ሰይጣን አገልጋዮቹን ማኅበረ ቅዱሳንን ተጠቅሞ ቤተክርስቲያንን ጉድ ከሠራት ሥራዎቹ አንዱን ነው ለዛሬ የምነግራቹህ!!!

ጥራዝ ነጠቆቹና ደፋሮቹ የሰይጣን አገልጋዮች ማኅበረ ቅዱሳን የቤተክርስቲያንን ቅዱሳት መጻሕፍት ወደ ኦሮምኛ በመተርጎም ያለ ቤተክርስቲያን ፈቃድ በራሱ ፍላጎት አገዛዙ ኦሮሚያ በሚለው የሀገራችን ክፍል በየቤተክርስቲያኑ ከውዳሴ ማርያም እስከ ቅዳሴው ድረስ በኦሮምኛ እንዲገለገል ሲያደርግ መቆየቱን ታውቃላቹህ!!!

እናም ይሄው ማኅበር በቴሌቪዥን ስርጭታቸው ከሚያስተላልፏቸው የኦሮምኛ ዝግጅቶች እንደተረዳቹህት ቅዳሴውን፣ ውዳሴ ማርያሙን፣ መዝሙራቱን፣ ቅዱሳት መጻሕፍቱን ወዘተረፈ. ወደ ኦሮምኛ ሲተረጉሙም እግዚአብሔር የሚለውን ቃል ምን ወደሚል ቃል ተረጎሙት መሰላቹህ ዋቃ ወደሚል ቃል ተርጉመው ነው አገልግሎቱ እንዲሰጥ ሲያደርጉ የቆዩት!!!

ልብ በሉ ዋቃ ማለት ዋቄፈና ወይም ዋቄፈታ በሚባለው ባዕድ አምልኮ የሚመለክ የሰይጣን ወይም የባዕድ አምላክ ስም ነው፡፡ ጥቁር እንደሆነም ያምናሉ፡፡ በዚህ የባዕድ አምልኮ እምነት ዋቃ የሚባለው ጥቁር ባዕድ አምላክ ጽድቅና ኩነኔ፣ ገነትና ሲዖል፣ ቅዱሳት መላእክትና እርኩሳት መላእክት ወይም ሰይጣን የሚባሉ ነገሮች አይታወቁም ወይም የሉም!!!

እንግዲህ የእግዚአብሔርንና የዋቃን ልዩነት ልብ በሉ፡፡ በዚህ ባዕድ አምልኳቸው ላይ ጥናት ያደረጉ እንደ ዶ/ር ገመቹ ያሉ ምሁራኖቻቸውእንደሚሉት የዚህ ባዕድ አምልኮ ንዋየ ቅድሳት የወንድ ጾታ ያላቸው የእምነቱ ተከታዮች ወንድ የሰለቡ መሆናቸውን ለማመልከት ከግንባራቸው ላይ የሚያስሩት ከለቻ የሚሉት በወንድ ብልት ቅርጽ የሚሠራው ጌጥ፣ በዚህ ባዕድ አምልኮ የሴት አምላክ የሆነችው አቴቴ የምትለመንበትና ሴቶቹ በበዓላቸው ዕለት ከአንገታቸው፣ ከራሳቸው፣ ከትክሻቸውና ከእጃቸው ላይ የሚያደርጉት ጥቁር ቀይና ነጭ ቀለም ያለው ከበዓሉ በኋላ በሙዳይ የሚያስቀምጡት ጨሌ፣ ሲንቄ የሚባለው በትርና የመሳሰሉት ናቸው!!!

ይሄ ሰይጣናዊው ባዕድ አምልኮ ዋቃ ለተባለው ጥቁር ባዕድ አምላክ እንደ ጥቁር በግ፣ ጥቁር ዶሮ፣ አረቂና ቅቤ የመሳሰሉ መሥዋዕትንና ምስጋናን የማቅረቢያ ኢሬቻ የሚባል በዓልም አለው፡፡ አያና የሚባለውን የዋቃን መንፈስ እየጠሩ ሥርዓቱን የሚያስፈጽሙትም ቃሉ ወይም ቃልቻና ባለውቃቤ የሚባሉ ካህናተ ባዕድ አምልኮም አለው፡፡ የእግዚአብሔርም ቃል ግን እንዲህ ይላል አሕዛብ የሚሠውት ለአጋንንት እንዲሆን እንጅ ለእግዚአብሔር እንዳይሠው እላለሁ፡፡ ከአጋንንትም ጋር ማኅበርተኞች እንድትሆኑ አልወድም፡፡ የጌታን ጽዋና የአጋንንትን ጽዋ ልትጠጡ አትችሉም፡፡ ከጌታ ማዕድና ከአጋንንት ማዕድ ልትካፈሉ አትችሉም!” 1. ቆሮ. 1020-22

