9 ጥቅምት 2020

ደራሲ መዓዛ መንግሥቴ

ጣልያን ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት ከፍተኛ ተጋድሎ ያደረጉ ሴት የነፃነት ታጋዮችን በሚዘክረው ‘ዘ ሻዶው ኪንግ’ መፅሃፏ ኢትዮጵያዊ-አሜሪካዊቷ ደራሲ መዓዛ መንግስቴ ለቡከር ሽልማት ከታጩት መካከል አንዷ ሆናለች።

ለነፃነት በተደረገው ትግል ላይ የጥቂት ወንዶች ሚና በጎላበት ሁኔታ ሴት ነፃነት ታጋዮች ከታሪክ መዝገብ መፋቃቸውንና ግዙፍ ሚናቸው ምን ይመስል ነበር በማለት አስርት አመታትን ወደ ኋላ ተጉዛም መዓዛ በ’ዘ ሻዶው ኪንግ’ ታስቃኛለች።

መዓዛ መንግሥቴ ከቢቢሲ ጋር ስለ አዲሱ መፅሃፏ፣ በጦርነቱ ወቅት ኢትዮጵያውያን ሴቶች በጣልያን ወታደሮች የደረሰባቸውን መደፈርና ጥቃት፣ ለአገር ነፃነትና በሰውነታቸውም ለመከበር ያደረጉትን ትግል በተመለከተም ቆይታ ካደረገችባቸው ጉዳዮች መካከል ይገኙበታል።

ቢቢሲ፡ ለቡከር ሽልማት በመታጨትሽ ምን ተሰማሽ?

መዓዛ፦ታቂያለሽ የማይታመን ነው። ምንም ያልጠበቅኩት ጉዳይ ነው። ለኔ ዋነኛውና ትልቁ ነገር መፅሃፉን መጨረስ ነበር። ከሚባለው በላይም መፅሃፉን ለመጨረስ ረዥም ጊዜ ነው የወሰደብኝ።

ለበርካታ አመታትም መፅሃፉን እጨርሰዋለሁ፤ አቅሙ የለኝም ብየም የማስብበት ጊዜ ነበር። በዚህም ትግል መፅሃፉን ጨርሼ፣ ማሳተሜ እንዲሁም ሰዎች ማንበባቸው ለኔ በጣም አስደናቂ ነው። ሆኖም ከዚህ ባለፈ በሽልማቱ ውስጥ መካተቴን በተደወለልኝ ወቅት የተሰማኝን ስሜት እንዲህ በቃላት ልገልፀው አልችልም። የሆነ የምኖርበት አለሜ ግልብጥብጡ የወጣ ነው የመሰለኝ፤ ለካ ይቻላል! በጣም መልካም ነው። ሌላ ምን እላለሁ።

ቢቢሲ፡ የመጀመሪያ መፅሃፍሽ ‘ቢኒዝ ዘ ላየን ጌዝ’ ከወጣ ከአስር አመታት በኋላ ነው ‘ዘ ሻዶው ኪንግ የተፃፈው። ዘ ሻዶው ኪንግ እንዴት እንደተፃፈ ልትነግሪን ትችያለሽ? መፅሃፉ በዋነኝነት የሚያጠነጥንባቸው የሴቶች አርበኞች ታሪክ፣ ታሪክን በነሱ መነፅር ማየትና መፃፍስ ምን ይመስላል?

መዓዛ፦መፅሃፉን ስጀምረው ዋነኛ ፍላጎቴ የጣልያን ወረራን በተመለከተ መፃፍ ነበር። የጣልያን ጦር ከአፍ እስከ ገደፉ በመሳሪያ ቢታጠቅም ለነፃነት ሲባል ስለታገሉና ስለተዋደቁ ኢትዮጵያውያንና ከአምስት አመት የመራራ ትግል በኋላ ማሸነፍ ስለቻሉት ኢትዮጵያውያንን ነበር መዘከር የፈለግኩት።

ታሪኩን መፃፍ ስጀምርም የተገነዘብኩት ነገር ቢኖርና የበለጠ የሳበኝ ነገር ቢኖር የግል ታሪኮች፣ የቀን ተቀን ኑሮ፣ ግንኙነት ነበር። ጦርነቱ እንደዚያ በተፋፋመበትና በተጋጋመበት ወቅት በወቅቱ የነበሩ ኢትዮጵያውን የቀን ተቀን ህይወትና፣ የርስ በርስ ግንኙነት የበለጠ ሳበኝ። በዚህ ሁሉ ቀውስ መካከል ኑሮ ምን ይመስላል የሚለውን ማውጠንጠን ጀመርኩ።

