ብሄራዊመግባባትናእርቅ ለኢትዮጵያ: ጥናታዊጽሁፍ (በተክሉአባተ

በአገራችን ኢትዮጵያ ያለውን ብሄር ገነን ሥርዓት በእውነተኛ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር ለመተካት ኢትዮጵያውያን (የሌላ አገር ዜግነት ያላቸውን ትውልደ ኢትዮጵያውያንንም ማለቴ ነው) የተለያዩ  መንገዶችንና ዘዴዎችን በመጠቀም እየታገሉ ይገኛሉ:: በአገር ቤት ያሉ ወደ 100 የሚጠጉ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በይፋ ሰላማዊ የትግል ስልት ይከተላሉ ቀላል የማይባል ህዝብም በሰላማዊ መንገድ መታገል እንደሚበጅ ያምናል:: በጣት የሚቆጠሩ ድርጅቶች ደግሞ እሾህን በእሾህ እንዲሉ መሳርያ አንስተው ወደበረሃ ገብተዋል:: እንደ ግንቦት 7 ያሉት ደግሞ ሁሉንም አይነት የትግል ስልት መጠቀም አዋጭ እንደሆነ ያምናሉ:: በአንድም በሌላም መንገድ ስለነዚህ የትግል ስልቶች አንጻራዊ አዋጭነትና አስፈላጊነት ውይይቶች ሲደረጉ ነበር:: ነገር ግን የትኛው የትግል ስልት ትክክለኛ ለውጥ ለማምጣት አስተማማኝ እንደሆነ መደምደም የሚቻል አይመስልም:: ለዚህም ይመስላል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማኅበራዊ ሚዲያዎችና በድረ ገጾች የሚደረጉ ውይይቶችና የሚለቀቁ መጣጥፎች ይህን ጉዳይ በቀጥታ የማያነሱት::

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በርከት ያሉ ውይይቶችና መጣጥፎች እያተኮሩበት የመጣው ጉዳይ ትንሽ የተለዬ ይመስላል:: ብሄራዊ መግባባትና እርቅ ማድረግ ለአገራችን ሰላማዊና ዘለቄታዊ ለውጥ ማምጣት እንደሚችል እየተነገረ ነው:: ብሄራዊ መግባባትና እርቅ ማድረግ ከባህላችን ጋር አብሮ ከመሄዱም በላይ እጅግ አስፈላጊና ወቅታዊም እንደሆነ የሚሞግቱ አሉ:: በአንጻሩ ደግሞ ብሄራዊ እርቅ ፈጽሞ የማይሰራ ከመሆኑም በላይ የህግንና ፍትህን መርሆች የሚቃወም እንደሆነ የሚያስጠነቅቁም አሉ:: አንዳንዶች ደግሞ ስለብሄራዊ መግባባትና እርቅ ማውራትና መወያየት የዋህነት አላዋቂነት ሃይማኖታዊነት እንደሆነ በድፍረት ይናገራሉ:: ሌሎች ደግሞ ሃሳቡ መንግስትና ባለሥልጣናቱን ለመታደግ የታሰበ የቆረጣ ስልት እንደሆ ይጠቁማሉ::

ዳሩ ግን ብሄራዊ ኢትዮጵያዊ መግባባትና እርቅን በተመለከተ ጠቅለል ያለ የዳሰሳ ጥናት እስካሁን አልቀረበም:: ጉዳዩን በተመለከተ የሚደረጉት የተናጥል ውይይቶችና የተጻፉት መጣጥፎች የተሟላ ሃሳብ ለማግኘት አያስችሉም:: እንዲያውም በጉዳዩ ላይ ምን ያህል እንደተጻፈና ምን ምን ዝርዝር ሃሳቦች እንደተነሱ አይታወቅም:: ይህም ብሄራዊ መግባባትና እርቅ በይፋ እንደ አንድ የትግል ስልት እንዳይቆጠርና በጽንሰ ሃሳብ ደረጃ ዳብሮ ሥራ ላይ እንዳይውል ተጽእኖ  አሳድሯል:: ይህን ችግር ለመቅረፍ የዳሰሳ ጥናት አስፈላጊ ሆኗል:: የዚህ ጥናታዊ ጽሁፍ ዓላማ ጉዳዩን በተመለከተ የተጻፉትን መሠረት በማድረግ አጠቃላይ ግንዛቤ እንዲኖርና በርዕሱ ላይ ውይይት ተጠናክሮ  እንዲቀጥል ማነሳሳት ነው::