ታዲያ እግዚአብሔርና ዋቃ ጨርሶ የማይገናኙና የተለያዩ ከሆኑ፣ የዋቄፈታው ዋቃ ማለት እግዚአብሔር ማለት ካልሆነና ሊሆንም የማይችል ከሆነ ጥራዝ ነጠቁ ማኅበረ ቅዱሳን ቤተክርስቲያን አውቃ የተወችውን ነገር በራሱ ፈቃድ ተነሣስቶ ያለ ቤተክርስቲያን ፈቃድ ቅዱሳት መጻሕፍቶቿን በሙሉ እግዚአብሔርን ዋቃ በማለት በእግዚአብሔር መቅደስ ውስጥ በቅዳሴውም ሆነ በሌላው አገልግሎት የሰይጣናዊውን ባዕድ አምላክ ስም ዋቃ ዋቃ እያስባለ የባዕድ አምላክን ወይም የሰይጣን ስም እያስጠራ ባዕድ አምላክን እንዴት ሊያከብር፣ ሊያወድስ፣ ሊያመሰግን፣ ሊያገለግል ቻለ??? ብላቹህ ከጠየቃቹህ መልሱ ማኅበሩ ሰይጣን ያደረበትና የሚገለገልበት ማኅበር ስለሆነ ነው መልሱ ሌላ አይደለም!!!

ማኅበሩን የመሠረቱት ደገኛው አባት አቡነ ጎርጎርዮስ ቢሆኑም በመልካም ዘር ላይ እንክርዳድን የሚዘራው ሰይጣን ልጆቹን አብሮ በማስገባቱና እነሱ በማሸነፋቸው ይሄው ማኅበሩ እንዲህ የሚያደርግ ሊሆን ችሏል!!!

የማኅበረ ቅዱሳን ጉድ በዚህ አያበቃም፡፡ በአቡነ ጎርጎርዮስ ስም የሚጠሩ ትምህርት ቤቶችን ከፍቶ በተማሪዎች ዩኒፎርም ሹራብ ላይ የዋቄፈታውን መለያ ቀለም ጥቁር ቀይና ነጭ ጥለት በማድረግ የእርኩስ መንፈስ አገልጋይነቱን በድጋሜ አስመስክሯል!!!

ብዙዎቻቹህ ምናልባት እነኝህን ቀለማት የማተብ ቀለማት አድርጋቹህ ስለምታስቡት ማኅበረ ቅዱሳንም እነኝህን ቀለማት የተጠቀመው ይሄንን ለማመልከት ይሆናል!” ትሉ ይሆናል፡፡ ነገር ግን የሚገርማቹህ የቀለሞቹ አደራደር ጥቁር ነጭና ቀይ እንኳን አይደለም ያደረጉት ልክ እንደ ዋቄፈናው ጥቁር ቀይና ነጭ ነው ያደረጉት፡፡ ይሄ ሆን ተብሎ መደረጉን ያመለክታል፡፡ ሲጀመር ጥቁር ቀይና ነጭ ቀለማት የማተብ ቀለማት አይደሉም፡፡ በስሕተት ነው እየተገለገልንበት ያለነው፡፡ ለዝርዝሩ ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው ማንበብና መረዳት ይችላሉ!!!