የጦርነት ገድሎችን ወደ ጎን ገሸሽ አድርጌም በዚህ ውስጥ ጋብቻዎች እንዴት ይሆናሉ? የፍቅር ግንኙነቶች በጦርነት ውስጥ ምን ይመስላሉ? እርስ በርስስ ያሉ ግንኙነቶች፣ በሴቶች፣ በወንዶች መካከል ጦርነቱ ምን አይነት ተፅእኖን ያሳርፋል የሚሉትንም ማጥናት ጀመርኩ።

በዚያውም በአለም ላይ ተንሰራፍቶ የነበረው የቅኝ ግዛት ኢንተርፕራይዝ ታሪኮችን (አፈ ታሪኮችን)፣ እምነትን፣ ሃሰትን፣ እና ፎቶዎችን በመጠቀም እንዴት ሚሊዮኖችን ለመጨቆንና ተቀባይነት ያለው ለማስመሰል እንዴት እንደጣሩም ማየት ጀመርኩ።

እናም ታሪኩ ከጣልያንና ኢትዮጵያ ጦርነት በላይ ሆነ። ከዚያም ባለፈ እኛ እና እነሱ አብረን እንዴት እንደምንኖር መመርመርና ማጥናቴን ቀጠልኩ።

ቢቢሲ፡ የምርመራው ጊዜ ምን ያህል ጊዜ ወሰደብሽ?

መዓዛ፦ ሳቅ የአምላክ ያለህ፣ ታቂያለሽ! መፅሃፉን ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ለመጨረስ አስር አመታት ያህል ወስዶብኛል። ለሁለት ወይም ለሶስት አመታት ያህል አትኩሮቴ ምርምሩ ላይ ነበር። በመሃልም ለመፃፍ እሞክራለሁ።

ምርመራውንም ለማድረግ ጣልያንኛ ቋንቋ መማር ነበረብኝ። በርካታ የተከማቹ መዛግብትን ለመፈተሽም በአስተርጓሚ መስራት አልፈለግኩም።

ከዚያም ባለፈ ስለ ጦርነቱ የነበረኝ ስሜት እና በአፍሪካውያን ላይ ጦርነት ስላወጁት አውሮፓውያን የነበረኝ ስሜት አሉታዊ ወይም ጨለምተኛ ነበር።

የጣልያንን መሬትም ስረግጥ ከፍተኛ የሆነ ንዴት ነው የተሰማኝ። መዛግብታቸውን ሳገላብጥና የምርምሩን ስራ ስጀምር የትኛውም ጣልያናዊ ምንም እንዲለኝ አልፈለግኩም።

ከዚያም አሰብኩበትና በከፍተኛ ንዴት ሆኖ መፅሃፍ መፃፍ አይቻልም አልኩኝ። እንዴትስ የተፈጠረውን ነገር ሙሉ በሙሉስ መረዳት ይቻላል? ብዬ ራሴን መጠየቅ ጀመርኩ።

እናም ከዚያ በኋላ ነው ጣልያኖቹን በተለይም ኢትዮጵያን የወጉትን ወታደሮች ልጅ፣ ልጆች ለማናገር እናም በምን መንገድ እንደሚረዱት ለማወቅም ነው ጣልያንኛ የተማርኩት።

ይሄም በራሱ የተወሰነ ጊዜ ወስዷል። ታሪኩም ሙሉ በሙሉ ተከፈተልኝ ማለት እችላለሁ። ታሪኩም የግለሰቦች ታሪክ ሆነ።

ቢቢሲ፡ የግለሰቦች ታሪክ ነው ብለሽ ስትናገሪ አንድ ነገር አስታወሰኝ። በአንድ ወቅት ሴት አያትሽ በጦርነቱም ዘምታ እንደነበር ተናግረሻል። ከመፅሃፉ ታሪክ ጋር ምን ያህል ቁርኝት አለሽ። ከአንቺስ የግል ታሪክ ጋር ምን ያህል የተገናኘ ነው?