የጥናቱዓላማ የዚህ ጥናት ዋና ዋና ዓላማዎች ቀጥለው የተዘረዘሩት ናቸው::

  1. እስካሁን ድረስ ስለብሄራዊ (ኢትዮጵያዊ) መግባባትና እርቅ  በጽንሰ ሃሳብ ደረጃ ምን እንደተጻፈ መመርመር
  2. ብሄራዊ መግባባትና እርቅን በተመለከተ በሚገባ ያልተብራሩ ሃሳቦችን ለይቶ ማውጣት
  3. ብሄራዊ መግባባትና እርቅን በተመለከተ ወደፊት በጽንሰ ሃሳብና በተግባር ደረጃ ምን መደረግ እንዳለበት መጠቆም

የጥናቱዘዴና የመረጃ ምንጮች

በእርግጥበድረገጾችበፌስቡክበፓልቶክክፍሎችእንዲሁምበቴሌቪዥንናበሬዲዮፕሮግራሞችጉዳዩን (ብሄራዊመግባባትናእርቅን)የተመለከቱውይይቶችተካሂደውይሆናል::ለዚህጥናትእነዚህንሁሉየመረጃምንጮችማካተቱጊዜወሳጅመሆኑ ታምኖበታል::በመሆኑምከላይየተዘረዘሩትንየጥናቱንዓላማዎችለማሳካትበዋናዋናድረገጾችየታተሙመጣጥፎችንመመልከትጠቃሚናጊዜቆጣቢሆኖተገኝቷል::አንድምየተቀናጀጽሁፍበድረገጾችማውጣትየተለመደነውና:: በመሆኑምይህጥናትአራትዋናዋናድረገጾችንበመረጃምንጭነትተጠቅሟል::እነሱም ECADF Ethiomedia Ethiopian Review እና Zehabesha ናቸው::እነዚህድረገጾችበኢትዮጵያዊያንዘንድበደንብየሚታወቁናፖለቲካዊማኅበራውባህላዊሃይማኖታዊምጣኔሃብታዊናሌሎችንምጉዳዮችያካተቱበርካታናጠቃሚጽሁፎችየሚታተሙባቸውናቸው::በአጠቃላይሲታይእነዚህድረገጾችስለብሄራዊመግባባትናእርቅበቂመጣጥፎችን እንደሚያትሙይገመታል::   በተመረጡት አራት ድረ ገጾችም የተጻፈውን ሁሉ አንድ በአንድ መፈተሽ አሰልቺና ጊዜ ወሳጅ ከመሆኑም በላይ አላስፈላጊም ነው:: በመሆኑም የእያንዳንዱን ድረ ገጽ የመፈለጊያ ሳጥን Search box በመጠቀም በጉዳዩ ላይ የተጻፉትን መጣጥፎች በቀላሉ ማግኘት ይቻላል:: ቀጥለው የተዘረዘሩትን የአማርኛና የእንግሊዝኛ የመፈለጊያ ቃላት ወይም ቁልፎች keywords በመጠቀም አራቱም ድረ ገጾች ተፈትሸዋል::

