October 20, 2020 

“ለሚ ኩራ” የአዲስ አበባ 11ኛ ክፍለከተማ በመሆን በምክር ቤቱ ጸድቋል፡፡

ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ አዲሱ ክፍለ ከተማ ተጨማሪ ይዞታ ሳይሆን ከዚህ ቀደም ከነበረው ከቦሌ እና ከየካ ክፍለ ከተሞች በመክፈል የተዋቀረ ነው ብለዋል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በከሰዓት ውሎው ክፍለ ከተሞችንና ወረዳዎችን እንደገና ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ወሳኔ አስተላልፏል፡

አዲሱ አደረጃጀት የነዋሪዎችን ብዛት በማመጣጠን ፣ አዳጊ የሆነውን የአገልግሎት ተደራሽነትና የማስተዳደር አቅምን በማጎልበት ለከተማው ነዋሪዎች ሚዛናዊ በሆነ ርቀትና ተደራሽ በሆነ መልኩ የአገልግሎት አቅርቦት በማመቻቸት ነዋሪው ፍትሃዊና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚረዳ ይሆናል ነው የተባለው፡፡በመድረኩ ላይ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ አዲሱ ክፍለ ከተማ ተጨማሪ ይዞታ ሳይሆን ከዚህ ቀደም ከነበረው ከቦሌ እና ከየካ ክፍለከተሞች በመክፈል የተዋቀረ ነው ብለዋል፡፡ምክር ቤቱ በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ሰፋ ያለ ውይይት ያደረገ ሲሆን ክፍለ ከተሞችን እና ወረዳዎችን ዳግም የማቋቋሚያ አዋጁንም ተቀብሎ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡በዚህም ለሚ ኩራ ክፍለከተማ የአዲስ አበባ 11ኛው ክፍለ ከተማ እንዲሆን ምክር ቤቱ በዛሬ ውሎው መወሰኑን

አዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Image may contain: 1 person

–በዚህ መሠረት፦1ኛ. አቶ ጥራቱ በየነ – በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማ ስራ አስኪያጅ ቢሮ ኃላፊ2ኛ. ዶክተር መስከረም ፈለቀ – ቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ3ኛ . ኢንጂነር አያልነሽ ሀ/ማርያም – ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ4ኛ. ዶክተር መስከረም ምትኩ – የፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር5ኛ. ዶክተር ሚልኬሳ ጃጋማ – መሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ6ኛ. ዶክተር ሙሉቀን ሀብቱ – ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ7ኛ. አቶ ተፈራ ሞላ – ሰራተኛና ማህበራዊ ቢሮ ኃላፊ8ኛ. አቶ ሙሉጌታ ተፈራ – ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ 11ኛው ክፍለ ከተማ “ለሚ ኩራ” ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ኤልያስ መሀመድ ሆነው ተሹመዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ለሌሎች ክፍለ ከተሞች የዋና ስራ አስፈጻሚ አመራሮች ሹመት ተሰጥቷል።

በዚህም ፦

– ወ/ሮ ሽታዬ መሀመድ – ልደታ ክ/ከተማ
– ወ/ሮ ነጻነት ዳባ – ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ
– አቶ ሙቀት ታረቀኝ – ኮልፌ ክ/ከተማ
– አቶ አባዌ ዮሀንስ – ጉለሌ ክ/ከተማ
– ወ/ሮ ፈቲያ መሀመድ – አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ
– ዶ/ር እመቤት ጌታነህ – አራዳ ክ/ከተማ
– አቶ አስፋው ተክሌ – የካ ክፍለ ከተማ ሆነው ተሹመዋል።

በሌላ በኩል ባሉበት የቀጠሉ የክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚዎች የሚከተሉት ናቸው ፦

– አቶ ጀማል ረዲ – ቂርቆስ ክ/ከተማ
– አቶ መኮንን አምባዬ – ቦሌ ክ/ከተማ
– አቶ ይታያል ደጀኔ – አዲስ ከተማ ክ/ከተማ

አዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት