October 24, 2020Konjit Sitotaw

ዛሬ በጂግጂጋ ዩኒቨርሲቲ በተካሄደ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች የምረቃ ስነስርዓት ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ፍሬው ተገኘ፣

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሴኔት “ተስፋ የተጣለበት መሪ” በሚል ለፕሬዝዳንት ሙስጠፌ መሐመድ ኡመር የሰጣቸውን የክብር ሜዳሊያ ሸልመዋቸዋል።

ፕሬዝዳንት ሙስጠፌ ባሳዩት የአመራር ጥበብ በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ተዋዳጅነትን ማትረፋቸውን ገልፀው የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ይህን ክብር ሲያጎናፅፋቸው ከፍተኛ ደስታ የሚሰማው መሆኑን ተናግረዋል።

በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ሶማሊኛ ቋንቋን በዲግሪ ደረጃ ባህር ዳር ማስተማር እንደሚጀምር አብስረዋል። ጂግጂጋ ዩኒቨርሲቲ ለዶክተር ፍሬው ተገኘ የሶማሌ ባህላዊ የክብር ልብስን በመሸለም ለክብር እንግድነታቸው አክብሮት ለግሶአል።

Image may contain: 1 person, standing and hat