16/10/2020
ስለ ጋዜጠኛው ከውቅያኖሱ በሻይ ማንኪያ!
……ዳንኤል ሽበሺ
ጋዜጠኛ ተመስገን ቢታሰርም ባይታሰርም ነፃ ሰው ። ቀድሞ ለሀገሩ የሞተ በድን ነውና ። ስለ ነፃነት እናውራ ካልን ደሞ ነፃነት ከውስጥ የሚፈልቅ እንጂ ከውጭ የሚጫን ሶፍትዌር አይደለም ።በእነሱ ቋንቋ ጋዜጠኛው አንድ ብጫ ካርድ ተሰጥቶታል ። ከዚህ በኋላ አንድ ብጫ ካርድ ይቀረዋል ። ሁለት ብጫ ቅጣት ካርድ አንድ ቀይ የቅጣት ካርድ ብዬ ነው። ዞሮ ዞሮ ተሜ Black list ውስጥ መግባቱን መጠርጠር ጠርጣራነት ነው ።ብጫዎቹም ሆነ ቀያዩ ካርዶች ለእሱ እንደ ወርቅ ሜዳሊያ Golden Medals ሽልማት ናቸው ። የማይታጠፉ ክንዶች የማይደርቅ ቀለማት የማይሸራረፍ ብዕረኛ የማይፋቁ ቀለማትን እየተፋ ከሐቅ ጋር እየተጋፈጠ ይቀጥላል። #ሰው ማለት እውነቱን ተናግሮ ፣ የተሸፋፈነውን ገልጦ፣ በትንተና አሳምኖ በመሸበት የሚያድር ነው ። ጋዜጠኛ ስንል ሰው ማለታችን መሆኑ መቸስ አይጠፋብንም ።በቅን ልቦና ለሀገራቸውና ለሐቅ የቆሙ ሁሉ በፈጣሪና በሕዝብ ልብ ውስጥ ለዘለዓለም ይኖራሉ ። አንረሳችሁም !!!