ሐራ ዘተዋሕዶ

October 22, 2020 

ከእኒኽም አጀንዳዎች ውስጥ፡-

በሌላ በኩል ምልአተ ጉባኤው፣ በአርቃቂው ኮሚቴ ተመጥነው የቀረቡለትን 16 የመነጋገርያ ነጥቦች፣ ዛሬ ከቀትር በኋላ በማጽደቅ፣ በአጀንዳዎቹ ላይ መነጋገር የጀመረ ሲኾን፤ የአጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ 39ኛ ዓመታዊ ስብሰባ የጋራ መግለጫ እና የውሳኔ ሐሳብ በንባብ አድምጧል፡፡ አስፈላጊ ማስተካከያዎችን በማከልም፣ የ2013 ዓ.ም. በጀት ዓመት የሥራ መመሪያ ኾኖ እንዲሠራበት፣ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤቱ በኩል ለመምሪያዎች እና ድርጅቶች እንዲሁም ለመላው አህጉረ ስብከት እንዲሠራጭ ወስኗል፡፡