መዓዛ፦ጦርነቱ ቤተሰባችን ጋር ይገናኛል። በአባቴ በኩል ወንዱ አያቴም ሆነ የአባቴ ወንድሞች (አጎቶቼም ) በጦርነቱ ዘምተዋል።

የአባቴ የአጎት ልጆችም በጦርነቱ ተሰውተዋል። የቀድሞ ፎቶዎችንም ከቤተሰብ ጋር ሰብሰብ ብለን በምናይበት ወቅት በጦርነቱ የተገደሉ ሰዎችን እየጠቆሙ እነዚህን አጥተናል ይላሉ።

በጦርነቱ ላይ የሴቶች ዘማቾችን ታሪክ ሰምቻለሁ። ነገር ግን ሁልጊዜም ቢሆን የሚተረክበት መንገድ ወንዶቹን እንዴት ተከትለው እንደሄዱ ነው። የሞቱትን በመቅበር፣ የቆሰሉትን በመንከባከብ፣ ውሃ በመቅዳትና በመሳሰሉት፤

መፅሃፉን ጨርሼ ለመጨረሻ ጊዜ ምርምር ለማድረግ ወደ ኢትዮጵያ ስሄድ፣ በመፅሃፌ ውስጥ የተካተቱትና ጦርነት የተካሄደባቸውን ቦታዎች ለመጎብኘትም ከእናቴ ጋር አብረን ሄድን። ጉዞውም አስር ቀናትን ያህል የፈጀ ነው።

ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ፣ ስለ መፅሃፉ እያወራን እንዲሁም በጦርነቱ ላይ የተሳተፉ ሴቶች ፎቶግራፍ ማግኘቴን እየነገርኳትም ነበር። ምንም እንኳን ታሪኩን ባለውቀውም ሌሎች ሴቶች አርበኞች ሊኖሩ ይችሉ ይሆን እያልኳት እያለ እናቴም ዝም ብላ እንደ ቀልድ ቅድመ አያትሽስ አለችኝ?

ኩኪዎችን መጠቀም ላይ መስማማትዎን ያሳውቁን

እኛም ሆን ቴክኖሎጂያችንን የሚጠቀሙ አጋሮቻችን ለምሳሌም ኩኪዎችን የምንጠቀመው, ና መረጃዎችንም የምንሰብስበው የሚፈልጓቸውን መረጃዎችና ማስታወቂያዎች ቅድሚያ እንዲያገኙዋቸው በማሰብና አግልግሎታችንም የተሻለ እንዲሆን ነው።እባክዎ መስማማትዎን ያሳውቁን

BBC News, አማርኛወደ ዋናው ይዘት ይለፉ

ሥነ-ጽሑፍ፡”ሴቶች የታሪክ አካል ተደርገው አይቆጠሩም፤ በታሪክነትም አንመዘግባቸውም” መዓዛ መንግሥቴ

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, ለቡከር ሽልማት የታጨችው ኢትዮጵያዊ-አሜሪካዊቷ ደራሲ መዓዛ መንግስቴ

እንደዛ ስትለኝ በማይገባኝ ቋንቋ እያወራች ሁሉ ነው የመሰለኝ። እና ምን አልሺኝ ብዬ ጠየቅኳት። በእነዚህ አመታት ሁሉ ምርምር ሳደርግ ታውቃለች። ስለ ሁሉም ነገር ታውቃለች። ከነዚህ ሁሉ አመታት በኋላ በዚህ ወቅት ነው ለመናገር የመረጠችው እናም ለምን ከዚህ ቀደም አልነገርሽኝም? ብዬ ጠየቅኳት።

እሷም በምላሹ ጠይቀሽኝ አታውቂም አለችኝ። በጣም ነው ያስደነቀኝ። ምክንያቱም የዚህ ጦርነት ታሪክ ምንድን ነው ስንል ሴቶች እርስ በርስ የሚነጋገሩት ታሪክ አይካተትም፤ በቤታቸው፣ በማዕድ ቤት። በእህቶች መካከል የሚነገረው ታሪክ፣ በእናትና በልጅ መካከል የሚነገረው እንደ ታሪክ አይነገርም።

ወንዶቹን ነው የምናየው። በቤተሰቤ የወንዶቹን ታሪክ አውቀዋለሁ ነገር ግን ይህንን ሰምቼ አላውቅም። ይሄ መፅሃፍ ከወጣ በኋላም ለብዙዎች የምናገረው በቤተሰቦቻችሁ ሴቶቹን ጠይቁ።በጦርነቱም ሆነ ነፃ በማውጣት ስለተሳተፉት በመላው አፍሪካ፣ በደቡቡ አለም፤ ምክንያቱም ሴቶች በእነዚህ ጦርነቶችም ሆነ ነፃ በማውጣቱ ተሳትፈዋል።

የናይጄሪያ ሴቶች ታሪክ መንፈሴን አነቃቅተውታል፣ የደቡብ አፍሪካ ሴቶች ለነፃነት ያደረጉትን ትግል መጥቀስ ይቻላል፤ ይሄ አዲስ ታሪክ አይደለም።ነገር ግን አናወሳቸውም፤ ስለነሱም አናወራም። የታሪክ አካል ተደርገውም አይቆጠሩም። ታሪክ ናቸው ተብለውም አይነገርላቸውም። በመማሪያ መፅሃፎች ውስጥ አልተካተቱም።

በአለም ታሪክ መዛግብት ውስጥም አልተካተቱም። በአለም ላይ ባለው ስርአት የአፍሪካ ታሪክ የአፍሪካ ነው። የአውሮፓ ታሪክ ደግሞ የአለም ታሪክ ተደርጎ ነው የሚታየው። እሱንም የአተራረክ መንገድ ነው መስበር የፈለግኩት። ጥቁር ሴቶች የአለም ታሪክ አካል ናቸው። ከመጀመሪያው ጀምሮ ታሪክ ሰርተዋል የሚለውንም ማስተላለፍ ነው የፈለግኩት

ቢቢሲ፡ እስቲ በመፃህፍሽ ላይ ስላሉት ሴቶች እናውራ፤ ዋነኛ ገፀ- ባህርያቱ ሴቶች ናቸው ለምሳሌ ሂሩት። ከዚህም በተጨማሪ የሴቶች ወታደሮች (አርበኞች) አስተዋፅኦ ጎልቶ እንዲወጣ አድርገሻል። ይሄ መፅሃፍሽ ላይ መካተቱ በጣም የሚያስደስት ነው። በዳሆሜ(ከ16ኛው- 18ኛው ክፍለ ዘመን በአሁኗ ቤኒን አካባቢ የነበሩ የሴት ጦረኞች) ስለነበሩት የሴት ወታደሮች ሰምተናል። መፅሃፍሽ ላይ የተጠቁሰት የሴት ጦረኞች በቅርብ ጊዜ በአፍሪካ የነበረ መሆኑን ማወቅም፣ ማንበብም በጣም ያስደስታል። መፅሃፍሽን መፃፍ ስትጀምሪ የነዚህ አርበኛ ሴቶች ታሪክ ዋነኛ የታሪኩ አካል ይሆናል ብለሽ አስበሽ ነበር?

መዓዛ፡ በጭራሽ! መጀመሪያ ስፅፍ የነበረው ሳድግ የሰማኋቸውን የጦርነት ታሪኮች አይነት ተመሳሳይ መጽሐፍ እፅፋለሁ ብዬ ነበር የተነሳሁት። ስለ ሴት አርበኞች ታሪክ የማውቀው አልነበረም።

ምናልባት አንድ የሰማሁት ታሪክ ሴቶቹ ከጣልያን እንደሚወልዱ ሰምቻለሁ። ወይም ደግሞ አክስትሽ ግማሽ ጣልያን የሆነ ሰው አገባች የሚሉ ታሪኮችን እሰማለሁ። ምን ተፈጠረ ስል? ምላሹ ስለዚህ ጉዳይ አናወራም የሚል ነበር።

እናም በርካታ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ወሲባዊ ጥቃት እንደደረሰባቸውና እንደተደፈሩ አወቅኩኝ። ጥቃቱ፣መደፈሩ፤ ማስፈራራቱ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ሰውነታቸው ላይ የታወጀባቸው ሌላኛው አይነት ጦርነት ነበር።

የደረሰባቸውን ጥቃት፣ መደፈር ማሳያው ግን በግልፅ እየታየ ነበር። እሱን ማሳየት ፈልጌ ነበር፤ ነገር ግን ስለ ጦርነቱ የወንዶች ታሪክ ነበር እየፃፍኩ የነበረው እሱንም ነው በደንብ የማውቀው፤

ዚህ አጋጣሚ አስደሳች የምለውና በኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ላይ ህዳር 19፣ 1935 የወጣ አንድ ፅሁፍ አየሁ።

ይህም ኢትዮጵያዊት ሴት በጦርነቱ አውድማ ላይ በጦርነቱ የወደቀውን የባለቤቷን ጠመንጃ አንስታ እሱ ሲመራው የነበረውን ሁለት ሺህ ወታደሮች (ዘማቾች) በመምራት ጦርነቱን ቀጥላለች።

