አማራ ሚዲያ ማዕከል / Amara Media Center

ጥቅምት 7 ቀን 2013 ዓ.ም

አዲስ አበባ ሸዋ

በዚህ መሰረት ተቋማቱን በአምስት የትኩረት መስኮች የተለዩ ሲሆን፥ በዚህም የምርምር፣ አጠቃላይ፣ የአፕላይድ ሳይንስ፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ እና የቴክኒካል ዩኒቨርስቲዎች ተብለው ተለይተዋል።በምርምር ዩኒቨርስቲነተ የተመደቡ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም፥ አዲስ አበባ፣ አርባ ምንጭ፣ ባህርዳር፣ ጎንደር፣ ሀረማያ፣ ሀዋሳ፣ ጅማ እና መቐለ ናቸው።አክሱም፣ አምቦ፣ አርሲ፣ አሶሳ፣ ደብረ ብርሃን፣ ደብረ ማርቆስ፣ ዲላ፣ ድሬዳዋ፣ ጅግጅጋ፣ ኮተቤ፣ ሰመራ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ወልቂጤ፣ ወለጋ እና ወሎ ዩኒቨርስቲ የአፕላይድ ዩኒቨርስቲዎች ተብለዋል።አዲግራት፣ ቦንጋ፣ ቦረና፣ ቡሌ ሆራ፣ ደባርቅ፣ ደብረ ታቦር፣ ድምቢ ዶሎ፣ ጋምቤላ፣ እንጅባራ፣ ጂንካ፣ ቀብሪ ደሃር፣ መዳ ወላቡ፣ መቅደላ አምባ፣ መቱ፣ ሚዛን ቴፒ፣ ኦዳ ቡልቱም፣ ራያ፣ ሰላሌ፣ ዋቸሞ፣ ወራቤ እና ወልዲያ ዩኒቨትስቲዎች ደግሞ አጠቃላይ ዩኒቨርስቲዎች ሆነዋል።የአዳማ ሳይንስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲነት ተለይተዋል።በቴክኒካል ዩኒቨርስቲ ስር ደግሞ የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተመድቧል።ይህንን ውሳኔ ለማሳለፍ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የሌሎች ሀገራትን ተሞክሮ መሰረት በማድረግ ጥናቱ ስለመደረጉም ተነስቷል።ይህንንም የልየታ ምክረ ሃሳብ ተግባራዊ ለማድረግ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማድረግ እንደሆንም ተጠቁሟል።ዘገባው የኤፍቢሲ ነው።

Image may contain: one or more people, people sitting, crowd and indoor, text that says 'Reserved'

FanaBC

ዩኒቨርሲቲዎች በተልእኮ እና በትኩረት መስክ ወደ ተደለደሉበት በፍጥነት እንደሚገቡ ተገለፀ

ዩኒቨርሲቲዎች በተልእኮ እና በትኩረት መስክ ወደ ተደለደሉበት በፍጥነት እንደሚገቡ ተገለፀ

On Oct 18, 2020

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዩኒቨርሲቲዎች በተልእኮ እና በትኩረት መስክ ወደ ተደለደሉበት ዓላማ በፍጥነት መግባት እንዳለባቸው ተጠቆመ።የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ ዩኒቨርሲቲዎቹን በትኩረት መስክ መለየት የሀገሪቱን ብልጽግና ለማሳካት እንደሚረዳ ተናግረዋል፡፡በመሆኑም ተቋማቱ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ በመወጣት ዓርአያ ሆነው የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ የሚፈልገውን ተወዳዳሪ የሰው ኃይል ማፍራት እንዳለባቸው ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሙሉ ነጋ በበኩላቸው የዩኒቨርሲቲዎች ልየታ ዋና ዓላማ ዩኒቨርሲቲዎቹን ለማበላለጥ ሳይሆን ከነበራቸው የትኩረት አቅጣጫ በመነሳት የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ጠቁመዋል፡፡በትምህርትና ስልጠና ፍኖተ-ካርታ ጥናት ውጤት መሠረት 8 የምርምር፣ 15 የአፕላይድ ሳይንስ፣ 2 የሳይንስና ቴክኖሎጂ እና ቀሪዎቹ 21ዱ የአጠቃላይ ዩኒቨርሲቲ ተብለው መለየታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።