ሁሌ እናስታውሳቸውተቀብሮ እንዳይቀርአኩሪ ታሪካቸው!!!!!!!

Image may contain: 1 person, standing, shoes and suit

ዘርሁ ክህሸን ማን ነው????

ወያኔ በተለይም በትረ ስልጣኑን ከተቆጣተረ በኋል ቁጥር አንድ ጠላት ብሎ የፈረጀውን ኢሕአፓን ከምደረ ገፅ ለማጥፋት በአፋኝ ደህንነቱ አምካኝነት ከፍተኛ የአፈና፤ደብዛ የማጥፋትና የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ አካሂዷል። እነ ጸጋዬ ገ/ መድህን ( ደብተራው) ና አበራሽ በርታ እንዲሁም ሌሎችን ብርቅዬ የኢሕአፓ ልጆች መዳረሻ አሳጥቷል። እንደ ጋይም የመሳሰሉትን በጠራራ ፀሃይ አስገድሏል። የድርጅቱን አባሎች ውስጥ ውስጡን እየገደለና እያፈነ የድርጅቱ ስም እንዳይጠራና እንደሌለ ለማስመሰል ከፍተኛ ስራ ሰርቷል።በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደረው ኢሕአፓ ግን ተዳከመ እንጂ አልጠፋም፤ እራሱን እንደገና በማደራጀት ትግሉንም እስካሁንም ቀጥሏል።ከአፈናው ባሻገር ዘረኛውና መሰሪው ወያኔ፤ ቁጥር አንድ ጠላት ብሎ የፈረጀውን ድርጅት ኢሕአፓን ለማጥፋት በጣም ከፍተኛ ባጀት በመመደብ፤ የመንግስት መገናኛ አውታሮችን በመጠቀም፤የኢሕአፓን ታሪክ አጠልሽተው የሚያሳዩ፤ አዛብተው የሚያሳዩ መጽሃፎች እንዲፃፉ በማበረታታትና በማሰራጨት፤ከ ከሀዲዎችና የኢሕአፓ ጠላቶች ጋር ቃለመጠይቆች እንዲካሄዱ ልዩ ልዩ የሚድያ መድረኮችን በማመቻቸትና በማበረታታት በፕሮፖጋንዳውም መስክ ከፍተኛ ስራ ሰርቷል፤ እየሰራም ነው።ይህ መሰሪ ወያንያዊ ተግባር አሁንም በ ዘረኛው ኮለኔል አብይ መልኩንና ተላላኪ የቁራ መልእክተኞቹን ቀይሮ በአዲስ መልክ ብቅ ብቅ ማለቱን ቀጥሏል። ያ ሁሉ ጀግና ኢትዮጵያዊ ወጣት የተሰዋበትን ህዝባዊ ትግል፤የኢሕአፓ የትግል፤ በቃላቶች ልዩነት “በቸና በሸ” ተጣሉ ብሎ የንቀት ዲስኩሮችን በመደርስኮር፤በመሰረታዊ የህዝብ ጥያቄዎች ምክንያት የተከሰቱትን ልዩነቶች በግለሰቦች ቂምና ቁርሾ እንደሆነ አድርጎ ለማቅረብ መሞከር የዚህ ተግባር አንዱ ገፅታው ነው።ኢሕአፓ ውስጥ የነብርሃነ መስቀል አንጃነትን ከፈጠሩት ዋና ዋና ነገሮቹ አንዱ በድርጅት ውስጥ የግለሰብን አምልኮ (individual cult) ቦታ እንዳይኖረውና ለድርጅታዊ አሠራር ጠር እንዳይሆን በማሰብ በነሐሴ ወር 1967 ዓ.ም ኢሕአፓ ራሱን ባዲስ መልክና ባዲስ ስም ሲያደራጅ “ ዋና ፀሃፊ” የሚባል የስልጣን እርከን በመሰረዙ፤ድርጅቱ ሊቀ መንበርም ሆነ ዋና ፀሃፊ የለውም ተብሎ በመታወጁ፤ ስልጣኑን ይፈልገው የነበረውን ብርሃነ መስቀል አስቆጣው።