https://www.ethiopanorama.com/?p=109553&lang=en

እናም በዚህ ማኅበር የተሰባሰቡ ሰዎች በሙሉ ማለት ባልችልም በአብዛኛው የማኅበሩ አባላት በተለይም ዋና ዋናዎቹ የአጋንንት መንፈስ ያደረባቸውና የሰይጣን አገልጋዮች ናቸው፡፡ እንዲህ ስላቹህ ሰዎቹ እራሳቸው የሰይጣን መንፈስ ያደረባቸው መሆናቸውንና ሰይጣንን የሚያገለግሉ መሆናቸውን ያውቃሉ ማለቴ አይደለም፡፡ በጣም ጥቂቶቹና የባሰባቸው ግን መንፈሱ በውስጣቸው ስለሚያስቸግራቸው ለራሳቸው በምሥጢር ቢይዙትም ሊያውቁ ይችላሉ፡፡ የተቀሩት ግን አያውቁም፡፡ በሚያደርጉት ሁሉ እግዚአብሔርን የሚያገለግሉ ነው የሚመስላቸው!!!

እንዲህ ዓይነቱ ሁኔታ የሚፈጠረው እንዴት መሰላቹህ ቤተሰቦቻቸው የቤት ጣጣ ወይም ባዕድ አምልኮ ያለባቸው ከሆኑ ከእንደዚህ ዓይነት ቤተሰብ የሚወለድ ልጅ ወላጆቹ በጨቅላነቱ በባዕድ አምልኮነት በሚያመልኩት የሰይጣን መንፈስ ያሸልሙታል፡፡ ይሄ ሰው ከዚያች ቅጽበት ጀምሮ እስኪሞት ድረስ ያ እርኩስ መንፈስ አድሮበት ይኖራል ማለት ነው፡፡ ሰብእናውንም ወይም ሰብእናዋንም እሱ በሚፈልገው መልኩ ቀርጾ የሚያሳድገው ወይም የሚያሳድጋት መንፈሱ ነው፡፡ ሰውየው ካደገ በኋላ መንፈሱ እንዳለበት አውቆ ከራሱ ለማስወጣት በብርቱ ጾም፣ ጸሎት፣ ስግደትና ጸበል በመጸበል ካልተጋና ጋልተጋደለና ካላስወጣው በስተቀር እስኪሞት ድረስ አይለቀውም!!!

ከዓመታት በፊት ዳንኤል ክብረት አባቱ መጥቁል መሆናቸውንና እሱንም በጨቅላነቱ የሚያመልኩትን እርኩስ መንፈስ እንዳዋረሱበት በዚህም ምክንያት የአውሬው አገልጋይ መሆኑን ነግሬያቹህ ነበረ፡፡ ልብ ብላቹህ ጸበል ቦታ ላይ ዓይታቹህ እንደሆነ አጋንንት የተጋለጠላቸው ዕድለኛ ጸበልተኞች ያደሩባቸው አጋንንት ሲለፈልፉ ብዙ ጊዜ ይሄንን ሲናገር ትሰሟቸዋላቹህ አሳድጌ አሳድጌ አልለቅም፣ ከጨቅላነቱ ጀምሮ ነው በወላጆቹ አደራ የተሰጠኝ/የተሰጠችኝ አብሬ እጠፋለሁ እንጅ አልለቅም!” እያለ ሲለፈልፍና ብዙ ሲያስቸግር ብዙ ሲያደክም የምትሰሙት ለዚህ ነው!!!

እንደዚህ ዓይነት ሰዎች መንፈሳዊ መስለው እስከ ክህነትም ደርሰው ከዚያም አልፈው እንዲያውም እስከ ጵጵስናም ደርሰው ሲያገለግሉ ሊገኙ ይችላሉ፡፡ አገልግሎታቸው ግን እግዚአብሔር የሚከብርበትና የሚቀበለው አይደለም፡፡ የሚገለገልባቸው ሰይጣን ነው፡፡ በንጽሕና በቅድስና ሥርዓቱና ቀኖናው በሚያዘው መልኩ አገልግሎታቸውን ስለማያቀርቡ ነው እግዚአብሔር የሚከብርበትና የሚቀበለው የማይሆነው፡፡ እንዲህ አድርገው እንዲያገለግሉ የማያደርጋቸው ደግሞ ያደረባቸው እርኩስ መንፈስ ነው!!!

