October 12, 2020 – Konjit Sitotaw

በዛሬው እለት ከዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ አቶ ዳውድ ኢብሳ እና የድሬጅቱ አመራሮች መግለጫ እየሰጡ የነበረ ሲሆን የፌዴራል ፖሊስ መግለጫውን እንዲቋረጥ በማድረግ እሳቸውንና 20 የኦነግ አባላትን ባሉበት እየጠበቃቸውጰነው ሲሉ አቶ በቴ ኡርጌሳ ለአውሎ ሚዲያ ተናገሩ።–የኦነግ ጊዚያዊ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ በቴ ኡርጌሳ አቶ ዳውደ ኢብሳና ጓዶቻቸው በአቶ ዳውድ ኢብሳ መኖሪያ ቤት ስለ ሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች በተለይም ስለ ኦሮሚያ ወቅታዊ ሁኔታና መፍትሔ መግለጫ እየሰጡ የነበረ ሲሆን ፖሊስ መግለጫውን በማቋረጥ በቁጥጥር ስር አውሎ ባሉበት እየጠበቃቸው ነው ሲሉ ነግረውናል።–አቶ በቴ እንደተናገሩት ፖሊስ በኦነግ ልሳን በሆኑት ሁለት የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት መስሪያ ሚዲያዎች የሚያገለግሉ ሶስት ጋዜጠኞችና ሁለት አስተባባሪዎች ፖሊስ ወደ ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ወስዷቸዋል ነው ያሉት።–ጋዜጠኞቹ የአቶ ዳውድ ኢብሳን ንግግር ቀጥታ ሲያስተላልፉ የነበሩ ሲሆን የፌዴራል ፖሊስ መግለጫው ካቋረጠ በሗላ በመኪና ወደ ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ወስዷቸዋል ሲሉ አቶ በቴ ተናግረዋል።–እንደ አቶ በቴ ኡርጌሳ ገለፃ ከሆነ አቶ ዳውድ ኢብሳን ጨምሮ 20 የኦነግ አመራሮች ይህ ዜና እስከ ተጠናከረበት ሰዓት ድረስ በአቶ ዳውድ ኢብሳ መኖሪያ ቤት ውስጥ በፌዴራል ፖሊስ ከበባ ውስጥ ናቸው።
–
አዉሎ ሚዲያ ጥቅምት 2/2013 ዓ.ም