ፅሁፉን ሳነብ፣ መፅሀፌን፣ ታሪኩን በአዲስ መልክ ነው የቀያየረው። ጠመንጃውን አንስታ ወንዶቹን ለመምራት በጦርነቱ ውስጥ ስትዋጋ ነበር ማለት ነው።

ወንዶቹም እንዲከተሏት ያስቻላቸው በሆነ የጦር አመራር ቦታ ነበረች ማለት ነው። ለጦሩ አዲስ አልነበረችም። ይህም ማለት በጦሩ ውስጥ በርካታ ሴቶች ነበሩ። ጭንቅላቴንም ሆነ መፅሃፉን በአዲስ መልኩ ነው የከፈተው

ቢቢሲ፡ መፅሃፉ ምን ያህሉ ነው በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተው?

መዓዛ፡ ሁሉም ማለት በሚቻል ሁኔታ እውነተኛ ታሪክ ነው።

እንደ ሂሩት አይነት ሰው አውቃለሁ? ስለ ሂሩት ስፅፍ ታዳጊ ልጅ ሆና የአባቷን ጠመንጃ ለማግኘት ስለምትታገል ልጅ አላውቅም ነበር። ቅድመ አያቴ የአባቷን ጠመንጃ ለማግኘት መታገሏንና መፋለሟን አላውቅም ነበር።

እንዲህ አይነት ታሪኮች በእውነተኛው መፈጠራቸውን እናቴ እስከምትነግረኝ ድረስ አላወቅኩም ነበር። ይህንንም የነገረችኝ መፅሃፌን እየቋጨሁ በነበረበት ወቅት ነው።

ነገር ግን መፅሃፌ ላይ እንዳሉት ገፀ ባህርያት ሂሩት፣ አስቴር፣ በታሪክ እንደነበሩ አውቃለሁ። ከልብወለድ መፅሃፎች ጋር በተያያዘ ሁሌም የሚነሳው አንዱ ይህ ነው።

በታሪክ ውስጥ የተፈጠረውን ክፍተት አግኝቸዋለሁ። ነገር ግን እነዚህ ሴቶች ነበሩ፣ ምንም እንኳን ስማቸው አስቴር፣ ወይም ሂሩት ባይሆንም።

መፅሃፉ ላይ ያለችው ምግብ አብሳይዋ ስሟን መናገር አትፈልግም፣ እንደ ምግብ አብሳይዋ ሴት በባርነት የተገዙ ሴቶች አውቃለሁ፤ ሆኖም የሰብዓዊነት ክብራቸውን በሆነ መልክ ያስጠበቁና ያስከበሩ ሴቶችን አውቃለሁ።

የመኖር መብታቸውንም በቻሉት መንገድ ያስከበሩ ሴቶችን አይቻለሁ። ከኢትዮጵያ፣ ከአፍሪካ እንዲሁም ከሌሎች አገራት የሚመጡና በተለምዶም ደካማ ተብለው የሚጠሩ ሴቶችን፤ ወይም ተጨቆኑ የሚባሉ ሴቶችን፤ እኔ ደካማ ሴት አጋጥማኝ አታውቅም።

ዝም ያሉ ወይም ዝምታን የመረጡ ሴቶች አጋጥመውኛል፤ አውቃለሁ። ዝምታ ግን ደካማነት አይደለም። ያንንም ነው በመፅሃፌ ላይ ማሳየት ፈለግኩኝ።

ቢቢሲ፡ በቤተሰብሽ ውስጥ ስለ ጦርነቱ የሚያውቁ ግን ምንም ማለት ያልመረጡ እንዳሉ እየተናገርሽ ነበር። የሌላ ትውልድ አካል መሆንሽና በጦርነቱ ውስጥ አለመሳተፍሽ ታሪኩን በልብወለድ መልኩ እንድትናገሪ ቀለል አድርጎልኛል ብለሽ ታስቢያለሽ?

