October 22, 2020 – Konjit Sitotaw
የባልደራስ ከፍተኛ አመራሮች ምስክር በዝግ ችሎት ይሰማ አይሰማ የሚለውን ለመወሰን 1 ወር ከ18ቀን ለህዳር 29 ቀን ተቀጠሩ።–

~ እስክንድር ነጋ (የባልደራስ ፕሬዝዳንት)~ ስንታየሁ ቸኮል( የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ)~ አስቴር ስዮም ( የክፍለ ከተማ አደራጅ)~ አስካለ ደምሴ (የሴቶች አደረጃጀት ሰብሰቢ)–በዛሬው የችሎት ውሎ ምን ተካሄደ….–አቃቢ ህግ ያቀረበውን ክስ ተከትሎ ተከሳሽ ምላሽ አንዲሰጥ በሚል ለመስከረም 29 መቅጥሩ ይታወሳል።ይህን ተከትሎ የተከሳሽ ጠበቆች በክሱ ላይ ምላሽ ሰጥተዋል።–ታዲያ ዛሬ ፍ/ቤት የቀረቡት የባልደራስ ከፍተኛ አመራሮች በክሱ ሁኔታና በምስክሮች አቀራረብ ያለውን ሂደት በማንሳት በቀጣይ የአቃቢ ህግ ምስክሮችን በምን መልኩ ያቅርብ በሚለው ጉዳይ ክርክር ተካሂዷል።–ክርክሩ …..አቃቢ ህግ ምስክሮችን ከመጋረጃ በስተጀርባ ላቅርብ የሚል ነበረ።–እነ እስክንድርና ጠበቆቻቸው ደግሞ….ምስክር መደመጥ ያለበት ከችሎት ፊት …በህዝብና በሚዲያ ፊት ነው መሆን ያለበት እንጅ ከመጋረጃ በስተጀርባ ማን እንዴት በኛ ላይ እንደሚመሰክር ስለማናውቅ…በተጨማሪም ምስክሮች የሚሰጡት ቃል ታአማኒንት በጅጉ ስለሚያሳስበን ምስክሮቹ በግልፅ መቅርብ አለባቸው የሚል ነበር።–ፍ/ቤቱ ምስክሮቹ በምን መልኩ ይቅረቡ የሚለውን ለመወሰን በሚል ለቀጣይ 1 ወር ከ18ቀን ማለትም ለህዳር 29 ቀን ቀጥሮታል።የቀጠሮውን ቀን መርዝም በተመለከተ እነ እስክንድር ነጋ እንዲስተካከልና ቶሎ ፍርድ ተሰጥቶ በቀጣይ አገራዊ ምራጫ ላይ ተሳትፈው በህዝብ መዳኘት እንደሚፈልጉ ገልፀው የነበረ ቢሆንም……ፍ/ቤቱ ግን የችሎት መደራረብ አለብን ቶሎ ማድረግ አንችልም በሚል ቀጠሮውን አፅንቶ ወጥቷል።(በወግደረስ ጤናው)–የመጋረጃ ጀርባን ምስክር አስመልክቶ እስክንድር በችሎት የተናገረው–~” በኢትዮጵያ የደርግ ባለሥልጣናት በዘር ማጥፋት ወንጀል ተከሰው፤ የዐቃቤ ህግ ምስክሮች በግልጽ ችሎት ቀርበው መስክረዋል “~ ” በአፍሪካ በርዋንዳዋ መቶ ሺዎች በግፍ ያለቁበት ጉዳይ በግልጽ ችሎት ምስክሮች ቃላቸውን ሰጥተዋል “~ ” በናዚዎች ጉዳይ ምስክሮች በግልጽ ችሎት ምስክሮች ተሰምተዋል “–እነኚህ እና የመሳሰሉ እጅግ በጣም ከባድ እና ትልልቅ ወንጀሎች በግልጽ ችሎች ፤ የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ቀርበው ምስክርነት ሰጥተዋል ። እስካሁንም በምስክሮች ላይ ደረሰ የተባለ አንዳችም ነገር ስለመኖሩ አልተገለጸም ።–~ ” የእኛ ጉዳይ በዝግ ችሎት ከመጋረጃ ጀርባ ምስክሮች እንዲቀርቡ መደረጉ ፤ የሐሰት ክስ መሆኑ እንጂ እስከ ዛሬ ከሰማናቸው ከፍተኛ እና አደገኛ ክሶች በልጦ አይደለም–ዐቃቤ ሕግ አሁን ላይ የተከተለው ልምድ ፤ በላቲን አሜሪካ አገራት የእጽ አዘዋዋሪዎች ጉዳይን በዝግ ችሎት ከመጋረጃ ጀርባ ምስክሮች የማሰማትን ልምድ ነው የተከተለው ።”