በሌሎችድረገጾችጉዳዩንበተመለተመጣጥፎችታትመውስለሚሆን Googleንበመጠቀምተጨማሪ ፍለጋተካሂዷል::ይህንምለማድረግከላይየተዘረዘሩትንየአማርኛናየእንግሊዝኛ  የመፈለጊያቃላትንተጠቅሜአለሁ::በአጠቃላይሲታይአራቱድረገጾችበርካታበብሄራዊመግባባትናእርቅላይየተጻፉትንይዘውተገኝተዋል::ዳሩግንበፍለጋውያልተገኙጥቂትመጣጥፎችሊኖሩይችሉይሆናል::የጥናቱ ዋና ዓላማ ስንት እንደታተመ መቁጠር ሳይሆን ምን እንደተባለ መመርመር ስለሆነ ይህ ብዙም አያሳስብም:: ለአንባቢግልጽመሆንያለበትሌላ ጉዳይቢኖርይህጥናታዊጽሁፍየሚያተኩረውየድኅረ 97 ምርጫጊዜንነው::ይህጥናትምርጫውንተከትሎየነበሩትንየእርቅሙከራዎችአያጠቃልልም:: ምንም እንኳን ከዚህ ውጭ የጊዜ ገደብ ባይደረግም በርዕሱ ላይ የተጻፉት ጽሁፎች ለንባብ የበቁት ከ2010 ጀምሮ መሆኑን ግንዛቤ ወስጃለሁ:: የጥናቱ ዋና ዋና ግኝቶች ቀጥለው ቀርበዋል::

የጥናቱግኝቶች  

በአጠቃላይሲታይ ብሄራዊመግባባትናእርቅንበተመለከተ 18 ጽሁፎችከ2010 እስከ 2014 ታትመዋል::ከዚህ ውስጥ ግማሽያህሉበ2014 ብቻ የታተሙናቸው::አብዛኞቹ (14ቱ)በ2013 እናበ2014 የተጻፉናቸው::ሰባቱበአማርኛሲጻፉቀሪዎቹ 11ዱደግሞበእንግሊዝኛተጽፈዋል::የ16ቱመጣጥፎችአርእስትናሙሉይዘታቸውብሄራዊመግባባትናእርቅሲሆንቀሪዎቹሁለቱየተጻፉትግንበሌላርዕሰጉዳይላይነው::ቢሆንምግንብሄራዊመግባባትናእርቅከተነሱትአበይትጉዳዮችውስጥይጠቀሳል::አብዛኞቹ መጣጥፎችን ያቀረቡት ብዙውን ጊዜ በተለያዪ ሚዲያዎች የሚታወቁ ኢትዮጵያውያን ፕሮፈሰሮች ወይም ዶክተሮች ናቸው:: ሁሉምጽሁፎችከዚህጽሁፍመጨረሻላይበጸሃፍትስምበታተሙበትዓመትበርዕሳቸውናጽሁፎችበታተሙባቸውድረገጾችተዘርዝረውይገኛሉአንባቢያን ጸሃፍትን በቀላሉ ይለዩአቸው ወይም ያውቋቸው ዘንድ ሙሉ ስማቸውን በቅንፍ ውስጥ ጠቅሻለሁ:: አንድጽሁፍበተለያዩ  ድረገጾችታትሞቢገኝምይህጥናታዊ ጽሁፍግንመጀመሪያየተገኘበትንድረገጽብቻይጠቅሳል::

ምንምእንኳንሁሉምጽሁፎችብሄራዊውይይትመግባባትናእርቅዋናጉዳያቸውቢሆንምበዝርዝርያተኮሩባቸውጉዳዮችእንዲሁምየሰጧቸውየመፍትሄሃሳቦችግን የተለያዩናቸው::በአጠቃላይ ሲታይ ግንየሚከተሉትጉዳዮችበተለያዩጽሁፎችተዳሰዋል::

እነዚህንጉዳዮችበተመለከተየተገኙት 18ቱመጣጥፎችምንእንዳስቀመጡቀጥሎ በአጭሩቀርቧል:: በቅንፍ የተመለከቱት የጸሃፍት ስምና መጣጥፎች የታተሙበት ዓመታት ናቸው:: ይህ ጽሁፍ የሚያተኩረው በዋናና ጠቅላላ ሃሳቦች ዙሪያ ስለሆነ ዝርዝር ጉዳዮችን ለመረዳት በአባሪ መልክ የተያያዙትን 18ቱን ጽሁፎች ማንበብ ይጠቅማል:: እንደገና የማሳስበው ጉዳይ ቢኖር 18ቱም ጽሁፎች ሁሉንም ከላይ የተዘረዘሩትን ንዑስ ጉዳዮች እንዳላተቱ ነው::