መዓዛ፡ በሆነ መንገድ ቀለል አድርጎልኛል። ከጦርነቱም ሆነ ካስከተለው ጉዳት ጋር ቀጥታ የሆነ ግንኙነት የለኝም።

ጦርነቱ ያስከተለውን ውርድት፣ ጣልያኖች በሰው ልጅ ላይ የፈፀሙትን ውርደት፣ ለመዝናናት ሲሉ ያስከተሉትን ኢሰብዓዊ ድርጊትና ስቃይ አላውቀውም።

ቅኝ ግዛት ይህንን ነው የፈፀመው። ጭካኔንና ኃይልን በሰዎች ላይ ስለሚችሉ ብቻ ጭነዋል። ያ ሁኔታ እኔ ላይ አልተፈፀመብኝም።

ነገር ግን በዚህ ፅሁፍ ሂደት ላይ የተፈጠሩትን ታሪካዊ እውነቶች እንደገና ለማሰብ በምሞክርበት ወቅት፣ ጣልያኖችን የፈፀሙትን ግፍ ለማሰብ በምሞክርበት ወቅትም በከፍተኛ ሁኔታ ሸክም እንደተጫነብኝ ያህል እየከበደኝ መጣ።

ታሪኩ ከአስርት አመታት በፊት የተፈጠረ ሳይሆን አሁን እየተከናወነ ያህል ይሰማኝ ነበር።በተቻለኝ መጠን ለማድረግም የሞከርኩት አንባቢው ያንን ወቅት እንዲያልፍበት ነገር ግን እንዲቋቋመው ማድረግ ነው። እሱን ማመጣጠን ትግል አለ።

ከዚያ በተጨማሪ ደግሞ ስለ ወሲባዊ ጥቃትም ፅፌያለሁ፣ አባዊ ስርአት (ፓትሪያርኪ) ሴቶች በየትኛውም የጦርነት ወገን ቢሆኑም ያስከተለውን ጭቆናና ጥቃትም ተመልክቻለሁ።

በሴቶች ላይ የሚደርሰው ጭቆናና ግፍ እስካሁን ድረስ የቀጠለውና የትኛውም የአለማችን ክፍል የሚፈጠረውን የሴቶች ጭቆናም ጋር የተያያዘ ነው። ይህንንም ስናየው ታሪኩ ያለፈ፣ የአሁንና የቀጠለ ይሆናል። ከአሁኑ የአለማችን እውነታም ጋር ይገናኛል። ይህንን ስፅፍ አሁን አለምን ካጥለቀለቀው ‘ሚቱ’ እንቅስቃሴ በፊት እንዲሁም በዚያኑ ወቅት ነው።

ከሂሩት ታሪክ ባሻገር፣ የሴቶችና የታዳጊዎችን ታሪክ መስማት ልብ የሚሰብር ጉዳይ ነው። መፅሃፉ ላይ ያሉት ሂሩት፣ አስቴርና በአሁኑ ሰዓት የምሰማቸው የሴቶችና ታዳጊዎች የትግል ታሪክ ይመሳሰላል።

በቻሉትም መጠን በህይወት ለመኖር ይታገላሉ፤ ትግላቸውም እንደቀጠለ ነው። ሴት አርበኞቹም ነበሩ፤ በአሁኑ ሰዓትም አሉ።

በየመንገዱም፣ በየጎዳናው ፖሊስን፣ ሙስናን ሲጋፈጡ እናያቸዋለን። ፖሊሲዎችን ተቃውመው ድምፃቸውን ሲያሰሙም እናያለን። ጨቋኝ የትዳር አጋሮቻቸውን ሲታገሉም እያየን ነው። ይሄ ለኔ ተስፋ ይሰጠኛል። ስፅፈውም ተስፋን የሰጠኝ ጉዳይ ነው።

ቢቢሲ፡ መፅሃፉ ከታተመ በኋላ ምን አይነት አስተያየቶችን እያገኘሽ ነው?

መዓዛ፡ በጣም የሚያስደስት ነው። ከአንባቢዎች ኢ-ሜይል፣ ደብዳቤ ማግኘት ደስ ያሰኛል። ከመላው አለም ነው መልእክት እየደረሰኝ ያለው። መፅሃፉ ጥሩ ተቀባይነትን አግኝቷል። ኢትዮጵያዊ ስለሆኑ ብቻ ሳይሆን ታሪኩ ጋር መገናኘት በቻሉ አንባቢዎች ሁሉ በደንብ ተቀብለውታል።

የስልጣን፣ ኃይል፣ ጥቃት፣ ቅኝ ግዛትን ታሪክ የተረዱ ሁሉ መፅሃፉ ከፍተኛ ትስስር አለው፤ ትርጉምም ሆነ ተስፋ ሰጥቷቸዋል። ይህም ሁኔታ በቃላት መግለፅ ከምችለው በላይ ያስደስታል።

