October 19, 2020 – Konjit Sitotaw
የፓስፖርት አገልግሎት ከጥቅምት 10 ጀምሮ መስጠት ይጀምራል ተባለ፡፡
–
በኢሜግሬሽን፣ ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ ተሬሳ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በኦን ላይን አማካኝነት ፓስፖርት አገልግሎት ከነገ ጥቅምት 10 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ መስጠት ይጀመራል ብለዋል።
–

ኤጀንሲው ከዚህ በፊት ፓስፖርት እና ሌሎች ተያያዥ አገልግሎቶችን በኢንተርኔት አማካኝነት በኦንላየን እንደሚሰጥ አስታውቆ ነበር።አሁን ላይ በዋናነት ከጥቅምት 2 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ በኦን ላይን የቪዛ ማራዘም ና ጊዜአዊ የመኖሪያ ፍቃድ የመስጠት አገልግሎት ተጀምሯል፡፡
–
የፓስፖርት አገልግሎት በተባለው ቀን ያልተጀመረው ሌሎች የደህንነት እና የቴክኒክ ስራዎች በታሰበው ጊዜ ባለመጠናቀቃቸው መሆኑንም አቶ ደሳለኝ ነግረውናል።
–
ተገልጋዮች በኦንላይን www.Evisa.com ላይ በመግባት ቪዛ ማራዘምና ጊዜያዊ የመኖሪያ ፍቃድን የመሳሰሉ አገልግሎቶችን ማግኘት እንደሚችሉ ገልፀውልናል፡፡
–
በመዲናዋ የሚሰጠው አጠቃላይ መደበኛ የፓስፖርት አገልግሎት ህዳር 1 ቀን እንደሚጀምርም ነግረውናል፡፡