የብሄራዊ እርቅ አስፈላጊነትና ጥቅም

ሁሉም ጽሁፎች ብሄራዊ መግባባትና እርቅ እጅግ ተፈላጊ የሆኑ ማኅበራዊ እሴቶችን ለመመስረትና ለማጽናት ወሳኝ እንደሆነ ያስገነዝባሉ:: እንዲሁም ከሌሎች የትግል ስልቶች አግባብነትና አተገባበር ጋር ብሄራዊ እርቅን ያወዳድራሉ ያነጻጽራሉ::  አብዛኞቹ ጽሁፎች ብሄራዊ እርቅ የሚያስፈልገው ኢትዮጵያ ያለችበት ዘርፈ ብዙ ችግር ተባብሶ ወደ ከባድ ቀውስ እንዳትገባ ስለሚያደርግ እንደሆነ ያትታሉ:: ያሉትን ችግሮች በህዝባዊ አመጽም ሆነ በጦርነት ለመፍታት አስቸጋሪ ከመሆኑም በላይ ተያይዞ ሊመጣ የሚችለው ቀውስ በቶሎ ማቆሚያ ሊኖረው እንደማይችል የብዙ አገሮችን ተሞክሮ በማንሳት ብዙዎች ያስጠነቅቃሉ:: ለምሳሌ ያህል ጥቂት ስለብሄራዊ እርቅ ጥቅም ወይም አስፈላጊነት የተሰጡት ማሳመኛዎች ቀጥለው ቀርበዋል::

2013/2014)

 

የሚታረቀው ማንነው?  

ይህን ጉዳይ በተመለከተ በቂ ትንተና አልተሰጠበትም:: ጠቅለል ያሉና ግልጽነት የጎደላቸው ሃሳቦች ግን ተቀምጠዋል:: ከአብዛኞቹ ጽሁፎች ጀርባ ተቀምጠው የሚገኙት ነጥቦች እንደሚያመላክቱት ከሆነ እርቅ የሚደረገው ወይም መደረግ ያለበት በመንግስትና በህዝቡ መካከል ነው:: መንግስት በዳይና ህዝብ ተበዳይ ስለሆኑ የሁለቱ መወያየት መግባባትና መታረቅ ወሳኝ እንደሆነ ያብራራሉ:: እንዲሁም አንዱ ህዝብ ወይም ብሄር ከሌላው ጋር በጥርጣሬና በመፈራራት ስለሚኖር መታረቅ እንዳለበትም የሚጠቁሙ አሉ:: በተጨማሪም መግባባትና እርቅ በግለሰቦች መካከል ያለውን ያልጠራ ስሜትም ለማከም ማገልገል እንዳለበት የጠቆሙ አሉ (አኢጋን 2014):: ከዚህ ባለፈ ግን ጉዳዩን ብትንትን አድርጎ ያስቀመጠ ጽሁፍ የለም:: አንዳንዶች (ለምሳሌ ያዕቆብኃይለማርያም 2014) ማንከማንተጣላና ነው እርቅ የሚያስፈልገውብሎመቀለድዋጋእንደሚያስከፍል ሲያስጠነቅቁ ሌሎች (ለምሳሌ ቴዎድሮስ ኪሮስ 2014; ተክሉ አባተ 2014 )ደግሞ በደፈናው በእርቁ መሳተፍ ያለባቸው ተቃዋሚኃይሎችናድምጹንያጠፋውአብዛኛውኢትዮጵያዊ እንዲሁም የፖለቲካእስረኞች መሆን እንዳለባቸው ይጠቁማሉ:: አኢጋን ደግሞ የመጀመሪያ ደረጃ እርቅ የሚያስፈልገው በዘር በቋንቋ በሃይማኖትና በፖለቲካ በሚለያዩ ቡድኖች መካከል ሲሆን ከዚያ ቀጥሎ ብሄራዊ እርቅ መደረግ እንዳለበት ይጠቁማል:: በአጠቃላይ ሲታይ እርቅ የሚያስፈልገው በህዝብና በመንግስት መካከል ብቻ ሳይሆን ወረድ ብሎም በየደረጃው መከናወን እንዳለበት ጽሁፎች ጠቁመዋል:: ይሁን እንጅ መንግስትና ህዝብ ዋናዎቹ እርቅ የሚያስፈልጋቸው አካላት እንደሆኑ ሁሉም ጽሁፎች ያመላክታሉ::       

እርቁን ማንያስተባብረው? 