ከአንዲት ኢትዮጵያዊት ሴት አንድ ኢሜይል አገኘሁ። “ምናልባት በአያትሽ እድሜ ላይ ልሆን እችላለሁ። መፅሃፍሽ ወደ ልጅነቴ መለሰኝ። ያስታወሰኝም በ60ዎቹ የነበረውን አብዮት ነው።

ያንን ጊዜ ለተወጡት ሴቶች በሙሉ ዘውድ ባጠልቅላቸው ምኞቴ ነው” አለችኝ። ሁኔታው በጣም ነው የነካኝ። እንደዚህ ስሜት የሚነኩ የተለያዩ መልዕክቶችን አገኛለሁ፤ የሚያስደስት ነው። ለዚህም አንባቢው በዚህ መንገድ ትስስር መፍጠሩ ክብር ይሰማኛል።

ቢቢሲ፡ እንደ ፀሃፊ ተፅእኖ ያሳረፉብሽ እነማን ናቸው?

መዓዛ፡ ለኔ ዋነኛ ተፅእኖ አሳረፍብኝ የምላት የጋናዋ ፀሃፊ አማ አታ አዱ ‘አወር ሲስተር ኪል ጆይ’ የሚለው መፅሃፍ ነው።

ይህንን መፅሃፍ ሳነብ ገና ጀማሪ አንባቢ ነበርኩኝ። ኮሌጅ ትምህርቴን የጀመርኩበት ወቅት ነው። ትምህርቴን የተማርኩት በአሜሪካ ነው፣ መምህራኖቻችን እንድናነብ ይሰጡን የነበሩት መፃህፍት የኔን ታሪክ ያላካተተ ነው።

የኔ ታሪክ እንደ ስደተኛ፣ አፍሪካዊ፣ እንደ ጥቁር ሴት አይንፀባረቅበትም። በዚህ ማህበረሰብ ውስጥ ራሴን እንደ እንግዳ የማይበትና መቼም ቢሆን መገናኘት ያልቻልኩት ማህበረሰብ ውስጥ ነው።

እናም በዚህ ወቅት ይህንን መፅሃፍ ሳነብ ብርሃን የተገለጠልኝ ነው የመሰለኝ። ራሴንም በተወሰነ መልኩ አገኘሁበት። የሆነ ሰው ዕውቅና የሰጠኝ መሰለኝ፣ ራሴን አየሁበት።እዛ መፅሃፍ ላይ የምመለስበትም ምክንያት በመሰረታዊ ደረጃ ፀሓፊዋ ያደረገችው ነገር ረቂቅ ነው።

ግሩም በሆነ መልኩ የተፃፈ ነው። ለዚያም ነው ይህ መፅሃፍ መሰረቴ ነው የምለው። ከዚያ በተጨማሪ ከግሪክ ፀሃፊዎች መካከል የሆመርን ፅሁፎች ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለሁ ትርጉም ይሰጡኝ ነበር።

ታሪኮቹን በጣም ነበር የምወዳቸው እናም የሚስቁብኝና የሚያፌዙብኝ ነበሩ። አንዲት አፍሪካዊት፣ ጥቁር የግሪክ ታሪኮችን ለምን ታነባለች? መምህራኖቼም ከግሪክ ፀሃፊዎች ጋር በፍፁም ትስስርም ሆነ ግንኙነት እንደሌለኝ አድርገው ነው ያሰቡኝ።

እናም በመፅሃፎቹ ላይ ኢትዮጵያ የሚለውንም ሳገኝ ይህ አፍሪካዊ ነው ማለት ጀመርኩ። ሮም መንደር እያለች እኛ ሃገር መስርተናል፤ እናንተ ጭራሽ አገር የሚለውንም ፅንሰ ሃሳብ አታውቁትም ነበር እላለሁ።

እኛ ግን በጥንታዊ ግሪክ ውስጥ ተጠቅሰናል፤ አለን። ሆመር እውቅና ሰጥቶናል ለምንድን ነው የኔ ታሪክ የማይሆነው፤ ከኔ ጋር ትስስር የማይኖረው ለምንድን ነው?

