- በጉራ ፈርዳ ወረዳ ከሰኞው የቀጠለ ጥቃት ተፈፅሞ ሰዎች መገደላቸውን የቲክቫህ አባላት አሳውቀዋል።
- ከሁለት ቤት ውስጥ ብቻ ከ10 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ህይወት አልፏል ብለዋል አባላቶቻችን።
- ለሁለት ቀናት በተፈጸመ ጥቃት የ31 ሰዎች ህይወት አለፈ።ጥቅምት 8 እና ጥቅምት 11 ቀን 2013 ዓ.ም በሁለት ቀበሌዎች በተፈፀመ ጥቃት የ31 ሰዎች ህይወት ማለፉን FBC ዘግቧል።

ዛሬ ጥቅምት 12/2013 ዓ/ም ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቲቺንግ ሆስፒታል ለእርዳታ ከመጡ 12 ሰዎች መካከል 6ቱ ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ህፃናት መሆናቸውን የቲክቫህ አባል የሆነ ሀኪም ገልጿል።
መልዕክታቸውን ያደረሱ የአካባቢው ቲክቫህ አባላት፥ ፓሊስ “ማንነታቸው ያልታወቁ” ይላል ይህ ትክክል አይደለም ጥቃት ፈፃሚዎቹ በግልፅ የሚታወቁ ናቸው ብለዋል።

በቤንች ሸኮ ዞን አስተዳደር በጉራ ፈርዳ ወረዳ ውስጥ ከጥቅምት ስምንቱ ምሽት ጥቃት በተጨማሪ ትላንት ረቡዕ በድጋሚ ጥቃት ስለመፈፀሙ ለአሀዱ ሬድዮ አረጋግጧል።
የፀጥታ መዋቅሩ የጥቅምት ስምንቱን ችግር እያረጋጋ ባለበት ወቅት ነው ትላንት በተመሳሳይ ወረዳ ጊኒቃ በምትባል ቀበሌ በድጋሚ ጥቃት መፈጸሙን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፍቅሬ አማን ያረጋገጡት።
ከታጠቁ አጥፊ ሃይሎች ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ 16 ግለሰቦች እስካሁን ድረስ በቁጥጥር ስር ውለዋል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው። የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ 500 ግለሰቦች ከአከባቢው ተፈናቅለዋል ብለዋል፡፡
ጥቃት ፈፃሚዎች እነማን ናቸው ? በምን ምክንያት ጥቃቱን ፈፀሙ የሚለው ጉዳይ ገና በመጣራት ላይ እንዳለ ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል፡፡
አስተዳደሩ ስለረቡዕ ጥቃት መጠን አልገለፀም።
በቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ በሰዎች ላይ ጥቃት በማድረስ የተጠረጠሩ 16 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
(ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ በሰዎች ላይ ጥቃት በማድረስ የተጠረጠሩ 16 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ ፡፡በቁጥጥር ስር ከዋሉት ግለሰቦች መካከል አንድ የፖሊስ አባልና አራት አመራሮች እንደሚገኙበት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፍቅሬ አማን በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡–ዋና አስተዳዳሪው በወረዳው ጥቅምት 8 እና ጥቅምት 11 ቀን 2013 ዓ.ም በሁለት ቀበሌዎች በተፈፀመ ጥቃት የ31 ሰዎች ህይወት ማለፉን እና አምስት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል፡፡–1 ሺህ 480 አባወራዎች ደግሞ ተፈናቅለው በቢፍቱ ከተማ የተጠለሉ ሲሆን ጊዜያዊ እርዳታ እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ ተፈናቃዮችን ወደ ነበሩበት ለመመለስና መረጋጋት ለማስፈን እየተሰራ መሆኑንም አስተዳዳሪው ገልፀዋል፡፡
Source – (Ahadu Radio, FBC , Tikvah Family GuraFerda)
PHOTO : TIKVAH FAMILY (GuraFerda)