እንዲህ ዓይነት ሰዎች ካደረባቸው እርኩስ መንፈስ የተነሣ ጠርተው አይጠሩም፡፡ አሁን ጠሩ ስትሏቸው መልሰው እዚያው ታገኟቸዋላቹህ፡፡ አውሬው እግዚአብሔርን ለመሳደብ ስሙንና ማደሪያውንም እስከመሳደብ ድረስ ራእ. 137 ፈጣሪን የሚገዳደር እጅግ ደፋርና እርኩስ ስለሆነ በማደሪያዎቹ አድሮ ይሄንን የሚያደርገው በእሱ ቤት እግዚአብሔርን ለማብሸቅ መሆኑ ነው፡፡ ሰይጣን የሚሠራውን ጥፋት ሁሉ የሚያጠፋው፣ የተመረጡ የተቀደሱ ሰዎችን ሳይቀር ተፈታትኖ ከተሳካለትም የሚያሰናክለው እግዚአብሔርን ለማብሸቅ ነው ሌላ ዓላማ የለውም!!! ሰው ስለተኮነነ የሚጠቀመው ነገር ኖሮ አይደለም!!!

እናም ማኅበረ ቅዱሳንን የሞሉት እንዲህ ዓይነት ሰዎች ናቸው፡፡ አንድ ላይ የሰበሰባቸውም እንደምናየው ብዙ ሊጠቀምባቸው አስቦ ስለነበረና ስለሚፈልግ ለተንኮሉ ሰይጣን እራሱ ነው የሰበሰባቸው፡፡ ሰይጣን ምን የማያደርገው ነገር አለ??? ጌታ በወንጌል ሰይጣንን የዚህች ዓለም ገዥ!” ዮሐ. 1231, 1430, 1611 እንደሆነ የተናገረውን ታስታውሳላቹህ አይደል???

በዚህ ምክንያት ነው እንግዲህ ማኅበረ ቅዱሳን የተባለው ማኅበር ቤተክርስቲያን እንዲህ ስትማቅቅ ይሄንን ሁሉ አሳር ፍዳና መከራ ስታይ፣ ባቀናቻት በገዛ ሀገሯ ይሄ ሁሉ ኪሳራ ሲደርስባትና እየከሰመች ስትሔድ ለቤተክርስቲያን የቆምን ነን!” እንደማለታቸው ዝም ጭጭ ከማለት በስተቀር አለፍ ካሉም ከባዶ ወሬ ውጭ አንዳችም ነገር ሲያደርጉ ዓይታቹሀቸው የማታውቁትም ለዚህ ነው!!! ጭራሽ እንዲያውም በከንቱ ግን ሰይፍ አይታጠቅምና ክፉ ብታደርግ ፍራ፡፡ ቁጣውን ለማሳየት ክፉ አድራጊውን የሚበቀል የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና!” ሮሜ. 134 በሚለው ቃለ እግዚአብሔር መሠረት ስለ ክርስትና ሲሉ ከክርስትና ጠላቶች ጋር ሲዋጉ በርካታ የክርስትና ጠላቶችን ፈጅተው በሠማዕትነት ያለፉትና ለክብር የበቁት የሮማውያኑ ቅዱሳን ሰማዕታት የእነ ቅዱስ መርቆሬዎስን፣ የእነ ቅዱስ ፋሲለደስን፣ የእነ ቅዱስ ቴዎድሮስን፣ የእነ ቅዱስ ጊጋርንሃይማኖት ያልገባቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ እየጠቀሱ ለማን? ማንን? መቸና እንዴት?” ብለው ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንን ሳይጠይቁና ሳይመረምሩ በመሰላቸው እየተረጎሙ ክርስቲያን ማለት የመሥዋዕት በግ ማለት እንደሆነ አድርገው በመስበክ ይህች እናት አባቶቻችን ታቦት ሳይቀር ወደ የጦር ዐውድ ተሸክመው በመዝመት ስንት ዋጋ ከፍለው ያቆዩዋትን ቤተክርስቲያን አለኝታና መከታ የሚሆን ትውልድ እንድታጣ አድርገዋል!!!

እና እንግዲህ ጥበበኛው ተንኮለኛው ሰይጣን በዚህ ማኅበር አድሮ ክርስቲያን ማለት ምንም ነገር ይፈጠር ምን ስንጥር እንኳን ብትሆን በማንም ላይ የማያነሣና ለገዳዮቹ አንገቱን አመቻችቶ የሚሰጥ የመሥዋዕት በግ ነው!” እያለ የተሳሳተ ስብከት እየሰበከ በሠራው በዚህ ተንኮለኛ ሥራው ጉድ አልሠራንም ታዲያ???

