
39ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ሰበካ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእስ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘእክሱም ወዕጨጌ ተክለሐይማኖት ርዕሰ መንበር ኢትየጵያ ውስጥ ያለው አለመረጋጋት በመመካከር፣ በመነጋገር እንዲፈታ ቤተክርስትያን ጠንክራ መስራት እንደሚጠበቅባት ገልጸዋል፡፡
በተፈጠረው አለመረጋጋት ለተጎዱ ወገኖች በሀገር ውስጥ እና በውጭ ያሉ ህዝበ ክርስትያን ድጋፍ ማድረግ የተሞከረ ቢሆንም ከችግሩ ሰፋት አንፃር በቂ አይደለም ብለዋል፡፡የአምበጣ መንጋ እና በአገሪቱ ያሉት ችግሮችን ከቤተክርስትያን ጋራ በመሆን ማስቆም እንደሚገባም ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ በጉባኤው ላይ ተናግረዋል፡፡
ሥራ አጥነት በመበራከቱ ወጣቶች በውጭ ሀገራት ተሰደው ለህልፈት፣ ለሰብአዊ ጥቃት እንዲሁም ለእስር ቤት መዳረጋቸውን በማንሳት አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተቋማት የሚመለከታቸው አካላትን መንግስት ጨምሮ በስደት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ግፊት ማድረግ እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡
