19 ጥቅምት 2020, 07:53 EAT

በመላው ፈረንሳይ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አንገቱን ተቀልቶ ለተገደለው መምህር ድጋፋቸውን ለመስጠት አደባባይ ወጡ።
ሳሙኤል ፓቲይ የተባለው መምህር በክፍሉ ውስጥ አወዛጋቢ የነብዩ መሐመድ የካርቱን ስዕሎችን ለተማሪዎቹ ካሳየ በኋላ ከትናንት በስቲያ አንድ የ18 ዓመት ወጣት ትምህርት ቤት አቅራቢያ አንገቱን መቅላቱ ይታወሳል።
ሳሙኤል ፓቲይ የሚያስተምርበት ትምህርት ቤት መምህራንን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች “እኔም መምህር ነኝ” “እኛ ፈረንሳይ ነኝ” የሚሉ መፈክሮችን ይዘው አደባባይ ወጥተዋል።
ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላ የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን መምህሩ አንገቱ ተቀልቶ የተገደለው “በእስላማዊ የሽብር ጥቃት ነው” ብለው ነበር። ጥቃት ያደረሰው ሩሲያ ውስጥ የተወለደው ወጣት አብዱላክ ሲሆን ጥቃቱን ባደረሰበት ስፍራ በፖሊስ በጥይት ተመትቶ ተገድሏል።
ከዚህ ጥቃት ጋር በተያያዘ የፈረንሳይ ፖሊስ 11 ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ይፋ አድርጓል። ከእነዚህም መካከል 4ቱ ከጥቃት አድራሹ ጋር የቅርብ ዝምድና የነበራቸው ናቸው።
ለ47 ዓመቱ መምህር ድጋፋቸውን ለመግለጽ አደባባይ ከወጡት መካከል “ለሪፐብሊኩ ጠላቶች ትዕግስት አያስፈልግም” “እኔም መምህር ነኝ፤ ፓቲይ አንተን አስብሃለሁ” የሚሉ መፈክሮችም ታይታዋል።
የፈረንሳይ ጠቅላይ ሚንሰትር ጄን ካስቴክስ በትዊተር ገጻቸው ላይ “እኛ ፈንሳይ ነን። . . . አታሸብሩንም” ሲሉ ጽፈዋል።

አርብ ዕለት የሆነው ምን ነበር?
ጥቃቱ አድራሹ ከሚኖርበት ከተማ 110 ኪ.ሜትር ተጉዞ ትምህር ቤቱ ጋር ከደረሰ በኋላ ሳሙኤል ፓቲይ የተባለው መምህር የትኛው እንደሆነ እንዲጠቁሙት ተማሪዎችን ጠይቋል።
ጥቃት አድራሹ ከዚህ ቀደም ከትምህር ቤቱ ጋርም ይሁን ከመምህሩ ጋር ግንኙነት አልነበረውም። መምህሩ ከትምህርት ቤት ወደ መኖሪያ ቤቱ ሲጓዝ ጥቃት አድራሹ ሲከተለው ነበር።
ከዚያም በቢላዋ ጭንቅላቱን መትቶ ከጣለው በኋላ አንገቱን ቀልቶታል። ፖሊስ እንደሚለው ጥቃቱን ሲያደርስ “አላሁ አክበር” ሲል የአይን እማኞች ሰምተውታል።
ጥቃቱን ካደረሰ በኋላ ለመሰወር ቢጥርም ጥሪ የደረሰው ፖሊስ በፍጥነት በስፍራው ተገኝቷል። ከዚያም 12 ጊዜ በጥይት ተመትቶ ተገድሏል። ፖሊስ 30 ሴንቲ ሜትር የሚረዝም ቢላዋ ከጥቃት አድራሹ ጎን ማግኘቱንም አስታውቋል።
በፈረንሳይ መሰል ጥቃት ሲፈጸም ይህ የመጀመሪያው አይደለም። ከሶስት ሳምንት በፊት ትውልደ ፓኪስታናዊ የ18 ዓመት ወጣት በስጋ መከትከቻ ትልቅ ቢላ ሁለት ሰዎች ላይ ጉዳት አድርሶ ነበር።
እአአ 2015 ላይ ሁለት ሙስሊም የፈረንሳይ ዜጎች የቻርሊ ሄብዶ መጽሔት ቢሮን ሰብረው በመግባት በሰራተኞቹ ላይ ተኩስ ከፍተው ሰራተኞቹን ጨምሮ በጠቅላላው 12 ሰዎች መግደላቸው የሚታወስ ነው።
ማክሮን፡ “ፈረንሳያዊው አንገቱን የተቀላው በሽብር ጥቃት ነው”
17 ጥቅምት 2020

የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን ከመዲናዋ ፓሪስ አቅራቢያ አንገቱ ተቀልቶ የተገደለው መምህር “በእስላማዊ የሽብር ጥቃት ነው” አሉ።
በጥቃቱ የተገደለው መምህር አወዛጋቢ የሆኑ የነብዩ መሐመድን ካርቱን ምስሎች ለተማሪዎቹ ያሳይ ነበር ተብሏል።
ጥቃት አድራሹ በፖሊስ ተመትቶ ተገድሏል።
ፕሬዝደንት ማክሮን በስም ያልተገለጸው መምህር የተገደለው “ሃሳብን በነጻነት መግለጽን በማስተማሩ ነው” ብለዋል።
ጥቃቱ የተፈጸመበት ስፍራ ተገኝተው፤ “አያሸንፉም. . . ፈጣን እርምጃ እንወስዳለን” ብለዋል ፕሬዝደንት ማክሮን።
ስለጥቃቱ እስካሁን የሚታወቁ
ጥቃቱ የተፈጸመው ትናንት በአገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 2 ሰዓት አከባቢ ትምህርት ቤት አቅራቢያ ነበር።
ጥቃት አድራሹ በመንገድ ላይ በትልቅ ቢላዋ የመምህሩን አንገት ቆርጧል። ፖሊስ እንደሚለው ማንነቱ ይፋ ያልተደረገው ጥቃት አድራሽ ጥቃቱን ሲያደርስ “አላሁ አክበር” ሲል የአይን እማኞች ሰምተውታል።
. ፈረንሳይ “ድንግልና” የሚመረምሩ ዶክተሮችን እቀጣለሁ አለች
ግለሰቡ ጥቃቱን ካደረሰ በኋላ ከስፍራው ለመሰወር ቢጥርም ጥሪ የደረሰው ፖሊስ በፍጥነት በስፍራው ተገኝቷል።

ፖሊስ ጥቃት አድራሹ እጁን እንዲሰጥ ቢጠይቀውም ዛቻ በማድረሱ ከፖሊስ በተተኮሰበት ጥይት ተገድሏል።
ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ አራት ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ኤኤፍፒ ዘግቧል። በቁጥጥር ሥር የዋሉት ግለሰቦች ከጥቃት አድራሹ ጋር ዝምድና ሳይኖራቸው አይቀርም ተብሏል።
ምንም እንኳ ፖሊስ የጥቃት አድራሹን ማንነት ይፋ ባያደርግም፤ ቢኤፍኤምቲቪ የተሰኝ የፈረንሳይ የቴሌቪዥን ጣቢያ ጥቃት አድራሹ ሩሲያ ሞስኮ ውስጥ የተወለደ የ18 ዓመት ወጣት ነው ሲል ዘግቧል።
አንገቱ ተቀልቶ የተገደለው መምህር ማነው?
እንደ ሌሞንድ ጋዜጣ ዘገባ ከሆነ የታሪክ መምህሩ በክፍል ውስጥ ሃሳብን በነጻነት ከመግለጽ ጋር በተያያዘ አወዛጋቢ የነብዩ መሐመድ የካርቱን ስዕሎችን በመጠቀም ያስተምራል።
መምህሩ በዚህ ደስተኛ የማይሆኑ ተማሪዎች ካሉ ክፍሉን ለቀው መውጣት እንደሚችሉ ይናገር ነበር ብሏል ዘገባው።
ከሳምንታት በፊት ሙስሊም ወላጆች የመምህሩን ተግባር በመቃወም ለትምህር ቤቱ ቅሬታ አቅርበውም ነበር።
በፈረንሳይ መሰል ጥቃት ሲፈጸም ይህ መጀመሪያው አይደለም። ከሶስት ሳምንት በፊት ትውልደ ፓኪስታናዊ የ18 ዓመት ወጣት በስጋ መከትከቻ ትልቅ ቢላ ሁለት ሰዎች ላይ ጉዳት አድርሶ ነበር።
እአአ 2015 ላይ ሁለት ሙስሊም የፈረንሳይ ዜጎች የቻርሊ ሄብዶ መጽሔት ቢሮን ሰብረው በመግባት በሰራተኞቹ ላይ ተኩስ ከፍተው ሰራተኞቹን ጨምሮ በጠቅላላው 12 ሰዎች ገድለው ነበር።
