Image may contain: text

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በታላቁ የሕዳሴ ግድባችን ላይ ግብፅና ሱዳን ሊወስዱት ስለሚችሉት እርምጃ የሰጡትን ሀሳብ እጅጉን ያወግዛል፤የሀገራችንን ሉዓላዊነት የሚዳፈር እንኳን ካንድ የታላቅ ሀገር ፕሬዚዳንት ጤናማ አዕምሮ ካለዉ ሰዉ የማይጠበቅ ተራና ተቀባይነት የሌለው ድስኩር መሆኑንም ማሳወቅ ይፈለጋል!

እኛ ኢትዮጲያውያን አባይ ህልዉናችን ነዉ ተፈጥሮ በለገሰችን ፀጋ ለመጠቀም የማንንም ይሁንታ አንጠይቅም ፤የማንንም እንግርግሪያና ዛቻ ፈርተንም የሕዳሴውን ግድብ የማጠናቀቅ ስራችንን ለማይክሮ ሰከንድ አናቋርጥም፤ኢሕአፓ መንግስት በዚህ በኩል ያሳየውን ቁርጠኛ አቋም እያደነቀ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብም በሉዓላዊነታችን ላይ የዉጪ ሀይሎች ሊያደርሱት የሚፈልጉትን ጥቃት በተባበረ ክንድ እንደ ጥንቱ መመከት እንድንችል ከጥላቻና ቁርሾ ፖለቲካ ወጥተን ፣በመፈቃቀርና በመመካከር ፣የእናት ጡት ነካሽ ባንዳ ፖለቲከኞችና አክቲቪስቶች በሚነዙት የሀሰት ትርክት ሳንታለል ሀገራችን ሁሉም ዜጎቿ በነፃነት የሚኖሩባት እንድትሆን ከጎሰኝነትና ዘረኝነት አስተሳሰብ እራሳችንን እንድናፀዳ ያሳስባል።

የዉስጥ አንድነታችን ሲዳከም ለታሪካዊ ባላንጣዎች መግቢያ በር ልንከፍት ስለምንችል በየቦታው የሚከሰቱ ጎሳና ብሔር ተኮር የእርስ በርስ ግጭቶችን በማስወገድ ለሁለንተናዊ እድገት በጋራ እንድንታገል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

በመጨረሻም በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ አንዳችም አይነት አሉታዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ በሚሞክሩ አካላት ላይ ቅንጣት ታክል ትዕግሥት የማናደርግ መሆኑን ማስጠንቀቂያ መስጠት እንፈልጋለን!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ!