October 11, 2020

የሰላም ጥሪ የጊዜ የሁኔታ እና የምክንያት አጥር የለውም! – ሙፈሪሃት ካሚል አህመድ–የሰው ልጆችን ቆዳ ቀለም ወይንም ቋንቋ እንዲሁም አመለካከት ሳይገድባቸው አንድ ከሚያደርጉ ቋንቋዎች ውስጥ ሰላም አንዱ ነው፡፡የሰላም ፍላጎት ከእያንዳንዳችን ውስጣዊ ግፊት የሚመነጭ ፤ ተፈጥሮ በውስጠ ልቦናችን ያጎናፀፈን ከራሳችንም ከአካባቢያችን እና ከተፈጥሮ ሁሉ ጋር በሰላም በተግባቦት እና በተዋደደ ሁኔታ የመኖር ስነልቦና ነው፡፡–

ሰላምን መፈለግ ማለት ሰው ከራሱ ጋር መስማማትን ከውስጡ ጋር መናበብን ወደ እውነተኛ ፍጥረቱ መመለስን የሚያመለከትን ጉዳይ ነው፡፡–ለዚህ ነው የሰላም ጥሪ የጊዜና የሁኔታ ገደብ የለውም የምንለው፤ ሰዎች በሞት ጣር፤በተፋፋመ እና ብዙ እልቂት ባለበት ግጭት ውስጥ ገብተው እንኳን የሰላም ጥሪን የሚሰሙበትና የተኩስ አቁም (cease fire) የሚያደርጉት ፤ከዚህ ወገን እንዲህ ጉዳት ደርሷል ከዚህ እንዲህ ጎሏል ሳይባል፤ መጀመርያ ሰላም በሚል እሳቤ ነው፡፡ ሰላሙ ራሱ ካሳ ስለሆነ ነው፡፡–ሰላም የሰብአዊነት ጉዳይ ነው፡፡ ሰላም ከራስ አልፎ ስለሌሎች ማሰብ ነው፡፡ ደካሞችን ምስኪኖችን ባላጠፉት የሚቀጡ የዋሆችን ማስተዋል ነው፡፡ ሰላም ከግል አጀንዳዎቻችን ላቅ ላሉ ጉዳዮች መረታትን ፤የግል ውስጣዊ ግፊትን መቋቋምንና ለብዙሃን ጥቅም መቆምን ያመላክታል፡፡–ሰላም ስክነት ነው፡፡ ስክነት ሁለንተናዊ አካታችነት ያለው ለሁሉም አይነት አማራጮች ክፍት የመሆን የሰላም አንዱ ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡ ከገፊ ምክንያቶች በላይ ምቹ ስነልቦና ፤ብስለት ያለው አርቆ የሚያይ፤ ከገታራነት የተላቀቀ፤ ለመግባባት የተግባባ መፍትሄ ፈላጊነት ነው፡፡–በሰላም ውስጥ አሸናፊ እና ተሸናፊ የለውም ፤ ክረት ጡዘትና ፤ስሜት ማጋጋል ወቅታዊና አላፊ ሲሆኑ ውሎ አድሮ ምናልባትም ፀፀት ውስጥ ሊከት የሚችል ነው፡፡ ሰላም የፈጠረ ሁሉ አሸናፊ ነው፡፡ ያጣ ቢመስለው እንኳን ያገኘዉ እሱ ነው፡፡ ትልቁ ስጦታ ሰላም ነውና!–ሰላም የተለየ ድምፀት ነው፡፡ ምናልባትም በሆነ ወቅት ሊሰማ የማይፈለግ፤ አጃቢና አጋፋሪ ላይኖረው የሚችል ድምፅ ፤ ነገር ግን ሰላም የደካማነት ሳይሆን የብርቱነት ፤የተሸናፊነት ሳይሆን የስነልቦና ልእልና መገለጫ ፤የዝቅታ ሳይሆን ከፍ ብሎ ነገሮችን የመቆጣጠር ብቃት ማሳያ ነው፡፡ ሰላም ድንበር ዘሎ (across the border) የሚራመድ ስብእና ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ነው የሰላም ጥሪ የጊዜ የሁኔታ እና የምክንያት አጥር የለውም የምንለው፡፡የሰላም ባለቤት እርስዎ ነዎት!ሰላማዊ ቀን ይሁንልን!