ያ ደግሞ የግለሰብ አምልኮ ለድርጅት ጠንቅ መሆኑን በግዜ የተረዱ የድርጅቱ አመራሮችለድርጅቱ ደህንነት በማሰብ የወሰኑት እንጂ አሁን አንዳንንድ ቱልቱላ አድርባዮች ለኮለኔል አብይ እጅ መንሻ ለማድረግ እንደሚወሻክቱት በብርሃነ መስቀልና በዘሩ ክሸን መካከል የነበረ የግል ቁርሾ አልነበረም።ሌላው መሰረታዊ ልዩነቶችን የፈጠረው የደርግ መንግስት በሚያዚያ ወር 1968 ዓ.ም በህቡእ ለተደራጁ ድርጅቶች ሁሉ የግንባር ጥሪ ሲያደርግ ብዙሃኑ የኢሕአፓ አመራር ጥሪውን በመሰረቱ እንደሚቀበል ከገለጸ በኋላ፤ መሟላት ያለባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ( ዋና ዋናዎቹ……ህዝባዊ መንግስት ለመመስረት ጥርጊያ መንገድ የሚከፍተው ጊዜያዊ ህዝባዊ መንግስትን ማቋቋም፤ ዴሞክራሲ ያለገደብ እንዲፈቀድ፤ ደርግ እያደረገ የነበረውን ጭፍጨፋ እንዲያቆም፤ለህዝብ ውይይት መድረክ እንዲከፈት ማድረግ፤ይሄውም ሁሉንም የሙያ፤የሰራተኞች፤የሴቶች ማህበራት ያቀፈ እንዲሆን፤ ሁሉም እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ) አስቀምጦ፤ እነኛ ቅድመ ሁኔታዎች ካልተሟሉ ከደርግ ጋር ግንባር እንደማይፈጥር አቋሙን አሳወቀ።ብርሃነ መስቀል ግን ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጡ ትክክል አይደለም ዘው ብለን ገብተን ከደርግ ጋር እንስራ ብሎ የብዙሀኑን ውሳኔ ተቃወመ።ሃቁ ይሄ ሆኖ ሳለ የግለሰቦች ቂምና ቁርሾ ከየት የመጣ ድራማ ነው?!በ ነሐሴ 1968 የኢሕአፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ “ራሳችንን ለመከላከል በከተማ ውስጥ ታጥቀን መንቀሳቀስ አለብን በማለት ሲወስን ብርሃነ መስቀል ደርግ ማርክሳዊ ነኝ ብሎ ያወጀ መንግስት ስለሆነ ማርክሳዊ መንግስትን በትጥቅ አመፅ መቃወም የአብዮታውያን ጸባይ አይደለም ብሎ አምርሮ ተቃወመ። ታድያ ይሄ ምኑ ላይ ነው የግለሰቦች ቂምና ቁርሾ የሚሆነው?አንጃነት ፈጥሮ ከደርግ ጉያ ውስጥ በመግባት የጓዶችን ስም ዝርዝር አሳልፎ ለፋሺስቶች መስጠትና ወጣቱን ለጭፍጨፋ መዳረግ ምኑ ላይ ነው ፃዲቅነቱ? የዛ ሁሉ ጀግና ወጣት ህይወት የተገበረበትን የኢሕአፓ ህዝባዊ ትግልን ላሁኑ ትውልድ ተዛብቶ እንዲቀርብ ማድረግ፤ በህይወት በሌለና እራሱን መከላከል በማይችል ሰው ላይ የውሸት ዘመቻ መክፈት ጥቅሙ ለማን?? ዘርሁ ክህሸን ማለት ይሄ ነው!!ዘርሁ ክህሸን በ 1934 ዓ.