ብሄራዊ እርቁን ማን ማስተባበር እንደሚገባው ግልጽ የሆኑ ሦስት ዋና ዋና አማራጮች ተቀምጠዋል:: አንድ እርቁን መጀመርና ማስተባበር ያለበት መንግስት እንደሆነ ያተቱ አሉ (ለምሳሌ ዘላለም እሸቴ 2014; መሳይ ከበደ 2013/2014 እና ገላውዲዎስ አርአያ 2010):: ፍላጎትና ዝግጁነት ካለው መንግስት ካለበት ብሄራዊ ኃላፊነትና ካለው አቅም አኳያ ይህን የማስተባበር ሥራ ቢወስድ እንደማይከብደው ይገመታል:: ሁለት እርቁን መምራት ያለባቸው  ተቃዋሚየፖለቲካ ፓርቲዎች ናቸው የሚሉም አሉ (ለምሳሌ ዋለልኝመኮንን 2012እና ቴዎድሮስኪሮስ 2014):: ይህ አማራጭ ከፖለቲካው ሜዳ በመንግስት እየተገፉ ያሉት ኃይሎች ሂደቱን እንዲመሩት ያመቻቻል:: ሦስት መንግስትና ተቃዋሚየፖለቲካ ፓርቲዎች ዋና የእርቁ አካል ስለሆኑና በዳይና ተበዳይም ስለሆኑ ነጻና ገለልተኛ ኢትዮጵያውያንን ያቀፈ አስታራቂ ግብረ ኃይል የእርቁን ሂደት መምራት አለበት የሚሉም አሉ (ለምሳሌ ተክሉ አባተ 2013 2014)::

ከነዚህ አማራጮች ለየት ያሉም አሉ:: ሁሉን አቀፍ የምክክር ጉባዔ እንዲጠራ ያሳሰቡም አሉ (ሰሎሞን ታረከኝ 2011):: መገናኛ ብዙኅን አስተዋጽዖ ማድረግ እንደሚችሉ ቢጠቀስም ሂደቱን ማን እንደሚመራውና እንደሚጀምረው ግን ግልጽ አይደለም:: እንዲሁም ወጣቱ ትውልድ ወደብሄራዊ እርቅ የሚያደርሰውን ውይይትና ምክክር በበላይነትና በባለቤትነት መምራት እንዳለበት ያሳሰቡ አሉ (አለማዬሁገብረ ማርያም 2012):: የተማረው ወጣቱ ትውልድ የትናንቱ ትውልድ ከሚዳክርበት የግራና የቀኝ የፖለቲካ አመለካከት ነጻ ሆኖ የእርቁን ሂደት ቢመራው እጅግ እንደሚሻል ተጠቁሟል:: ይህ እንዴት መካሄድ እንዳለበትም የመነሻ ሃሳቦች ተሰጥተዋል::

እርቅ እንዴት ይካሄድ?  

ብሄራዊ መግባብትና እርቅ እንዴት መካሄድ እንዳለበት በርከት ያሉ ትንተናዎች ተሰጥተዋል:: ብዙዎች (ለምሳሌ ተክሉ አባተ 2014; ዘላለም እሸቴ 2014; ሰሎሞን ታረከኝ 2011; አለማዬሁ ገብረ ማርያም 2012; ገላውዲዎስ አርአያ 2010) ከእርቅ በፊት ቀጣይነት ያላቸውና ሁሉን አቀፍ ክርክሮችና ውይይቶች መካሄድ እንዳለባቸው ጠቁመዋል:: ብሄራዊ ክርክሮችና ውይይቶች መንግስትናተቃዎሚድርጅቶችንበእኩልነትየሚያስተናግዱ: የእያንዳንዳቸውንጠንካራናደካማጎንመለየት የሚያስችሉ: እንዲሁም በእውነት ላይ የተመረኮዙ መሆን እንዳለባቸው ተጠቁሟል:: ሌሎች ስለእርቅ ሂደት የተዘረዘሩ ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው::

ብሄራዊ መግባባትና እርቅ በሚጀመርበት ጊዜ የፍትህ አገሯ ወዴት ይሆናል? ይህ ጥያቄ ከኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ አኳያ በቂ መልስ ያገኘ አይመስልም:: ከ18ቱ መጣጥፎች ውስጥ ሦስት የሚሆኑት ብቻ ይህን ጉዳይ በግልጽ አንስተዋል:: በጣም  ለተበደሉ ወገኖች ፍትህ (ለምሳሌ ካሳ) መደረግ እንዳለበት ጠቆም ያደረጉ አሉ (ያዬህ አበበ 2014; አኢጋን 2014):: በጣም የተበደሉት ወገኖች እነማን እንደሆኑና ምን አይነት ካሳ በማን መሰጠት እንዳለበት ግን የተብራራ ነገር የለም:: ከሁሉም ጽሁፎች ገለታው ዘለቀ (2014 ገጽ 4)የጻፉት የእርቅና የፍትህ ግንኙነት እጅግ በተሻለ መልኩ እንደሚከተለው ያብራራል:: ዋናው መልእክት እርቅ በሚደረግበት ጊዜ እንደአስፈላጊነቱ ፍትህም ሥራ ላይ ሊውልበት የሚችል እድል እንዳለ ያመላክታል:: የእርቅና የፍትህ ውሳኔዎች በአንድ ላይ ተጣጥመው መሄድ እንደሚችሉ ባህላችንን በምሳሌነት እያነሳ ይተነትናል::

በስምምነትላይየተመሰረተባህላዊውህደትብሄራዊእርቅንበኢትዮጵያየሚያየውእንደዚህነው።በዚህጽንሰሃሳብመሰረትብሄራዊ እርቁሪስቶሬቲቭጀስቲስንመሰረትያደረገናበሚያድግዴሞክራሲችግሮችንሊፈታየሚችልስምምነትማለትነው።ይህማለትግን ሪትሪቢዩቲቭጀስቲስቦታየለውምማለትኣይደለም።በኣሁኑሰዓትበከፍተኛሙስናናከፍተኛወንጀልእየፈጸሙያሉሰዎችይህንን ኣሳባችንንእያዩእንደጅልነትኣይተውከስልጣንእስኪወርዱበግፋቸውእንዲቀጥሉበርኣይከፍትም። የብሄራዊእርቅሰነዱእንደነዚህኣይነትሰዎችንበቡድንእያየሳይሆንበግለሰብደረጃወደፍርድሊያመጣቸውመቻሉኣያጠያይቅም። እንደቡድንእንደሃገርኢኮኖሚያዊችግሮቻችንንዝግእያለሊሰራጭበሚችልየሪዲስትሪቢዩሽንዘዴተመጣጣኝእድገትለማምጣት መስማማት፣ፖለቲካዊተሳትፎንከባህላዊውህደትስምምነትኣንጻርኣይቶከብሄርፖለቲካኣውጥቶበኣንድብሄራዊማንነትስር ለመገንባትመስማማት፣ዋናየሃገሪቱንቋንቋዎችንቁጥርመጨመርኣጠቃላይፈውስንለማምጣትይጠቅማል። ኢትዮጵያሪስቶሬቲቭጀስቲስላይእንድታተኩርየሚያደርጋትለዘላቂሰላምናልማትኣንድነትየሚረዳትሲሆንይህየፍትህኣሰጣጥዘዴ በኢትዮጵያቡድኖችዘንድየተባረከናየሚበረታታነው።የኦሮሞስርዓትንብናይለሪስቶሬቲቭጀስቲስትልቅቦታኣለው።ይቅርማለትን፣ በዳዩንከመቅጣትይልቅተበዳዩንመካስንያበረታታል።ኣማራውኣካባቢያለውንየሽምግልናስርዓትስናይበኣብዛኛውሪስቶሬቲቭ ጀስቲስ የሚበረታታበት ሁኔታ ኣለ። በደቡብ፣ በምስራቅ በተለይም በሶማሌ ክልል ይህ የፍትህ ስርዓት ከፍተኛ ተጽእኖ ኣለው ገለታው  