ሲያስፈልግማ እኮ እንኳንና ተራ ምእመን ይቅርና ነቢይና ካህን የሆነ ሰውም ቢሆን ጠላትን መግደል ይቻላል፡፡ ሳሙኤል በቤተመቅደስ ያደገ በእግዚአብሔር በእጅጉ የተወደደ እንደ ሊቀ ነቢያት ሙሴ የእግዚአብሔር ነቢይ፣ ካህንና መስፍን መሆኑ ይታወቃል፡፡ ሳሙኤል አትግደል!” የሚለው የእግዚአብሔር ሕግ እያለና ያውም ካህንና ነቢይ ሆኖ ሳለ ጨካኙን፣ አረመኔውን የአማሌቅን ንጉሥ ሰዎችን እያሰቃየ ይገድል በነበረበት መንገድ አሰቃይቶና ቆራርጦ ገድሎታል ሳሙ. 1533 የእስራኤል ካህንና መስፍን ሳሙኤል ይሄንን በማድረጉ እግዚአብሔር ተደሰተበት እንጅ ያውም ካህንና ነቢይ ሆነህ ነፍስ አጥፍተሃልና ኃጢአተኛ ነህ!” አላለውም!!! የእግዚአብሔር ሕግ በብሉይ ኪዳንም ሆነ በሐዲስ ኪዳን መቸ? ለማን? ለምን? የትና እንዴት?” እየተባለ በፈርጅ በፈርጅ እንደ ዐውዱ ይተረጎማል እንጅ አትግደል ማለት በቃ ማንንም ቢሆን አትግደል ነው!” እየተባለ በጥቁርና ነጭ ዕይታ አይተረጎምም!!!

እነኝህ ጥራዝ ነጠቆቹ ግን ከዚህም አልፈው ዛሬ እንደምታዩዋቸው ከአንባሳደርነት እስከ አማካሪነት፣ ከኢምባሲ ጸሐፊነት እስከ የተለያዩ የመንግሥት መሥሪያቤቶች የተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ድረስ ተሹመው ይሄንን በቀደመ ዘመኑ የኦርቶዶክስን አከርካሪ እንዳያንሰራራ አድርጌ ሰብሬዋለሁ!” ይል የነበረውን አሁን ደግሞ በአደባባይ ኦርቶዶክስ ሀገር ናት!” እያለ እየሸነገለ በጓዳ ግን ኦርቶዶክስ የብልጽግና ፀርና እንቅፋት ናት!” ብሎ በፓርቲ ሰነዱ ላይ በጠላትነት የፈረጃትን ፀረ ቤተክርስቲያን አገዛዝ እያገለገሉ ይገኛሉ!!! እንዲህ የፀረ ቤተክርስቲያን አገልጋይ ሊሆኑ የቻሉትም ካደረባቸው የአጋንንት መንፈስ የተነሣ ነው!!!

እናም ሰይጣን በረቂቅ ጥበብ እየተገለገለበት ያለውን የዚህን ማኅበር ማንነት በደንብ እወቁት፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ለቤተክርስቲያን ብዙ መልካም ነገሮችን የሠራ ሊመስላቹህ ይችላል፡፡ እኔም እንደዚያ ይመስለኝ ነበረ፡፡ በዚህ ምክንያትም በረሐ ካሉ ከበቁ ቅዱሳን አባቶች ጋር ሳይቀር አልግባባ ብየ ብዙ ተቸግሬ ነበረ፡፡ የበቁ አባቶች ማኅበረ ቅዱሳንን ለምን እንደሚጠሉት ምሥጢሩ የተገለጠልኝና የገባኝ ግን አሁን በመጨረሻ ነው፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ለቤተክርስቲያን የሠራው ሥራ ማለት የዜሮ ብዜት ማለት ነው፡፡ ቢሊዮንም ቢሆን ከዜሮ ጋር የሚባዛ ማንኛውም ቁጥር ውጤቱ ምንድን ነው የሚሆነው??? ዜሮ ነው አይደል??? እንደዚያ ማለት ነው የማኅበረ ቅዱሳን ዋጋ ለቤተክርስቲያን!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው