Dejene Assefa

Yesterday at 2:10 AM  ·

መላው ህዝብ እና የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሊያውቃቸው የተገቡ 10 ወቅታዊ መረጃዎች!!!!

የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ!!!! ማንበብ ያስፈልጋል!!!==============================

1ኛ) ትህነግ ምሽግ ቁፋሮ እንደ አዲስ ጀምሯል:: በራያ ዋጃ ጥሙጋ : ስሌን ውሃ እና ራያ መረዋ በተመረጡ ቦታዎች ምሽግ እየተቆፈረ ሲሆን ከ 700 በላይ ጆንያዎች (አፈር የሚሞላባቸው) ወደነዚህ ቦታዎች ተልኳል::

.2ኛ) በራያ ህዝብ ላይ አፈናውን አጠናክሮ ቀጥሏል:: ትላንትና እና ዛሬ 60 የራያ ተወላጆች በራያ አላማጣ ታፍነዋል:: የአፈናው አመክንዮ ደግሞ ማን ይደግፈናል ማን ይቃወመናል የሚል ማጣራት ለማድረግና ህዝቡን ለማሸማቀቅ ነው:: አፈናውን የሚመሩት እቁባይ (ሚግ) እና ጣሰው ቦጋለ ናቸው:: 60 ሰው ታፍኗል!!!

.3ኛ) የኤርትራ ጦር በራያ ቆቦ በኩል እየገባ ነው የሚል የውሸት ፕሮፖጋንዳ ለመስራት በማሰብ የትህነግ ልዩ ሃይል በ 30 ፓትሮል መኪኖች ተጭኖ ትላንት ወዲያ በውድቅት ለሊት ወደ ራያ አላማጣ መዝለቁ ታውቋል:: ይህም አስቀድመው ሊሰሩት የፈለጉት ሴራ ስላለ እንጅ የኤርትራ ጦር የሚባል ኮሽታ እንደሌለ ተረጋግጧል::

.4ኛ) ትህነግ ለልዩ ሃይሉ የሚሆን የመከላከያ ሰራዊትን መለዬ እያዘጋጀ መሆኑ ታውቋል:: የመከላከያን የደንብ ልብስ አስለብሶ ሊፈፅመው ያለ ሻጥር እንደሚኖር ተገምቷል:: መንግስት ከፍተኛ ጥንቃቄ ያድርግ:: የሰሜን እዝ መከላከያ ሌላውን ማህበራዊ ጉዳይ ትቶ በዚህ አንገብጋቢ ጉዳይ ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያድርግ:: ውስጡን ያጥራ:: አመራሩን ይለውጥ:: የራያ ቆቦ ህዝባችንም ታርጌት በመደረጉ አሁንም አመራሮቹን አበክሮ ይፈትሽ:: ጥንቃቄ ያድርግ:: ተናግሬያለሁ!

.5ኛ) ትህነግ የማያምናቸውን የራያ ተወላጆችን ትጥቅ እያስፈታ ነው:: ራያ ዋጃ ስድስት (6) ሚሊሻዎችን ትጥቅ ያስፈቷቸው ሲሆን የሰጧቸው ምክንያት እድሜያችሁ ገፍቷል የሚል ነው:: በቅያሪ ግን ቁመህ ጠብቀኝ እና 10 ጎራሽ የማይረባ ያረጀ መሳሪያ ውሰዱ እያሏቸው ይገኛል::

.6ኛ) ትላንት ጥቅምት 21 በራያ አላማጣ ከተማ ዙሪያ የሚገኙ የራያ ሚሊሻዎችን ሰብስቦ ሚሊሻው 10,000 ብር ማባበያ እንዲሰጠውና እንደ ልዩ ሃይሉ #ለ 7 አመት ኮንትራት እንዲፈርም ሲያስገድድ ውሏል:: አብዛኛው ሚሊሻ ፈፅሞ እንደማይፈርም እና በቀጣይ የራሱን አማራጭ ይወስዳል ተብሏል:: ክብር ለራያ ሚሊሻ!! አስቂኙ ነገር ትህነግ 7 አመት እቆያለሁ ብሎ የማያምንበትን ነገር መናገሩ ሲሆን ሚሊሻውም አሽሙሩ ገብቶት ሲሳሳቅባቸው አምሽቷል::

.7ኛ) የራያ ወጣት በልዩ ሃይል አባልነት ተመዝግቦ ለጦርነት እንዲዘጋጅ የሚል ግዳጅ የተጀመረ ሲሆን እያንዳንዱ #ቀበሌ 600 ወጣት እንዲያመጣ ታዟል:: ነባር የመከላከያ ሰራዊት አባል የነበሩም ልዩ ሃይሉን እንዲቀላቀሉ ታዟል:: ወላጆች ልጆቻቸውን ለጦርነት እንዲሰጡ እየተገደዱ ነው:: በአጠቃላይ የብሄራዊ ውትድርና ግዳጅ ራያ ላይ ተጀምሯል::

.8ኛ) እያንዳንዱ ነዋሪ 100 ብር እንዲያዋጣ ተገዶ በየቤቱ እያተዞረ እያስከፈሉት ሲሆን ቤት ተከራይተው የሚኖሩ ደግሞ 50ብር እንዲያዋጡ ግዳጅ ተጥሎ በሃይል እንዲያዋጡ ተደርጏል:: ባለሃብቶች የተጣለባቸው ክፍያ ብዙ ሲሆን እያንዳንዱ ባለሃብት በደብዳቤ ይታዘዛል ተብሏል:: ራያ ላይ ወከባው በዝቷል:: ሽብሩ : አፈናው እና ማሸማቀቁ ቀጥሏል:: ጦር አውርድ እያሉ ነው:: የጦርነት ድባብ አለ::

