October 24, 2020

No photo description available.

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) የብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈፀመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ።

* የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ዛሬ ጥቅምት 14 ቀን 2013 ዓ.ም እያካሄደ ባለው አስቸኳይ ስብሰባ የአማራን ሕዝብ እየገጠሙት ባሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ እየተወያየ ይገኛል።

በውይይቱ በዋናነት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በአማራዎች ላይ እየደረሰ የሚገኘውን የዘር ማጥፋት ወንጀል እና ሌሎች መዋቅራዊና ሕግ ሰራሽ መገለሎችን የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በ «አማራ ክልል» በሚገኙ ከተሞች በመጭው ረቡዕ ጥቅምት 18 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲሁም በአዲስ አበባ እሁድ ጥቅምት 22 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲደረግ ወስኗል።