https://www.dw.com/amB4/a-55208003
ወይዘሮ ያየሽ ተስፋሁነይ በተለይ ከዶይቼ ቨለ ጋር ባደረጉት ቃለ-መጠይቅ፤ “አንድ ፓርቲ በዘፈቀደ ተነሱና ውጡ ስላለ ብቻ ፓርላማን ለቆ መውጣት ህጋዊ ተቀባይነት የለውም” ብለዋል።
«የአንድ ፓርቲ ጫናና ተፅዕኖም ሆነ ፅንፍ የረገጠ አመለካከት የመረጠኝን ሕዝብ በፅናት ከማገልገል እንድቆጠብ አያግደኝም» ወይዘሮ ያየሽ ተስፋሁነይ
የአንድ ፓርቲ ጫናና ተፅዕኖም ሆነ ፅንፍ የረገጠ አመለካከት የመረጠኝን ሕዝብ በፅናት ከማገልገል እንድቆጠብ አያግደኝም ሲሉ የህወሓትን ጥሪ ወደጎን በመተው በቅርቡ በፓርላማ ስብሰባ ላይ የተካፈሉት ብቸኛዋ የህወሓት እንደራሴ ገለፁ:: የመንግሥት የአምስት ዓመታት ህጋዊ የስልጣን ዕድሜ ካለፈው መስከረም 25,2013 ዓ.ም በኋላ አብቅቷል፤ ሲል በሕዝብ ተወካዮች፣ በፌዴሬሽን እና በሚኒስትሮች ምክርቤቶች የሚገኙ ተጠሪዎቹ ከፓርላማም ሆነ ከመንግሥት አመራርነት እራሳቸውን እንዲያገሉ ህወሓት ያስተላለፈውን ጥሪ እንደማይቀበሉ ገልፀው በስብሰባው የተሳተፉት ብቸኛዋ የህወሓት እንደራሴ ወይዘሮ ያየሽ ተስፋሁነይ በተለይ ከዶይቼ ቨለ ጋር ባደረጉት ቃለ-መጠይቅ፤ “አንድ ፓርቲ በዘፈቀደ ተነሱና ውጡ ስላለ ብቻ ፓርላማን ለቆ መውጣት ህጋዊ ተቀባይነት የለውም” ብለዋል:: አንድ ግለሰብ በፓርቲ ተወዳድሮ የፓርላማ አባል ከሆነ በኋላ ተገዢ የሚሆነው ለሕዝቡ፣ ለህሊናውና ለሕገ መንግስቱ ነው ያሉት እንደራሴዋ፤ የኮረና ወረርሽኝ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የዓለም ስጋት በመሆኑ በሕጋዊ አግባብ ሀገራዊ ምርጫው በመተላለፉ ህወሓት የፓርላማው የስራ ጊዜው አብቅቷል ማለቱ ፈፅሞ አሳማኝ እንዳልሆነና እንደማይቀበሉትም አስረድተዋል።አድርገዋል:: ወይዘሮ ያየሽ ከህወሓት ጋር አብሮ የመስራት ፍላጎት እንደሌላቸውና፤ ከቀጣዩ ምርጫ በኋልም የብልጽግናንም ሆነ ሌሎች የትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ተቀላቅሎ በፖለቲካ ተሳትፎዋቸው ለመቀጠል ገና ውሳኔ ላይ አለመድረሳቸውንም ይፋ አድረገዋል:: ዝርዝሩን የፍራንክፈርቱ ወኪላችን እንዳልካቸው ፈቃደ አጠናቅሮታል።
እንዳልካቸው ፈቃደ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