October 31, 2020Konjit Sitotaw

ጋዜጠኛ አብርሃ በላይየኢትዮ ሚዲያ መስራች እና ዋና አዘጋጅ

የህወሃት አቋም አለማወቅ ውድ ዋጋ ያስከፍላል። ደርግ እድሜው ያጠረው ያንን ሀቅ ባለማወቁ ነበር። ትህነጎች የሚናገሩትን 100% በሚባል መልኩ ይተገብሩታል። ቢመረንም ሀቅ ነውና መቀበል ግድ ይለናል።

–የጠላነውን ማናናቅ አይጠቅመንም። ይልቁንስ የጠላት ጠንካራ ጎኑ ምንድነው ብሎ መፈተሽ አዋቂነት ነው። የአብይ ስህተት እንደውቅያኖስ ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ ለጥ ብሎ ድጋፉን ሰቶት የነበረውን የኢትዮጵያ ህዝብን ዘሎ ወደ ኤርትራ በመዝለቅ ከአምባገነኑ ኢሳያስ አፈወርቂን ጋር መጎዳኘቱ ነው። ምክር የሚሰማ መስሎን ቀደም ብለን በትህነግ እና በትግራይ ህዝብ መካከል የኖረውን ቀጭን ገመድ በጥሶ፣ የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጥቶ ከኢትዮጵያዊው ወገኑ ጋር እንዲያሰልፍ መክረን ነበር።

አድማጭ አልተገኘም። አብይ የደርግ እጣ ፈንታ ሊገጥመው ይችላል ብለን ነበር። የፈራነው እየደረሰ ነው። ይህ ሊሆን የቻለው ወርቃማ እድል ያገኘው ህወሃት የትግራይ ህዝብን ከጎኑ ለማሰለፍ በመቻሉ ነው። የአብይ-ኢሳያስ የጋራ ግንባር ጦርነት ቢጀመር፣ ህወሃት ቅድሚያ የሚሰጠው ከጓሮው በኩል ሊያጠፋው የሚመጣውን ጠላቱን ቀድሞ መደምሰስ ይሆናል።

በግርግር የኤርትራን ህዝብ ከባርነት ካወጣም እሰየው! ያኔ ፊቱን ወደ ደቡብ እንደሚያዞር ነው። ኢትዮጵያን መልሶ ይቆጣጠራል እያልኩ አይደለም። ግን ትህነግ ሀገር የማተራመስ አቅም አለው ባይ ነኝ። ታድያ ያኔ ኢሳያስን ያጣው አብይ የፖለቲካ ብልጥነት ማሳየት አለበት። አስቸኳይ፣ ሁሉም-አቀፍ ብሄራዊ እርቅ ጠርቶ ውድዋ ኢትዮጵያችንን ከሶሪያነት ማዳን!