ም በ ትግራይ አዲግራት ውስጥ በምትገኝ አዲ አመተክርስቶስ በምትባል ትንሽ ከተማ ውስጥ ተወለደ። እድገቱ በ አዲግራት አጋሜ የነበረው ዘርሁ ክህሸን የመጀመርያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ በወቅቱ ቀዳማዊ ኅ/ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ያሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመግባት የኢኮኖሚክስ ትምህርቱን ተከታትሏል። እንደማንኛውም የዛ ዘመን ወጣቶች በትምህርቱ ጎበዝ የነበረው ዘርሁ ክህሸን በወቅቱ በነበረው የተማሪዎች እንቅስቃሴ ግንባር ቀደም መሪ፤ ጀግና፤ፊት ለፊት የሚጋፈጥ፤ ደፋርና አይበገሬ ኢትዮጵያዊ ወጣት ነበር።በዚህም በተማሪው ትግል በነበረው ጉልህና የመሪነት ሚና ምክንያት ዘርሁ ክህሸን በ 1957 ዓ.ም የቀዳማዊ ኅ/ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች “ መሬት ላራሹ” የሚል መፈክር አንግበው ድምጻቸውን ለፓርላማ ያሰሙበትን ታሪካዊ ሰልፍ ካደራጁት መሀል አንዱና ግንባር ቀደሙ ነበር።በዚሁ ሰልፉም ምክንያት ከትምህርታቸው ከተባረሩት ዘጠኝ ተማሪዎ አንዱ ነበር።ከሱ ጋር የተባረሩት ገብሩ ገ/ወልድ፤ ሀይሉ ገ/ ዮሃንስ፤ዮሃንስ ስብሃቱ፤ታዬ ጉርሙ፤ስዩም ወ//ዮሃንስ፤ ብርሃነ መስቀል ረዳ፤ሀብቴ ወ/ጊዮርጊስና ሚካኤል አበበ ነበሩ። ትግሉ ከተማሪው ትግል ወደ ከፍተኛ ደረጃ አድጎ ተደራጅቶ ትግል የወቅቱ ጥያቄ በሆነበትም ወቅት ከኢሕአፓ መስራቾች አንዱ በመሆን ድርጅቱን በራሱ ፈቃድ ጥሎ እስከወጣበት 1972 ዓ.ም ድረስ በኢሕአፓ የፖሊት ቢሮ ውስጥ በአመራርነት በቆራጥነት ታግሏል። ደፋርና በአላማው ፅኑ አቋም የነበረው ዘርሁ ክህሸን በድርጅቱ ወሳኝ በሆኑ ተልእኮዎች ላይ ከአባሎች ጎን ተሰልፎ በግንባር ቀደምትነት ይሳተፍ እንደነበረ የሚያውቁት ጓዶች ይመሰክራሉ።በወቅቱ በድርጅቱ፤ በቅርብ ጓዶቹና ጓደኞቹ ላይ በደረሰው ከፍተኛ እልቂትና ጉዳት ምክንያት ተስፋ የመቁረጥ ሁኔታ የታየበት ዘርሁ ክህሸን፤ ከድርጅቱ በፍቃዱ ከወጣና በስደት ቆይቶ በ 1994 ዓ.ም በአምስተርዳም ሆላንድ በደረሰበት ህመም ምክንይት ከዚህ አለም በሞት እስከተለየበት ጊዜ ድረስ በትግል የቀጠሉትን አክብሮ የኖረ ጓድ ነው።አምስተርዳም ሆላንድ ለረጂም አመታት በኖረበት ወቅት በአንዳንድ የኮሚኒቲ ስብሰባዎች ብቅ ሲል የሚያውቁት የዛ አካባቢ ሰዎች ዘርሁ ክህሸንን ሲገልፁት ልታይ ልታይ የማይል፤ቀደም ቀደምን የማያውቅ ማዳመጥን የሚወድ፤ ብዙ ማውራትን የማይወድ እስከ እለተ ሞቱ በኢትዮጵያዊነቱ ኮርቶ የኖረ አድርገው ያቀርቡታል።

ክብር ከፋሺስቶች ጋር ሲታገል ግንባሩን ለጥይት እየሰጠ በጀግንነት ለተሰዋ አይበገሬ ትውልድ!!