ሐራ ዘተዋሕዶ
October 23, 2020
- የሕግ ባለሞያዎች፥ በሀገር ውስጥ እና በውጪ አህጉረ ስብከት የቤተ ክርስቲያን ውክልና እየተሰጣቸው ግፈኞችንና ያለስሟ እና ያለግብሯ በሐሰተኛ ትርክት ለማጠልሸት የሚንቀሳቀሱትን እንዲፋረዱ ወሰነ!

- በቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመሩ ኹለት የብፁዓን አባቶች ኮሚቴዎች፣ በቤተ ክርስቲያንና በአገር ሰላም መንግሥትንና የፖሊቲካ ኃይሎችን በቀጥታ ያነጋግራሉ፤
- ሕዝብ እየተገደለና አገር እየጠፋ ያለው፣ በፖሊቲካው ትርምስ በመኾኑ፣ በቅራኔ የተፋጠጡ ኃይሎች ሰላም እንዲያወርዱ ይማፀናሉ፤ ለተገደሉ ኦርቶዶክሳውያን ካሳን፣ ለተፈናቀሉት መመለስን፣ በሐሰት ተከሰው በእስር ለሚንገላቱት መፈታተን፣ ለተደፈሩት ይዞታዎች መከበርን እንዲያነብር መንግሥትን ይጠይቃሉ፤
- የቅድመ አደጋ ማስጠንቀቂያ ሥርዓትን የመዘርጋቱ ሥራ፣ ቀደም ሲል በተላለፈው ውሳኔ መሠረት በአስቸኳይ እንዲጀመር፣ ምልአተ ጉባኤው ጠቅላይ ጽ/ቤቱን አሳስቧል፤
- ለድንገተኛ አደጋዎች እና ችግሮች ፈጣን ምላሽ እና ርዳታ የሚሰጥ አስተባባሪ አካል፣ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ በማእከል እንዲቋቋም መመሪያ ሰጥቷል፤ በተለይ የውጪ አህጉረ ስብከት፣ ፋይናንሳዊ፣ ማቴሪያላዊ እና ሞያዊ ድጋፎችን እንዲያስተባብሩለት ተስማምቷል፡፡
