Image may contain: 2 people, people sitting, beard, hat and indoor

📍 *የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንና የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን መግለጫ!*የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሕዳሴው ግድብ ጉዳይ ያስተላለፉትን ንግግር እንዳሳዘናት ገልጻለች።ፕሬዝዳንቱ በአገራችን ላይ ያስተላለፉት የጦርነት ጥሪ ቅዱስ ሲኖዶስ አጥብቆ ይቃወማል ሲል የገለጸው መግለጫው መላውም የዓለም መንግሥታትና ሕብረተሰብ ችግሩን በጥልቀት እንዲገነዘቡት ቅዱስ ሲኖዶሱ አሳስቧል፡፡በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በቅርቡ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በሰጡት መግለጫ ማዘኗን ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ አስታውቀዋል።ፕሬዝደንት ትራምፕ የተናገሩት ንግግር መላውን የአሜሪካ ሕዝብ እና መንግሥታቸውን ይወክላል ብለን ፈጽሞ አናምንም ሲሉም ነው የገለጹት።”የኢትዮጵያ ጉዳይ ይመለከተናል የምትሉ ምሁራን፣ ፖለቲከኞች እና ለሀገራችሁ ብልጽግና ቀናዒ የሆናችሁ በሙሉ ማንኛውንም ልዩነቶቻችሁን ወደጎን በመተው ሀገራዊ በሆኑ ፐሮጀችቶች ላይ ሁሉ የጋራ አቋም በመያዝ ትብብር እንድታደርጉ እማጸናችኋለሁ” ሲሉ በመልዕክታቸው ጠይቀዋል።