Muferihat Kamil Ahmed

9h  · የሰላም ጥሪ የጊዜ የሁኔታ እና የምክንያት አጥር የለውም!

የሰው ልጆችን ቆዳ ቀለም ወይንም ቋንቋ እንዲሁም አመለካከት ሳይገድባቸው አንድ ከሚያደርጉ ቋንቋዎች ውስጥ ሰላም አንዱ ነው፡፡
የሰላም ፍላጎት ከእያንዳንዳችን ውስጣዊ ግፊት የሚመነጭ ፤ ተፈጥሮ በውስጠ ልቦናችን ያጎናፀፈን ከራሳችንም ከአካባቢያችን እና ከተፈጥሮ ሁሉ ጋር በሰላም በተግባቦት እና በተዋደደ ሁኔታ የመኖር ስነልቦና ነው፡፡
ሰላምን መፈለግ ማለት ሰው ከራሱ ጋር መስማማትን ከውስጡ ጋር መናበብን ወደ እውነተኛ ፍጥረቱ መመለስን የሚያመለከትን ጉዳይ ነው፡፡
ለዚህ ነው የሰላም ጥሪ የጊዜና የሁኔታ ገደብ የለውም የምንለው፤ ሰዎች በሞት ጣር፤በተፋፋመ እና ብዙ እልቂት ባለበት ግጭት ውስጥ ገብተው እንኳን የሰላም ጥሪን የሚሰሙበትና የተኩስ አቁም (cease fire) የሚያደርጉት ፤ከዚህ ወገን እንዲህ ጉዳት ደርሷል ከዚህ እንዲህ ጎሏል ሳይባል፤ መጀመርያ ሰላም በሚል እሳቤ ነው፡፡ ሰላሙ ራሱ ካሳ ስለሆነ ነው፡፡
ሰላም የሰብአዊነት ጉዳይ ነው፡፡ ሰላም ከራስ አልፎ ስለሌሎች ማሰብ ነው፡፡ ደካሞችን ምስኪኖችን ባላጠፉት የሚቀጡ የዋሆችን ማስተዋል ነው፡፡ ሰላም ከግል አጀንዳዎቻችን ላቅ ላሉ ጉዳዮች መረታትን ፤የግል ውስጣዊ ግፊትን መቋቋምንና ለብዙሃን ጥቅም መቆምን ያመላክታል፡፡
ሰላም ስክነት ነው፡፡ ስክነት ሁለንተናዊ አካታችነት ያለው ለሁሉም አይነት አማራጮች ክፍት የመሆን የሰላም አንዱ ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡ ከገፊ ምክንያቶች በላይ ምቹ ስነልቦና ፤ብስለት ያለው አርቆ የሚያይ፤ ከገታራነት የተላቀቀ፤ ለመግባባት የተግባባ መፍትሄ ፈላጊነት ነው፡፡
በሰላም ውስጥ አሸናፊ እና ተሸናፊ የለውም ፤ ክረት ጡዘትና ፤ስሜት ማጋጋል ወቅታዊና አላፊ ሲሆኑ ውሎ አድሮ ምናልባትም ፀፀት ውስጥ ሊከት የሚችል ነው፡፡ ሰላም የፈጠረ ሁሉ አሸናፊ ነው፡፡ ያጣ ቢመስለው እንኳን ያገኘዉ እሱ ነው፡፡ ትልቁ ስጦታ ሰላም ነውና!
ሰላም የተለየ ድምፀት ነው፡፡ ምናልባትም በሆነ ወቅት ሊሰማ የማይፈለግ፤ አጃቢና አጋፋሪ ላይኖረው የሚችል ድምፅ ፤ ነገር ግን ሰላም የደካማነት ሳይሆን የብርቱነት ፤የተሸናፊነት ሳይሆን የስነልቦና ልእልና መገለጫ ፤የዝቅታ ሳይሆን ከፍ ብሎ ነገሮችን የመቆጣጠር ብቃት ማሳያ ነው፡፡ ሰላም ድንበር ዘሎ (across the border) የሚራመድ ስብእና ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ነው የሰላም ጥሪ የጊዜ የሁኔታ እና የምክንያት አጥር የለውም የምንለው፡፡
የሰላም ባለቤት እርስዎ ነዎት!