.9ኛ) ጦርነት ከተጀመረ ራያ አላማጣን እና ራያ ኮረምን ሙሉ ለሙሉ አውደመው እንደሚሄዱ ከራሳቸው ከልዩ ሃይሎቹ አንደበት የተሰማ ሲሆን ይህም የዋና ባለስልጣናቱ ዕቅድ መሆኑ ተረጋግጧል:: ስለዚህ ራያ እና ወልቃይት የጦርነት ኮሪደር እንዳይሆኑ መንግስት ቅድመ ጥንቃቄ ያድርግ:: የትህነግ አሸባሪው ቡድን መቀሌ እንጅ ራያ ውስጥ እንደሌለ ይታወቃል::

.10ኛ) ትህነግ በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ የራያ ዋጃ ድንበርን ዋና መንገዱን እንደሚዘጋ ተነግሯል:: ይህም የሃገር መከላከያ ሰራዊት እንዳያልፍ ለማድረግ ነው ተብሏል:: መከላከያ የሚያልፍ ከሆነ ጦርነት ሊጀምሩ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል:: አስታውሱ- ራያ እና ወልቃይት የወቅቱ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ማዕከላት ናቸው!!! የትህነግ እንዘጭ እንቦጭ ራያን እና ወልቃይትን ላለማጣት እንጅ አራት ኪሎ ለመመለስ አይደለም!!! ስለዚህ ሁለቱን ለማጥፋት አይቦዝንም:: ራያ እና ወልቃይት ልዩ ትኩረት ያሻቸዋል!!!

.ማጠቃለያ!!!!

ትህነግ በከፍተኛ የገንዘብ እጥረት ቀውስ ነው:: ይህም ሁሉን ነገሩን አቃውሶታል:: በግራም በቀኝም በሰሜንም በደቡብም በውጭም በውስጥም የነበሩት ሁሉም አማራጮች ተዘግተውበታል:: ለልዩ ሃይሉ ደሞዝ መክፈል ተስኖታል:: በመዋጮ እና በቅጣት ህዝብን እየመዘበረ ያለው ስለተጨነቀ ነው:: ሰራተኛው በግዳጅ ከደሞዙ እየተቆረጠበት ያለው ትህነግ ጭንቅ ውስጥ በመግባቱ ነው:: ልዩ ሃይሉ ምሬት ውስጥ ነው:: የሦስት ወር ደሞዝ አልተከፈለውም:: በዚህ ሁኔታ ትህነግ ብዙ እንደማይቆይ ግልፅ ነው:: ምናልባትም ከውስጥ በሚነሳበት ተቃውሞ ሊጠፋ እንደሚችል አውቋል::

ስለዚህ የወሰደው አማራጭ የክብር ሞት ልሙት የሚል ሆኗል:: ቢያንስ ተንፈራግጦ የክብር ሞት ለመሞት ከፌደራል መንግስት ጋር ጦርነቱን ፈልጎታል:: ፈልጎታል ማለት ግን ትንሽ ኮሽ ቢል ተወረርን ብሎ በመጮህ የአለም አቀፉን ማህበረሰብ ጣልቃ ገብነት ለድርድር እንዲገባ ለመጠየቅ እና በሌላ በኩል ደግሞ ኢትዮጵያን እንዲወጉ ያዘጋጃቸው የውጭ ሃይሎች እንዲገቡ ሊያመቻች ካልሆነ በቀር ከግዙፉ የመከላከያ ሰራዊት ጋር ገጥሞ እንደማያሸንፍ ግልፅ ነው:: በመሆኑም የፌደራል መንግስት ከትህነግ ይልቅ ውጩንም ውስጡንም በደንብ ይመልከት:: ያጥራ:: ሚኒስትሮችን እና ኮምሽነሮችን ይመርምር:: የአላማ አንድነት ይፍጠር:: አመራሩ አንድ አቋም ይያዝ:: የውጭ ወራሪዎችን ለመመከት በተገቢው ይዘጋጅ:: ግድቡን ይጠብቅ:: ከአፋር ሶማሊ እና አማር ክልል አመራሮች ጋር በጥልቀት ይስራ:: በዚህ ወቅት የራያን እና የወልቃይትን ህዝብ ደህንነት ማስጠበቅ ቢችል የፌደራል መንግስት ጦርነቱን ያዘግየው::

ጦርነቱ ቢዘገይ ትህነግ በራሱ ሰዓት ተባልቶ ይጠፋል:: አይደለም የራያ እና የወልቃይት ህዝብ የትግራይ ህዝብም ጭምር መሮታል:: ወጣቱ ደክሞታል:: ገበሬው ታክቶታል:: በዶክተር ደብረፅዮን እና በአለም ገብረዋህድ ቡድን መካከል ያለው ከፍተኛ ፍጥጫም ይለይለታል:: ጦርነቱ ቢዘገይ ከውስጡ በሚመጣ ተቃውሞ ብቻ ትህነግ ይጠፋል:: ይህ አልሆን ብሎ የትህነግ ህገወጥነት እና ትንኮሳ አደገኛ ደረጃ ላይ ደርሶ መከላከያ ሰራዊት በአሸባሪው ትህነግ ላይ እርምጃ የሚወስድ ከሆነ ግን: እርምጃው የማያዳግምና በአጭር ስዓታት የሚጠናቀቅ ኦፕሬሽን ሊሆን ይገባዋል!!! DONE ✅