሰምር፣ ሁሉም የፖለቲካ ሃይሎች ከአፈና እና ሁከት በፊት መነጋገርን ማስቀደም አለባቸው- ብለዋል አማካሪው። ብሊንከን በቀድሞው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ሥልጣን ዘመን ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚንስትር የነበሩ ናቸው።
