
ቤተ እስራኤላዊው ምክትል የደህንነት ሚኒስትር ጋዲ ያቫርከን የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሰጡትን መግለጫ ተቃውመዋል።
የትራምፕን ከሀገራቸው እስራኤል ጎን መቆምን ያደነቁት ሚኒስትሩ፤ፕሬዝዳንቱ በግድቡ ዙሪያ በኢትዮጵያ እና በግብፅ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት የሄዱበትን ሚዛናዊ ያልሆነ አስተያየት በፃፉት ደብዳቤ ተችተዋል።
“3500 ዓመት በነፃነት የኖረች ሉዓላዊት ሀገር በክልሏ ውስጥ ለዜጎቿ ጥቅም እና ደህንነት ያሰበችውን የማድረግ መብት አላት” ነው ያሉት።
ኢትዮጵያዊያን እና ግብፃውያን በዘመናት ውስጥ ሲነሱ እና ሲወድቁ እዚህ የደረሱ ሁለት ጥንታዊ ህዝቦች ናቸው፤አሁንም በስኬት እና በኩራት እንደ ጎረቤት ይቀጥላሉ ብለዋል።
ኢትዮጵያ የእስራኤል የቅርብ አጋር እና የቤተ እስራኤላውያን ማህበረሰብ ትውልድ ቦታ መሆኗን ጠቅሰው ፤አሜሪካ እንደ አንድ የነፃው አለም መሪ ፤ በሀገራት መካከል የሚፈጠርን አለመግባባት ለመፍታት ገለልተኛ መሆን አለባት ብለዋል።
በአፍሪካ ግዙፍ የሆነው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ሀገሪቱ ለያዘችው እድገት ወሳኝ እና በአስቸጋሪ ሁኔታ በግብርና የሚተዳደሩ በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን የኤሌክትሪክ ሀይል ተጠቃሚ ያደርጋል።
ኢትዮጵያውያን ግድቡ ተገንብቶ ለታለመለት አላማ እንዲውል በገንዘባቸው በርትተው በመገንባታቸው እና እንደ ቅድመ አያቶቻቸው ለተፈጥሮ መብታቸው በመነሳታቸው ኩራት እንደሚሰማቸው ገልፀዋል፡፡
ቤተ እስራኤላዊው ምክትል የደህንነት ሚኒስትር ጋዲ ያቫርከን የውጭ ጫናዎች ቢኖሩም፤ለኢትዮጰያውያን ብልፅግና ስለሚያስፈልግ የተጀመረው ታላቅ ግድብ ይጠናቀቃል ብለዋል።
በመሆኑም በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳዮች ላይ የሚደረግ ማንኛውም የውጭ ጣልቃ ገብነት ዓለም አቀፍ ሕግን የጣሰ ይሆናልም ሲሉ አስረድተዋል፡፡
ቤተ እስራኤላዊው ጋዲ ያባርካን የግብፅ መንግስትን በአባይ ውሃ ላይ ጥገኛ መሆን እንደሚረዱ እና ለዛም ክብር እንዳላቸው ገልፀዋል።
ስለሆነም ኢትዮጵያ እና ግብፅ ለጉዳዩ መፍትሄን እንዴት መፈለግ እንደሚችሉ በእርግጠኝነት ስለሚያውቁ አሜሪካ የተጀመረውን የድርድር ሂደት እንድትደግፍ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ምንጭ-https://artdaily.cc/index.asp?int_sec=11&int_new=129512… See Less
