October 8, 2020

አቶ ልደቱ ዛሬ ችሎት ቀርበዋል። የዛሬው ቀጠሮ በምስራቅ ሸዋ ከፍተኛ ፍርድ ለዛሬ የተጠረጠሩበት ወንጀል ያስከስሳል አያስከስስም የሚለውን ለመወሰን ነበር።–የዛሬው ችሎትም ያስከስሳል ስለዚህ ለማክሰኞ አቃቢ ህግ ምስክሮች አቅርቦ እንዲ ያስረዳ ተወስኗል። አቶ ልደቱም እስከ አሁን ከአንድም ሁለት ሶስቴ ፍርድ ቤቱ በኔ ላይ ውሳኔ ሰጠቷል። ነገር ግን ፖሊስ አለቅም ብሏል።–ይሄ የሚያሳየው የታሰርኩት በፖለቲካ አስተሳሰቤ ነው። የሚፈለገው የኔን ድምፅ ማፈን ነው። ፍርድ ቤት፣ ዳኛ እና የፍትህ ስርአት ካልተከበረ አገር አለኝ ማለት አልችልም። እኔ ፍርድ ቤት ነፃ አድርጎኝ ለ5 ደቂቃ የፍርድ ቤት ውሳኔ ተፈፃሚ ሆኖ ሌላ መጥሪያ ተሰጥቶኝ ብታሰር ደስ ይለኝ ነበር።–ነገር ግን ፍርድ ቤት ቀጠሮ መሀል ችሎት የሚወስነው ውሳኔ ምን እንደሆነ ይጠበቅ እና ሌላ የክስ ቻርጅ እየተዘጋጀ በፍትህ ስርአቱ ነው እየተቀለደ ያለው። ስለዚህ ለችሎቱ ክብር እና ለተቋማችሁ ይህን ቀልድ አስቁሙ ብለዋል።–ፍርድ ቤቱም ፖሊስ ለምን አለቅም እንዳለ መርምረው ነገ ውሳኔ እንደሚሰጡ እና ጠበቆች ውሳኔውን መጥተው እንዲሰሙ ትእዛዝ ሰጥቷል።አቶ አዳነ ታደሰ (የኢዴፓ ፕሬዘዳንት)