የሆመርን ታሪኮች በማይበትም ወቅት፣ አፍሪካውያን ለምን ያህል ሺ አመታት ነው ታሪክ ነጋሪዎች የነበሩን። የማሊ ግሪዮትስን (ታሪክ ነጋሪዎችን) መጥቀስ ይቻላል።

የምዕራቡ አለም በጭራሽ ያልነበረው ነው። ሆመር አዲስ ነገር አልፈጠረም። በአፍሪካ ከጥንት ጀምሮ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የነበረ ነው።

ታሪኮቻችንን ከትውልድ ወደ ትውልድ አሻግረናል፤ ትዝታዎቻችንን፣ የዘር ግንድና አመጣጥ በዘፈኖቻችን በታሪኮቻችን አሻግረናል። የሆመርን ግጥሞች መግቢያ ሳነብ ለኔ አዝማሪዎችን ያስታውሰኛል። በዚህ ባህል ነው ያደግኩት፣ አቀዋለሁ።

ቢቢሲ፡ ታሪኮቻችንን በቃል መንገር ብቻ ሳይሆን በመፅሃፍ መልክ መፃፉ ጥቅሙ ምንድን ነው ብለሽ ታስቢያለሽ?

መዓዛ፡ ይሄንን ሳስብ የቅድመ አያቴ ታሪክን አስታውሳለሁ። ከመሞቷ በፊት አግኝቻታለሁ። ነገር ግን የጦርነቱ አርበኛ እንደነበረች አላውቅም። ስለዚህ ታሪክ ምንም አላውቅም። ከሰዎች ሰዎች ሲነገር የማቀውን ነው የሰማሁት።

እናቴ ባትነግረኝ ኖሮ ይሄ ታሪክም ሳይታወቅ፣ ከታሪክ መዛግብት ተፍቆ ይቀር ነበር። ለዛም ነው ታሪክ መፃፍ ያለበት፣ መመዝገብ ያለበት፣ በበርካታ የእስያና አፍሪካ አገራት አገር በቀል ቋንቋዎች እየጠፉ ነው፣ እየሞቱ ነው።

በርካታዎቹም የራሳቸው ፊደል የላቸውም። እናም የምናጣው ታሪክ ስጋት ፈጥሮብኛል። ሆኖም በአሁኑ ወቅት ቴክኖሎጂን በመጠቀም መቅረፅ (ሬኮርድ) ማድረግ እንችላለን። ታሪኮቹን፣ ቋንቋዎቹን መቅዳትና ማስቀመጥ የምንችልበት ዘመን ላይ ነን።

ቤተሰቦቻችሁ ጋር ሄዳችሁ ታሪካቸውን ጠይቁ፣ በስልካችሁ ቅዷቸው። ምን እንደሚያመጣ አታውቁም። እነዚህን ታሪኮች እየሰበሰቡ ያሉ ሰዎች እንዳሉም ተስፋ አደርጋለሁ። ማግኘትም እፈልጋለሁ። ሆኖም በመላው አፍሪካ ይህንን ማድረግ አለብን።

የምዕራቡም አለም በሚፅፈው ታሪክ ነው የበላይነቱን ማሳየት የሚፈልገው ፤ ታሪክ አለን፣ የተፃፈ መሆን የለበትም። በማንኛውም መንገድ ሊሆን ይችላል፣ ማስቀጠል አለብን።

https://l.facebook.com/l.php?u=https%3A%2F%2Fbbc.in%2F33HtM4x%3Ffbclid%3DIwAR0-JEMtl0wSezzxdOzL3zPSoHC6Ptn6RhyzsbQfSc3cmjjGMIkTIZtw-P0&h=AT33ZIdc3_I5sFinulVpn2wac054-Ifcjz6brf_nxprdz8V6zFYdepQ5jsyyRs2xPg7RXnEFIc8uvlYs3gfkvVNbaM_np3Y1cqlmpOfJs-G8gwbOJ3UcjLn6FMqTmExdrQ&tn=-UK-R&c[0]=AT1YWGF_RTaS2-gpEBG1G0yMy9beCqfLNYTfWwPXybXEeu3zQ-6ltnri6JN_Flhy3VOd96VJotgonHsvH_ujhGl2tsF8oz1yXNjva0im_Cs-QWMgca_dJ8qi1bUbHTZPeaLw-us4Cs36LvlShNFp-TOm9agBXmOHL5Kn54asR88u98VhHeJmMCsMys1XECw

ለቡከር ሽልማት የታጨችው ኢትዮጵያዊ-አሜሪካዊቷ ደራሲ መዓዛ መንግስቴ - BBC News አማርኛ