November 2, 2020

በትላንትናው ዕለት በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ቃንቃ ቀበሌ ጨለማን ተገን በማድረግ ባደረሰው ጥቃት ሰላማዊ ዜጎች በአሰቃቂ ሁኔታ በጅምላ በገደለው ኦነግ ሸኔ ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አስታወቀ።

የክልሉ መንግሥት እንደገለጸው፣ ኦነግ ሸኔ በትላንትናው ዕለት በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ቃንቃ ቀበሌ ጨለማን ተገን በማድረግ ባደረሰው ጥቃት ሰላማዊ ዜጎች በአሰቃቂ ሁኔታ በጅምላ ተገድለዋል።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከሕዝብ እና ከሁሉም የመንግሥት የፀጥታ መዋቅር ጋር በመሆን እነዚህን ጥቃት አድራሾች ለቃቅሞ አስፈላጊውን እርምጃ የሚወስድባቸው መሆኑን ነው የገለጸው።

የክልሉ መንግሥት ለተጎጂዎች ቤተሰቦች እና ዘመዶች እንዲሁም ለመላው ሕዝብ መፅናናትን ተመኝቷል።

በጉዳዩ ላይ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በአፋን ኦሮሞ ያወጣው መግለጫ የአማርኛ ትርጉም እንደሚከተለው ይቀርባል

መንግሥት የሕዝቡን ፍላጎት እና ጥያቄን ከግንዛቤ በማስገባት እያከነወነ ባለው የልማት፣ ሰላም እና የሥርዓት ግንባታ ላይ በማተኮር ትርጉም ያለው ሥራ እየሠራ ባለበት በዚህ ምዕራፍ ከለውጡ ተቃራኒ የቆሙ ኃይሎች በሕዝቡ ላይ አሰቃቂ አደጋዎችን ማድረሳቸውን ቀጥለውበታል።

እነዚህ ኃይሎች እንደ ሀገር እና እንደ ክልል የፖለቲካውን እና የዴሞክራሲውን ምኅዳር ለማስፋት እየተሠሩ ካሉ ሥራዎች በተቃራኒው በመቆም ከባድ የጭቃኔ ድርጊቶችን በሕዝባችን ትከሻ ላይ እየጫኑ ይገኛሉ።

የኦነግ ሸኔ ሽፍቶች ከወያኔ ጋር በመሻረክ የኦሮሚያ ክልልን እና ሀገራችንን ሰላም ለመንሳት እየሠሩ ያሉ መሆናቸው ይታወቃል።

በተለያዩ ጊዜያት የእርስ በርስ የግጭት እና የፍጅት አጀንዳዎችን በመቅረፅ በሚዲያ በማወጅ እና በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገር በገቡ ዘመናዊ መሣሪያዎች በሰላም አስከባሪዎች፣ በመንግሥት መዋቅሮች እና በተለያዩ የኅብረተሰቡ አካላት ላይ የግድያ እርምጃዎችን በመውሰድ አለመረጋጋት እንዲፈጠር ሲያደርጉ ቆይተዋል።

እነዚህ ኃይሎች ጭካኔ በተሞላው በዚህ ድርጊታቸው የሕዝቡ ሥነ-ልቦና እንዲሸረሸር፣ ሁሉም ሰው በስጋት እንዲሞላ እና ከዕለት ተዕለት ሥራው ርቆ በረሃብ እና በጥማት እንዲጠበስ እያደረጉ ይገኛሉ። –

በተለይ በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኙ ዞኖች ውስጥ ሕፃናት፣ ሴቶች፣ አረጋውያን እና ወጣቶች ሳይቀሩ፣ በአሰቃቂ ሁኔታ እንደተገደሉ፣ በእሳት እንደተቃጠሉ፣ በአካል እንደጎደሉ እኑ ሥነ-ልቦናቸው በእጅጉ እንደተጎዳ ይታወቃል።

ከሁሉም በላይ ጫካን ተገን በማድረግ ከቦታ ቦታ የሚዘዋወሩ የኦነግ ሸኔ ሽፍቶች የደፈጣ እንቅስቃሴን በመጠቀም ሰዎችን አፍነው እየወሰዱ አሰቃቂ ጉዳት እያደረሱባቸው መቆየታቸው ይታወቃል።

በተለያዩ ጊዜያት የአካባቢውን የፀጥታ አካላት አፍነው በመውሰድ ጫካ ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገድሉ እንደነበርም እንዲሁ።

የኦነግ ሸኔ ሽፍቶች እስካሁን ሲፈፅሙ በቆዩት የሽብር ድርጊት በርካታ ቤተሰቦች ተለያይተዋል፣ ልጆች ያለ እናት እና አባት ቀርተዋል። የግል እና የሕዝብ ንብረትን በማውደምም የማይሽር ጠባሳ በሕዝቡ ላይ እየፈጠረ ይገኛል።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የተሰጠውን የሕዝቡን ሰላም የማረጋገጥ ኃላፊነት ለመወጣት ሰፊውን ሕዝብ ባሳተፈ መልኩ የሕግ የበላይነት የማስከበር ሥራን እያከናወነ ይገኛል።

የወያኔ አሽከር ሆኖ እያገለገለ የሚገኘው የኦነግ ሸኔ ሽፍታ ሕዝብ እና መንግሥት በጋራ በመሆን እየሠሩት ባለው የሕግ የበላይነትን የማስከበር ሥራ ተጠራርጎ በመጥፋት ላይ ይገኛል።

በዚህ የሕግ የማስከበር ሥራ የቀብር አፋፍ ላይ የሚገኘው ኦነግ ሸኔ፣ ተስፋ በመቁረጥ ስሜት በአንድ ቦታ በሚኖር ሕዝብ ላይ ጥቃት በማድረስ ላይ ይገኛል።

ኦነግ ሸኔ በትላንትናው ዕለት በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ቃንቃ ቀበሌ ጨለማን ተገን በማድረግ ባደረሰው ጥቃት ሰላማዊ ዜጎች በአሰቃቂ ሁኔታ በጅምላ ተገድለዋል።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከሰፊው ሕዝብ እና ከሁሉም የመንግሥት የፀጥታ መዋቅር ጋር በመሆን እነዚህን ጥቃት አድራሾች ለቃቅሞ አስፈላጊውን እርምጃ የሚወስድባቸው መሆኑን አስታውቋል።

ለተገጂዎች ቤተሰቦች እና ዘመዶች እንዲሁም ለመላው ሕዝብ መፅናናትን ተመኝቷል።

app-facebook

Oromia Communication Bureau5 hours ago

Ibsa Bulchiinsa Mootummaa Naannoo Oromiyaa

Boqonnaa mootummaan fedhiifi gaaffii ummataa xiinxaluudhaan hojiiwwan misoomaa, nageenyaafi ijaarsa sirnaarratti fuulleffatee hojii hiika ol’aanaa qabu hojjechaa jiru kanatti, humnoonni faallaa jijjiiramaa dhaabbatan ummatarratti balaawwan suukanneessaa geessisuu itti fufaniiru. Akka biyyaafi naannootti hojiiwwan dirree siyaasaafi demokraasii bal’isuuf hojjetamaa jiran faallaa dhaabbachuudhaan eelaa gochoota hammeenyaa ulfaataa gati…See More

1K716267