የማጠቃለያሃሳቦች

ይህጥናትብሄራዊ መግባባትና እርቅን በተመለከተ በርካታ ጠቅለል ያሉ ጉዳዮችን ዳሷል:: ዝርዝር ትንተናዎችን ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት መጣጥፎች ማግኘት ይቻላል:: ለማጠቃለል ያህል ግን ጥቂት ነጥቦችን ማንሳት ያስፈልጋል::

አንደኛ ምንም እንኳን የተዳሰሱት 18ቱ መጣጥፎች የብሄራዊ መግባባትና እርቅን ጠቀሜታና አስፈላጊነት ከሌሎች የትግል ስልቶች ጋር በማነጻጸርና በማወዳደር ለማቅረብ መሞከራቸው ክፉ ባይሆንም ጉዳዩን በሌላ መነጽር መመልከቱ ይበልጥ ጠቃሚ ነው:: ብሄራዊ መግባባትና እርቅ ተጀምሮ የተወሰነ አጓጊ ደረጃ እስኪደርስ ድረስ ሌሎችን ትግሎች ማቆም ላያስፈልግ ይችላል:: ሌሎች ትግሎች (ለምሳሌ የተቀናጀና ደረጃ በደረጃ የሚመራ ህዝባዊ እምቢተኝነት http://tekluabate.blogspot.no/2014/08/blogpost_6.html#more) ምናልባትም መንግስት የእርቁን ጉዳይ በሚገባ እንዲያጤነው ሊያስገድዱት ይችላሉ:: በመሆኑም የእርቅን ጠቀሜታ ለማውሳት ሌሎች ትግሎችን ማኮሰስ የግድ አይጠበቅም::

ሁለተኛ የተወሰኑ ጽሁፎች ህዝብ ለህዝብ መታረቅ እንዳለበት አሳስበዋል:: ምንም እንኳን ሃሳቡ በራሱ ክፉ ባይሆንም ለበርካታ ችግሮች ሁሉ ተጠያቂ የሆነውን አካል ማለትም መንግስትን ላላ አርገን እንድንይዝ የሚጋብዝ :: በመጀመሪያ ደረጃ ህዝብ ለህዝብ ሊጣላ አይችልም:: ከበስተጀርባ ያሉ ተንኳሽ የመንግስት ፖሊሲዎችና ፕሮፓጋንዳዎች የህዝብን ልብ ይከፍላሉ:: መንግስት ከትንኮሳው ሁሉ ታቅቦ ህዝቦች በሰላምና በአንድነት እንዲኖሩ ቢሰራ በአጭር ጊዜ ውስጥ የነበረን መከባበርና መተሳሰብ ይመለሳል:: ስለዚህ መታረቅ ያለበት መንግስ ከህዝብ ጋር ነው ብዬ አምናለሁ::

ሦስተኛ መንግስትም ሆነ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች እውነተኛ እርቅን ጀምረው ማስተባበር ይችላሉ ማለት ዘበት ነው:: መንግስት እንደግለሰብ ቂመኛ በቀለኛና ትምክህተኛም ነው:: ለተቃዋሚዎች ያለው ንቀትና ጥርጣሬ መጠን የለውም:: እርቅን እሱ ቢጀምር የመሸነፍና የመዋረድ ያህል ይመለከተዋል:: ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ቢሆኑ ከመንግስት ጋር ያላቸው ቅራኔ እርቅ ለመጠየቅ የሚያበቃ አይመስልም:: ሰጥቶ የመቀበልና የማሳመን ችሎታና ፍላጎት እስካሁን አላየንም:: በመሆኑም ሌላ ገለልተኛና አንጻራዊ በሆነ መልኩ ንጹህ ኢትዮጵያውያን የተሰባሰቡበት አካል ያስፈልጋል:: ይህን አካል የሚያቋቁመው አካል: የሚቋቋምበት መስፈርት: የሚኖረው ዝርዝር የሥራ ድርሻ: የሚጠቀማቸው ዘዴዎች: ወዘተ ግን ጥርት ብለው ለውይይት ቢቀርቡ የተመረጠ ነው እላለሁ:: እንዲሁም ፍትህና እርቅ ምን ያህል የሚዛመዱና የሚቃረኑ እንደሆነ የኢትዮጵያን ተጨባጭ ሁኔታዎች ግምት ውስጥ በማስገባት አስቀድሞ መተንተን ያስፈልጋል::

