October 27, 2020

ሰበር መረጃ! የአብን ከፍተኛ አመራሮች በስብሰባ ላይ እንዳሉ በአዲስ አበባ ፖሊስ ሠራዊት ተከበዋል

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ /አብን/ ከፍተኛ ስራ አስፈፃሚዎች ፤ አዲስ አበባ 4ኪሎ በሚገኘው ዋ/ፅ/ቤት በስብሰባ ላይ እንዳሉ ፥ ከፍተኛ ቁጥር ባለው አዲስ አበባ ፖሊስ ሠራዊት ተከበዋል!

አመራሮቹ ሠላማዊ ሠልፉን በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠትና ውሳኔ ለማሳለፍ ከትናንት ጀምረው በፅ/ቤት በስራ ላይ እንደሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ፥ በአሁኑ ሠአት በመንግሥት አዲስ አበባ ፖሊስ ሠራዊት ታግተዋል! በክልሉ ከተሞች በተመሳሳይ መትረየስ የታጠቀ ሠራዊት ከተሞችን ፓትሮል እያደረገ ህዝቡን ማስፈራራት ቀጥሎበታል!

ፓርቲያችን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ በአማራ ሕዝብ ላይ የተፈፀመውንና እየተፈፀመ ያለውን ተከታታይ የዘር ፍጅት ለማውገዝ ጥቅምት 18/2013 በአማራ ክልል እንዲሁም ጥቅምት 22/2013 በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፎችን መጥራቱ ይታወሳል።

የአብን ከፍተኛ አመራሮችን ስለሰልፉ ዝርዝር ሁኔታዎች በዋና ጽ/ቤቱ እየመከሩ ባሉበት ወሳኝ ሰዓት የአዲስ አበባ ፖሊስ ከበባ በመፈፀም መግባትና መውጣትም አትችሉም የሚል አፈና በመግባቱ የታቀደውን ሰልፍ በተቋማዊ ማዕከላዊነት ለመምራት እና ለሰልፉ የተዘጋጁ ሎጂስቲኮችን ለማንቀሳቀስም ሆነ ሰልፉን ለመምራት ስራ አስፈፃሚው ወደ ክፍለ ሀገር እንቅስቃሴ ለማድረግ ተቸግረናል።

በዚህ የተነሳም አብን የጠራውን ሰልፍ በኃላፊነት መምራት የማይችል መሆኑን የድርጅታችን አባላት፣ ደጋፊዎችና መላው ሕዝባችን እንድታውቁት እንፈልጋለን።

መንግስት አማራ ማዘን እንኳን አይችልም በሚል እርቃን የወጣ አምባገነንነት ውስጥ በመግባቱ በቀጣይ መደረግ ስለሚገባቸው የትግል አካሄዶችን በተመለከተ የምናሳውቅ መሆኑንም ጨምረን እናሳውቃለን።

ሰበር መረጃ!
***
ፓርቲያችን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ በአማራ ሕዝብ ላይ የተፈፀመውንና እየተፈፀመ ያለውን ተከታታይ የዘር ፍጅት ለማውገዝ ጥቅምት 18/2013 በአማራ ክልል እንዲሁም ጥቅምት 22/2013 በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፎችን መጥራቱ ይታወሳል።

የአብን ከፍተኛ አመራሮችን ስለሰልፉ ዝርዝር ሁኔታዎች በዋና ጽ/ቤቱ እየመከሩ ባሉበት ወሳኝ ሰዓት የአዲስ አበባ ፖሊስ ከበባ በመፈፀም መግባትና መውጣትም አትችሉም የሚል አፈና በመግባቱ የታቀደውን ሰልፍ በተቋማዊ ማዕከላዊነት ለመምራት እና ለሰልፉ የተዘጋጁ ሎጂስቲኮችን ለማንቀሳቀስም ሆነ ሰልፉን ለመምራት ስራ አስፈፃሚው ወደ ክፍለ ሀገር እንቅስቃሴ ለማድረግ ተቸግረናል። … See More