በአጠቃላይ ይህ አስተባባሪ ኃይል ከእርቅ በፊት በእርቅ ጊዜና ከእርቅ በኋላ ሊሟሉ የሚገባቸውን ሁኔታዎች እጅግ በዝርዝር አዘጋጅቶ ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ አቅርቦና በውይይት አዳብሮ ሊንቀሳቀስ ይገባል:: ይህ ቀላል ሥራ ስላልሆነ የሚመረጡት ሰዎች ስሜታቸውን የሚቆጣጠሩና የሞራል ብስለት ያላቸው: አዋቂዎችና አስተዋዮች: እንዲሁም የመግባባትና ጫናን የመቋቋም አቅም ያላቸው ሊሆን ይገባል:: ልዩ ልዩ አይነት መስዋዕትም ለመክፈል የተዘጋጁ መሆን አለባቸው:: በመሆኑም ብሄራዊ መግባባትና እርቅ በብርቱ ልፋትና መከራ የሚመጣ እንጅ እንደሚታሰበው ‘ሰላማዊ’ ብቻ ላይሆን ይችላል::

የመጀመሪያው ችግር የሚሆነው ይህን አስታራቂ ኃይል ማቋቋም ነው:: ማን ነው ይህን ሊያነሳሳው የሚችለው? በተለያዩ  አካላትስ ተቀባይነት ይኖረዋል? ፍላጎትና ለኢትዮጵያ መልካም ራእይ ያለው ማንኛውም አካል ሊጀምረው ይችላል:: ቢያንስ ቢያንስ ይህ ጥናታዊ ጽሁፍ የገመገማቸውን 18ቱን በብሄራዊ መግባባትና እርቅ ላይ ያተኮሩ መጣጥፎችን ያቀረቡት ምሁራን በመመካከር ለጉዳዩ የሚሆን መሪ ሃሳብ roadmap ማዘጋጀትና ለውይይት ማቅረብ ይችላሉ:: ጥናቱን በማካሂድበትጊዜየታዘብኩትናወደፊትትኩረትሊሰጠውየሚገባውጉዳይግን አለ::ሁሉምመጣጥፎችራሳቸውንየቻሉናሌላውንለድጋፍምይሁንለትችትበፍጹምየማይጠቅሱናቸው::ስለአንድጉዳይበሚጽፉሰዎችመካከልምንምአይነት ‘መናበብ’እንደሌለአመላካችነው:: ሁሉምየግልሩጫውንተያይዞታል::ይህን አቁመን በአንድ ጉዳይ ላይ የምንጽፍ ሰዎች መናበብ ብንጀምርና የመነሻ ሃሳብ ብናቀርብ ብሄራዊ ግዴታችንን እንደመወጣት ይቆጠራል:: የያዘውን የወረወረ ፈሪ አይባልም!!! ሰላም አንድነትና ብልጽግና ለኢትዮጵያ!

///////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////////

ገንቢ አስተያየት ወይም ጥያቄ ካለዎት በteklu.abate@gmail.com ይላኩ!

ስለብሄራዊእርቅየተጻፉጽሁፎች 

በአማርኛየተጻፉ 

http://www.ethiomedia.com/14store/gojjee_bahlochachin_final_part.pdf

በእንግሊዝኛየተጻፉ

http://ethiomedia.com/2012_report/4559.html

http://ecadforum.com/2011/01/20/acallforanationalconferencetosaveethiopia/ 

http://www.zehabesha.com/inclusivediscourseapreludetonationalreconciliation/§Teodros Kiros 2014 Reconciliation is the language of communicative rationality.  http://www.africanidea.org/reconcilation_kiros.html 

http://www.zehabesha.com/ethiopiacallforoppositiongovernment/

http://www.zehabesha.com/ethiopiareconciliationpyramidzelalemeshetephd/